ወጣት የምግብ ሥራ ተማሪዎች፡፡

ከ4 እስከ 7 ሰዓት (መማርን ለማጠናከር በተመረጡ አማራጭ መልመጃዎች በሚወስዱት የጊዜ መጠን ላይ በመመርኮዝ)

ይህ የመጨረሻ ክፍለ ትምህርት ሕግ በመረቀቅ ደረጃ ላይ እያለ ሕጎችና ፖሊሲዎች ተፈጻሚ የሚሆኑባቸውን መንገዶች ስለ ማቀድ አስፈላጊነት አጽንኦት ይሰጣል፡፡ ይህ ሕጎቹና ፖሊሲዎቹ በተግባር ምን እንደሚመስሉና መብቶች እንዴት እንደሚረጋገጡ መመልከትን ይጠይቃል፡፡ የውል ተገዢነትን እንደ መሳሰሉት ሌሎች አቀራረቦች ሁሉ ፍትሐዊ አሠራሮችን እንዲሁም አስተዳደራዊ አስፈጻሚ ተቅዋሞችን ለማጠናከር የሚወጡ ስትራቴጂዎችን ይመረመራሉ፡፡

የመማር ዓላማዎች

በኮርሱ ፍጻሜ ተሳታፊዎች ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች ዙሪያ በቂ ችሎታ ይኖራቸዋል፡-

  • የሕግ አፈጻጸምን አስፈላጊነት ያብራራሉ፡፡
  • ለሕጉ ተፈጻሚነት አቀራረቦችን ይለያሉ፡፡
  • አንድን ሕግ በተግባር የመተረጐም እንደምታዎችን ይገልጻሉ፡፡
  • በሕጉ ስር የግለሰብን መብቶች በማረጋገጥ ዙሪያ የፍትሕ እና/ወይም የአስተዳደራዊ ሥነ ሥርዓቶችን አስፈላጊነት ይዘረዝራሉ፡፡
  • የፍትሕ አሠራሮችን ለማጠናከር ምሳሌዎችን አጉልተው ያሳያሉ፡፡
  • አስተዳደራዊ አስፈጻሚ ተቅዋሞችን የሚደግፉትንና የሚቃወሙትን ያወያያሉ፡፡