የሥልጠና ዝርዝር

2.1. መደበኛ ገለጻ - የዓሥድ ድንጋጌዎችና መሪ ሃሳቦች

  • የገለጻ ማሳያ 3ን ተጠቅመው የዓለም ሥራ ድርጅት (ዓሥድ) ምን እንደሆነ ያስረዱ፡፡ ዓሥድ በዋነኛነት ዓለም አቀፍ የሥራ ድንጋጌዎችና መሪ ሃሳቦች በማጽደቅ አማካይነት መስፈርቶችን በማስቀመጥ ተልእኮዎቹን እንደሚያካሂድ ያስረዱ፡፡
  • ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በፊት ጀምሮ እኩል የሥራ ዕድሎችን ማሳደግ የዓሥድ ቁልፍ ዓላማ መሆኑን ያስረዱ፡፡ በ1944 በዓለም አቀፍ የሠራተኞች ጉባኤ የጸደቀውን «የፊላዴልፊያ መግለጫ» ለመመልከት የገለጻ ማሳያ 4ን ይጠቀሙ፡፡
  •  
    አማራጭ መልመጃ፡- ተሳታፊዎች መግለጫውን ልብ እንዲሉና በትክክል ምን ማለት እንደ ሆነ ሃሳቦችና አመለካከቶችን እንዲጋሩ ይጠይቁ፡፡ በአሁኑ ወቅት በየአገሮቻቸው ይህ እምነት ምን ያህል እንደ ተጠበቀ ወይም ውሱንነቶች እንዳሉ ተጨባጭ ምሳሌዎች እንዲሰጡ ይጠይቁአቸው፡፡
  • የገለጻ ማሳያ 5ን በመጠቀም ወደዚህ ወደ እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎች ታሪክ ደረጃ እንድንደርስ በዓሥድ የተወሰዱትን እርምጃዎች አጉልተው ያሳዩ፡፡ ከተጠቀሱት አብዛኛዎቹ ድንጋጌዎች አካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ ሆነው ሳሉ ነገር ግን በሥራ ስምሪትና በሙያ ረገድ የሚፈጸም መድልዎን በሚመለከት በ1958 የወጣው ድንጋጌ (ቁ. 111) አካል ጉዳትን ከመድልዎ ጥበቃ እንደሚያስፈልገው ፈርጅ በተናጥል እንደማይጠቅሰው ለተሳታፊዎች ያመልክቱ፡፡
  • የገለጻ ማሳያዎች 6–8 ያሉትን በመጠቀም እኩል የሥራ ስምሪት ዕድልን አስፈላጊነት ለማጠናከር በዓሥድ በኩል የተወሰዱትን እርምጃዎች አጉልቶ ማሳየትን በመፈጸም ይህን ክፍል ይጨርሱ፡፡