የቃላት መፍቻ
አዎንታዊ እርምጃ
በትምህርትና በሥራ ስምሪት እንደሚደረገው ሁሉ እኩል ዕድልን ለማረጋገጥ በተግባራዊ እርምጃዎች አማካይነት ከዚህ ቀደም የተፈጸመ መድልዎን ለመካስ የሚሻ ፖሊሲ ወይም ፕሮግራም፡፡
ፍትሐ ብሔር (ሲቪል) ሕግ
ከግለሰቦች የግል መብቶችና እነዚህን ከሚመለከቱ ሕጋዊ እርምጃዎች ጋር የሚገናኝ ሕግ፡፡
ሕገ መንግሥት
የአንድ አገር እጅግ ከፍተኛው ሕግ፡፡ በማንኛውም በሚመለከተው አገር ሕገ መንግሥት ውስጥ የተቀመጡት ሃሳቦች መንግሥቱ ለዜጎቹ ያለበትን ኃላፊነትና መንግሥቱ ለዜጎቹ ያረጋገጣቸውን መብቶች ይገልጻሉ፡፡
የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ
ስርቆትን የመሰለ የማንኛውም ወንጀል መፈጽም የሚመለከቱ ሕጎች ወይም ደንቦች፡፡
የዓለም ሠራተኞች ጽህፈት ቤት
የድርጅቱ ቋሚ ጽህፈት ቤት፣ ተንቀሳቃሽ መሥሪያ ቤቶቹ፣ የምርምር ማእከሉና የማተሚያ ቤቱ፡፡
የዓለም ሥራ ድርጅት (ዓሥድ)
በነፃነት፣ በደህንነትና በሰብአዊ ክብር ሁኔታዎች ምቹና ምርታማ ሥራን ለሴቶችና ለወንዶች ለማራመድ የተቋቋመ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ድርጅት፡፡ ዋነኛ ዓላማዎቹ የሥራ ላይ መብቶችን ማሳደግ፣ ምቹ የሥራ ስምሪትን ማበረታታት፣ ማኅበራዊ ጥበቃን ከፍ ማድረግና ከሥራ ስምሪት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በመፍታት ረገድ ማኀበራዊ ውይይትን ማጠናከር ናቸው፡፡
የሠራተኛ ሕግ፣
የሥራ ስምሪትን የሚመለከቱ ሕጎችና ደንቦች፡፡
መድልዎ አልባነት
ሰዎችን ያለ ጭፍን አመለካከት በመልካም ሁኔታ መያዝ፡፡
የቅጣት ሕግ
አንድን ድርጊት የሚከለክሉና ከተፈጸመም ቅጣትን የሚጥሉ ሕጎችና ደንቦች፡፡