ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦች

የመሠረታዊ ሃሳቦችን ጠንካራ መሠረት በመስጠት ፈጠራዊ የአካል ጉዳት እኩል የሥራ ስምሪት ዕድል ሕግ እንዲቀርጹ ፖሊሲ አውጪዎችን መደገፍ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ይህ ክፍለ ትምህርት ለእኩል የሥራ ስምሪት ዕድል መንታ ትርጕም ያቀርባል፣ ይህም በአካል ጉዳት ላይ የተመሠረተ መድልዎን መከልከል እና አካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎች እንደሚያገኙ ለማረጋገጥ የሚወሰድ አዎንታዊ እርምጃ ነው፡፡ አካል ጉዳት በሕግ ውስጥ መጠቃለል በሚችልበት ዙሪያ አካል ጉዳትን ለማብራራት ከሚያገለግሉት ሁለት አቀራረቦች ጋር ዐውደ ንባብ የቀረበ ሲሆን በሕግ አማካይነት ለአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ማስከበር የተባለው ዐውደ ንባብ በእንግሊዝኛ በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-

http://www.ilo.org/global/publications/ilo-bookstore/order-online/books/WCMS_091340/lang--en/index.htm

በዚህ ክፍለ ትምህርት የሚታየው ስኬታማ የይዘት አቀራረብ እርስዎ እንደ አስተማሪ ለሚቀርቡት መረጃዎች በሚሰጡት ዕሤቶች ላይ በተመሠረተ ጠንካራ ጭብጥ ላይ ይመረኮዛል፤ ይኸውም የአካል ጉዳት አጋጣሚን በሚመለከት የየራሳቸውን ዋጋዎችና የአመለካከት መንገዶች እንዲዳስሱና እንዲፈትኑ ለኮርስ ተሳታፊዎች ዕድል መስጠት ነው፡፡ ተሳታፊዎች እንዲመልሱት መቅረብ ያለበት አስፈላጊ ጥያቄ የአካል ጉዳት አጋጣሚ ከየት ይመነጫል ብለው እንደሚያስቡ ነው – ተፈጥሮአዊ መሆኑ ለግለሰቡ ነው ወይስ ለአካባቢው? ከዚህ በታች በሚገኘው የአሠልጣኙ ዝርዝር አመለካከቶቻቸውን በዚህ መስክ እንዲዳስሱ ተማሪዎችን ለመርዳት መልመጃዎች ቀርበዋል፡፡