የሥልጠና ዝርዝር
2.8. መደበኛ ገለጻ- ማኅበራዊ ፖሊሲና አዎንታዊ እርምጃ
- ለአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ማሳደግ በአካል ጉዳት ጭብጥ ላይ ተመሥርቶ የሚፈጸም መድልዎን መከልከል ብቻ እንዳልሆነ፣ ግን ደግሞ አካል ጉዳተኞች በሥራው ገበያ የሥራ ስምሪት ዕድሎች ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ መንግሥታት አዎንታዊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይጠይቃል፡፡ ይህ ቅድመ ገቢራዊ አቀራረብ መሥራት ለሚችሉ አካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆን አስፈላጊ ከሆነ ከተገቢ የቴክኒክ እርዳታዎች ወይም ድጋፎች ጋር የሥራ ቦታ አካባቢን ተስማሚ የማድረግ ጥያቄዎችን ያካትታል፡፡ በቀላሉ መድልዎን የሚከለክሉ ሕጎች ወይም ደንቦች ማሳለፍ በቂ አይደለም፡፡
- ሁልጊዜ የተፈቀዱ በሆኑት በማኅበራዊ ፖሊሲ እርምጃዎችና ከእኩል አያያዝ ደንብ ስለሚያፈነግጡ መስተካከል ባለባቸው የአዎንታዊ ተግባር እርምጃዎች መካከል ያለውን ልዩነት ለተሳታፊዎች ክለሳ ያድርጉ፡፡ ለምሳሌ የትራንስፖርት ኩባኒያዎች በአካል ጉዳተኞች ላይ መድልዎ መፈጸም እንደማይችሉ ሕጉ ዝም ብሎ ቢገልጽ ዊልቼር የሚጠቀሙ ሰዎች በአውቶቡሱ መጠቀም መቻላቸውን ለማረጋገጥ በበቂ ሁኔታ ግልጽ አይደለም፡፡ ይልቁን ለዊልቼር ተጠቃሚዎች ተደራሽነታቸውን ለማረጋገጥ ኩባኒያዎች በቂ ብዛት ያላቸው አጫጭር አውቶቡሶች ወይም እንደ ታክሲና ሚኒባስ ያሉትን መግዛትና በመንገዶች ሁሉ እንዲሰማሩ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለሰብአዊ ክብር የሚሰጥ ከበሬታ እንዲህ ያሉትን ማኅበራዊ ፖሊሲዎች መቀረጽ እንደሚጠይቅ በማስረዳት የገለጻ ማሳያ 34ን ተጠቅመው የአንዳንድ ማኅበራዊ ፖሊሲዎች ምሳሌዎችን ያሳዩ፡፡ ተሳታፊዎች ተጨማሪ የማኅበራዊ ፖሊሲዎችን ምሳሌዎች እንዲያመነጩ ያድርጉ፡፡
- የገለጻ ማሳያ 35ን, ተጠቅመው የአዎንታዊ ድርጊት (ወይም ገንቢ ድርጊት) እርምጃዎች ለተጐሳቆሉ ወይም ውክልና ለሌላቸው ወገኖች አባላት አንዳች ዓይነት የአማራጭ አያያዝ በመስጠት የእኩል ዕድል መርሆን ለማሳደግ እንደሚሹ ያስረዱ፡፡ አዎንታዊ እርምጃ መድልዎ እንዳልሆነ አጥብቀው ይግለጹ፡፡ የአዎንታዊ ድርጊት እርምጃዎች የዕድል እኩልነትን ለማሳደግ የሚሹ ሲሆን አንድ ወገን ያጋጠመውን መዋቅራዊ ተጎጂነት ለማሸነፍ የታቀዱ ናቸው፡፡