የመረጃ መረብ ምንጮች
ይህ የዓለም ሥራ ድርጅት ይፋ ድረ ገጽ (ዌብ ሳይት) ከዓሥድ ጋር የተያያዙ ተነሣሽነቶች፣ ኅትመቶችና ዓለም አቀፍ የዜና ርእሶች ክምችቶችና ማውጫዎችን ይሰጣል፡፡ በተለይ «ስለ እኛ– About Us » የተሰኘው ክፍል የግንቦት 1933ቱን የፊላዴልፊያ መግለጫን ጨምሮ ስለ ዓሥድ ታሪክ፣ አባልነት፣ እንዲሁም ስለ ድርጅቱ ዓላማዎችና የመተዳደሪያ ሕገ ደንብ የሚገልጹ የድረ ገጽ ትስስሮች (links) አሉት፡፡ ከዚህ ሌላ ድረ ገጹ የሠራተኛ ስታቲስቲኮች ገጾች፣ የዓለም አቀፍ የሥራ ጥናቶች ተቅዋም የድረ ገጽ ትስስር (ሊንክ) እና በሥራ ስምሪት ዙሪያ ሙሉ የሆነ ክፍል አለው፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል የሚከተሉትን እንመልከት፡-
http://www.hrweb.org/resource.html
ይህ ድረ ገጽ በዓለም ዙሪያ ባሉ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች የድረ ገጽ ትስስሮች (ሊንኮች) ላይ ያተኮረ ሙሉ ገጽ አለው፡፡ ይህ ድረ ገጽ በሰብአዊ መብቶች ድር የሚካሄድ ሲሆን ከተመድና ከመንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ገጾች ጋር ትስስር አለው፡፡ በተጨማሪም በዓለም አህጉሮች የተከፋፈሉ አካባቢያዊና ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶችና ምንጮች አሉ፡፡
http://www.dredf.org/international/lawindex.shtml
የአካል ጉዳት መብቶች ትምህርትና መከላከያ ድርጅት ድረ ገጽ ክፍል የሆነው ይህ ገጽ በዓለም ዙሪያ ካሉ አገሮች የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕጎች ማውጫ ነው፡፡ ገጹ በኢንተርኔት ላይ የሚነበቡ የሕግ ቅጂዎችን የሚይዝ ሲሆን ማውጫው እንደ ኮሎምቢያ፣ ፊጂ፣ ማዳጋስካርና ታይላንድ ያሉትን አገሮች ያካትታል፡፡
ይህ ድረ ገጽ በዓለም ባንክ የሚካሄድ ሲሆን በኢንተርኔት ላይ የሚገኙ ኅትመቶችና ሪፖርቶችን በሚመለከት ከጠቃሚ የመረጃ መረብ ትስስሮች (ሊንኮች) ጋር በአካል ጉዳት ዙሪያ ያተኩራል፡፡ ድረ ገጹ በክፍለ አህጉራት የተከፋፈሉ የአካል ጉዳት ጉዳዮች፣ እንዲሁም እንደ ሥርዓተ ፆታና ድህነት ባሉ ልዩ የአካል ጉዳት ርእሶች ዙሪያ ምንጮች አሉት፡፡ ከእነዚህ ኅትመቶች አንዳንዶቹ አካል ጉዳትን በሥራ ቦታ በመምራት ዙሪያ ርእሶችን ይሸፍናሉ፡፡
http://www.ilo.org/public/english/region/asro/bangkok/ability/index.htm
ይህ ድረ ገጽ በእስያና በፓሲፊክ አካባቢ ያሉትን ፕሮጀክት እንቅስቃሴዎችን፣ አሠሪዎችና ሠራተኞችን፣ መስፈርቶችና መብቶችን፣ ብሔራዊ ሕጎችና መረጃዎችን እንዲሁም ኅትመቶችን በማሳየት የዓለም ሥራ ድርጅት (ዓሥድ) የአካል ጉዳት ፕሮግራምን ይወክላል፡፡