አካል ጉዳተኛው ሰው ግጥሞቹን ለመጻፍ በግንባሩ ላይ የታሰረለትን ብሩሽ ይጠቀማል፡፡ ሥዕል በመሥራት በሚያኘው አነስተኛ ገቢ ራሱን ይደግፋል፡፡ይህ ክፍለ ትምህርት ይህን መመሪያ በመጠቀም ረገድ የመማርን ልምድና በሕግ አማካይነት ለአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን በማስከበር ዙሪያ ሊከሰት የሚችል ውጤትን ለማሳደግ ጠቃሚ ምክሮች ይሰጣል፡፡

ይህ የትምህርትና የሥልጠና መመሪያ ከማኅበራዊ አጋሮችና ከሲቪል ኅብረተሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን የአካል ጉዳተኞችን እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎች በውጤታማ ሁኔታ የሚደግፍ ሕግ እንዲያወጡ፣ እንዲተገብሩና እንዲገመግሙ የመንግሥታትን የተሻሻለ አቅም ለመደገፍ የታቀደ ነው፡፡ ያንን ለማሳካት ፖሊሲ አውጪዎች፣ ሕግ አውጪዎች፣ ማኅበራዊ አጋሮች፣ አካል ጉዳተኛ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ለእነርሱ ተሟጋች የሆኑትና ሌሎች ቁልፍ ግለሰቦች አዎንታዊ የሕግ አወጣጥ ውጤት እንዲያገኙ በማስቻል ረገድ ይህ ጠቃሚ መመሪያ ለአስተማሪዎችና ለአሠልጣኞች ይሰጣል፡፡

የኮርስ ፍሬ ነገር

እንደ አስተማሪ እና/ወይም አሠልጣኝ እርስዎ በዚህ መስክ እድገትን የሚደግፉ የማስተማር ልምዶችን በመፍጠርና በመስጠት ለአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን በአዎንታዊ መልኩ ተጽእኖ የሚያደርጉ ሕግና ፖሊሲዎች መቀረጽን ለማነሣሳት ችሎታው አለዎት፡፡ እርስዎ የተለዩ የሕግና የፖሊሲ ለውጦችን በቀጥታ የማያመጡ ሆነው ሳለ የሚያስተምሩአቸው ወይም የሚያሠለጥኑአቸው ግለሰቦች ያ ቀጥተኛ ተጽእኖ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት መስክ አዎንታዊ ለውጦች ማስገኘት በተለያዩ ደረጃዎች ማለትም የወቅቱን ሕግ በመለመጥና በማሻሻል፣ አዲስ ሕግ በመቅረጽ እና/ወይም ደንቦችን፣ ፖሊሲዎችን፣ ወይም የተለዩ ሕጎችን ለመተግበር በሚወጡ መመሪያዎች አማካይነት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ዕድሎች ለማሳደግ በእርስዎ የትምህርት ክፍሎች ውስጥ ያሉት ግለሰቦች ደረጃ በወቅቱ፣ ወይም አሁን፣ ወይም ወደፊት ምንም ሊሆን ይችላል፡፡ ቁልፉ የማስተማር ዕድሎችን እንዴት መጠቀም እንደሚገባና እያንዳንዱ የኮርስ ተሳታፊዎች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድል አጀንዳን ለማሳደግ የሚያስፈልጋቸውን መረጃ እንዴት ማስጨበጥ እንደሚቻል ማወቁ ላይ ነው፡፡ እነዚህን ግቦች ለመማሳካት እንዲረዳዎት ይህ የትምህርትና የሥልጠና መመሪያ ሰባት ክፍለ ትምህርቶችን ያቀርብልዎታል፡፡

ክፍለ ትምህርት አንድ፡-

አስተማሪው ይህን መመሪያ እንዲጠቀም፣ የማስተማር ዘዴውንና በኮርሱ ተሳታፊዎች ላይ የሚያመጣውን ውጤት ለማሳደግና ለመለካት ያስችለዋል፡፡

ክፍለ ትምህርት ሁለት

በአካል ጉዳት ጽንሰ ሃሳብና በመሠረታዊው የሰብአዊ መብቶች ጭብጥ ዙሪያ ያሉትን ዋነኛ መርሆዎች ጨምሮ የውቅቱን የአካል ጉዳት ሕግ አዝማሚያዎች ይቃኛል፡፡

ክፍለ ትምህርት ሦስት፡-

የአካል ጉዳት ሕግ ስፋትን፣ የመድልዎ ዓይነቶችንና ተመጣጣኝ ማመቻቸት ጽንሰ ሃሳብን ጨምሮ የመድልዎ አልባነት ሕግን ይዳስሳል፡፡

ክፍለ ትምህርት አራት፡-

አስገዳጅ የሆኑና አስገዳጅ ያልሆኑ አቀራረቦችን፣ ኰታዎች በተግባር እንዲሠሩ ለማድረግ ምክሮችን ጨምሮ የኰታ አሠራሮችን አጠቃላይ እይታ ይሰጣል፡፡

ክፍለ ትምህርት አምስት፡-

ትራንስፖርትና ልዩ መሣሪያዎችን ጨምሮ የትግበራ ዕቅድና መታየት ያለባቸውን ልዩ ደንቦች ዝርዝር ያቀርባል፡፡

ክፍለ ትምህርት ስድስት፡-

ሕግና ፖሊሲ ለማርቀቅ የሚረዱ ስትራቴጂዎችን፣ እንዲሁም ሂደቱን ለመደገፍ ወሳኝ ባለ ድርሻዎች በሂደቱ ውስጥ በሚሳተፉበት ሁኔታ ዙሪያ ሃሳብ ያቀርባል፡፡

ክፍለ ትምህርት ሰባት፡-

ቁጥጥርና ተገዥነትን መገምገም፣ እንዲሁም የሕግ አጠቃቀምን ጨምሮ ሕግችና ፖሊሲዎች እንዴት ተፈጻሚ መሆን እንደሚኖርባቸው ይመለከታል፡፡

እንደ አሠልጣኝ እርስዎ ለማስተማር የሚወስኑትና የመማር ልምዱን እንዴት መቅረጽ እንዳለብዎት የሚወስኑት በሚያሠለጥኑአቸው ሰዎችና እርስዎ በሚሹአቸው ውጤቶች ላይ ይመረኰዛል፡፡ ችሎታ ያላቸውን የኮርስ ተሳታፊዎች በሚያስቡበት ጊዜ መንግሥታትን፣ የአሠሪዎች ማኅበራትን፣ የሠራተኞች ማኅበራትን፣ ሕግ አውጪዎችን/የፓርላማ አባላትን፣ እንደ ማኅበረሰብ ተሀድሶ ፕሮግራሞች ያሉ የአካባቢ ድርጅቶችን፣ የመንግሥት ተወካዮችን፣ የአካል ጉዳት ቡድኖችና ማኅበራትን፣ የወላጆች ቡድኖችና ማኅበራትን፣ የሠራተኛ ማኅበራትን እንዲሁም የነጋዴ ቡድኖችን እንዳካተቱ ያረጋግጡ፡፡ እነዚህ ቡድኖች ሁሉ በእኩል ዕድሎች ውስጥ የሚጫወቱት ሚና ያለ ሲሆን በዚህ መስክ አዎንታዊ ለውጦችን በማስገኘት ረገድ መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡