«መልክን ሳይሆን አቅምን እንመልከት» – የግራ እጅ ሳይኖራት የተወለደችው ሳቦፕሀ ቪዥን ፈንድ ካምቦድያ ለተባለ ድርጅት በኮምፒውተር ዳታ አስገቢነት ትሠራለች፡፡

ከ6 እስከ 9 ሰዓት (መማርን ለማጠናከር የተመረጡ አማራጭ መልመጃዎች በሚወስዱት የጊዜ መጠንላይ በመመርኮዝ)

ይህ ክፍለ ትምህርት አንድ አገር የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ ለመተግበር በሚያቅድበት ጊዜ መጤን ያለባቸውን አስፈላጊ ነጥቦች ይዘረዝራል፡፡ ይዘቱ በመረጃ ዘመቻዎች ሚና፣ የሕጉን ትግበራ ለመደገፍ ጥበቃ ለሚደረግለት የአካል ጉዳተኞች ሁኔታ እና/ወይም ለድርጅቶችና ለአሠሪዎች ሊሰጡ በሚችሉ ወሳኝ የሥራ ስምሪት ድጋፍ እርምጃዎች ዙሪያ ውይይት ያካትታል፡፡

የመማር ዓላማዎች

በኮርሱ ፍጻሜ ተሳታፊዎች ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች ዙሪያ በቂ ችሎታ ይኖራቸዋል፡-

  • ለአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ ትግበራ በሚታቀድበት ጊዜ የመረጃ ዘመቻን አስፈላጊነት ያብራራሉ፡፡.
  • ሕጋዊ ትግበራን ለመደገፍ ሊወስዱ የሚችሉትን ሦስት መሠረታዊ የሥራ ስምሪት ድጋፍ እርምጃዎች ዓይነቶች ይለያሉ፡፡
  • በሥራ ስምሪት ድጋፍ መልክ በተለየ ሁኔታ ከሥራ ጋር የተያያዙ ልዩ መሣሪያዎችና ለማስተካከያ የሚደረጉ የገንዘብ እርዳታዎችን አስፈላጊነት ይዘረዝራሉ፡፡
  • በሥራ ስምሪት ድጋፍ መልክ ለዕለታዊ ኑሮ የሚጠቅሙ ልዩ መሣሪያዎች የመስጠትን አስፈላጊነት ይዘረዝራሉ፡፡
  • ወደ ሥራ ሲሄዱና ሲመለሱ ለአካል ጉዳተኞች አስተማማኝና ተገቢ መጓጓዣ ለማሳደግ አቀራረቦችን ይለያሉ፡፡
  • የመድልዎ አልባነት ሕግ ግዴታዎችን በማሟላት ረገድ አሠሪዎችን ለመርዳትና ለመደገፍ ሌሎች የቴክኒክ አማካሪና የድጋፍ አገልግሎቶችን ያወያያሉ፡፡
  • አካል ጉዳተኞችን በሥራ ስምሪት ለማበረታታትና ለመደገፍ የገንዘብ ድጋፎችን በመስጠት ረገድ የተለዩ አቀራረቦችን ይለያሉ፡፡
  • ጥበቃ በሚረግለት ሁኔታ ስር ላሉ ግለሰቦች የሥራ ስምሪትን ለማበረታታት ለአሠሪዎች የገንዘብ ድጎማ በመስጠት ረገድ አማራጮችን ይለያሉ፡፡