አካል ጉዳተኛ አስተማሪ ከተማሪዎች ጋር፡

ከ6 እስከ 9 ሰዓት (መማርን ለማጠናከር የተመረጡ አማራጭ መልመጃዎች በሚወስዱት የጊዜ መጠንላይ በመመርኮዝ)

ይህ ክፍለ ትምህርት የመድልዎ አልባ ሕግን ጠቀሜታ በአጽንኦት የሚያሳይ ሲሆን የአካል ጉዳት ሕግ መያዝ ያለበትን አድማስ በአጭሩ ያትታል፡፡ በተጨማሪም ይህ ክፍለ ትምህርት ሊከሰቱ የሚችሉ የመድልዎ ዓይነቶችን አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን ለተመጣጣኝ ማመቻቸት አስፈላጊነት ጭብጥን ይመሠርታል፡፡

የመማር ዓላማዎች

በኮርሱ ፍጻሜ ተሳታፊዎች ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች ዙሪያ በቂ ችሎታ ይኖራቸዋል፡-

  • የአካል ጉዳት መድልዎ አልባነትን አስፈላጊነት ይዘረዝራሉ፡፡
  • የአካል ጉዳት ሕግ ሊይዘው የሚችለውን ስፋት ያውቃሉ፡፡
  • መድልዎ መያዝ የሚችላቸውን መልኮች ያስረዳሉ፡፡
  • ተመጣጣኝ ማመቻቸትን ያብራራሉ፡፡
  • የተመጣጣኝ ማመቻቸት ምሳሌዎችን ይሰጣሉ፡፡
  • ማስረጃ የማቅረብ ግዴታን ጽንሰ ሃሳቦችን ያብራራሉ፡፡