ከ6 እስከ 8 ሰዓት (መማርን አማራጭ መልመጃዎች በሚወስዱት የጊዜ መጠን መልመጃዎች መጠን ላይ በመመርኮዝ)
ይህ ክፍል ውጤታማ የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ በማውጣት ረገድ ምክር ሊጠየቁና ኃላፊነቱ ሊሰጣቸው ከሚገባው ባለ ድርሻዎች ጋር ግንኙነት ላላቸው ፖሊሲና ሕግ አውጪዎች አጠቃላይ መመሪያ ይሰጣል፡፡ አካል ጉዳተኞችና የሚወክሉአቸውን ድርጅቶች፣ አሠሪዎችና የአሠሪዎችና ማኅበራትን፣ ሠራተኞችና የሠራተኛ ማኅበራትን፣ አገልግሎት ሰጪዎችና ፍላጎቱ ያላቸውን ሌሎች ወገኖች ጨምሮ የተለያዩ ባለ ድርሻ ወገኖች ጠቅላላ እይታ ድጋፋቸውንና ተሳትፎአቸውን ለማግኘት ከሚጠቅሙ ስትራቴጂዎች ጋር ቀርቦአል፡፡ የምክክር ሂደቱ እንዴት መዋቀር እንዳለበትና ሌሎች አገሮች አስቀድሞ ሂደቱን እንዴት እንደ ቀረጹ ልዩ ምሳሌዎች ቀርበዋል፡፡
የመማር ዓላማዎች
በኮርሱ ፍጻሜ ተሳታፊዎች ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች ዙሪያ በቂ ችሎታ ይኖራቸዋል፡-
-
በሕግ ማውጣቱ ሂደት የምክክርን አስፈላጊነት ያብራራሉ፡፡
- የእኩል ሥራ ስምሪትና የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግና ፖሊሲ በማርቀቅ ወቅት ለምክክር የታቀዱትን አራት ቀዳሚ ቡድኖች ለይተው ያውቃሉ፡፡
- ትክለኛ የምክክር ሕጋዊ ሂደትን ይገልጻሉ፡፡
- በሕግ ማውጣት ሂደታቸው ዒላማ ከሆኑ የተወሰኑ ባለ ድርሻዎች ጋር በመመካከር ረገድ ስላላቸው ልምድ ቢያንስ የሦስት አገሮችን ምሳሌዎች አጉልተው ያሳያሉ፡፡