የሥልጠና ዝርዝር
አጀማመር፡- ትውውቅ
- ይህን ክፍለ ጊዜ ለመጀመር ስክሪኑን ያብሩ፡፡ የገለጻ ማሳያ 1
- «መሠረታዊ ደንቦች» የሚለው ወረቀት በግልጽ እንደሚታይና ሌሎቹ የተገላጭ ወረቀቶች እንዳልሸፈኑት ያረጋግጡ፡፡
- የገለጻ ማሳያ 2ን በመጠቀም የዚህን ክፍለ ጊዜ አጠቃላይ ገጽታ ለተሳታፊዎች ያቅረቡ፡፡
- በሴሚናሩ ወቅት ለሚነሡ ውይይት እየተደረገበት ካለው ርእስ ጋር አግባብነት ኖሮአቸው ወይም ሳይኖራቸው የሚነሡ ጥያቄዎችን «የማቆሚያ ቦታ» በተባለው ወረቀት ላይ እንደሚመዘግቡ ለተሳታፊዎች ያሳስቡ፡፡ «የማቆሚያ ቦታ» ጽንሰ ሃሳብ በትምህርቱ ወቅት የሚነሡትን ጥያቄዎችና ጉዳዮች አስተማሪው የሚመዘግብበት መሣሪያ ነው፡፡ በወቅቱ ላለው ርእስ አግባብነት ያላቸው ግን ዘግይቶ ውይይት የሚደረግባቸው ጥያቄዎች የተማሪውን ጥያቄ የሚያረጋግጡ ሲሆን ዘግይቶ ውይይት እንደሚደረግባቸው ጭብጥ ያስቀምጣል፡፡ አግባብነት ለሌላቸው ጉዳዮች አሁንም የተማሪውን ጥያቄ የሚያረጋግጥ ሲሆን እንደ አስተማሪ በሚቻል ሁኔታ መረጃና በሥልጠናው ላልተዳሰሰው ለዚያ ጉዳይ ጥቆማ ለመስጠት ከግለሰቡ ጋር በሌላ ጊዜ እንደሚገናኙ ለማረጋገጥ ለእርስዎ ጠቃሚ ፍንጭ ይሰጥዎታል፡፡