ማጣቀሻዎችና ምንባቦች

  • IILO: Achieving Equal Employment Opportunities for Persons with Disabilities Through Legislation : Guidelines (2007) Geneva— ዓሥድ፣ በሕግ አማካይነት ለአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ማስከበር፤ መመሪያዎች (2007) ጄኔቫ (በአማርኛ ተተርጕሞ የታተመ)

    እነዚህ መመሪያዎች የአካል ጉዳትን እንደ ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ዳግመኛ ግምት ያንጸባርቃሉ፡፡ ለፖሊሲ አውጪዎችና ለሕግ አርቃቂዎች የታሰቡትና «የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት፤ የሕግ ተጽእኖ» የተባለው የዓሥድ ፕሮጀክት አንድ ክፍል የሆኑት መመሪያዎቹ የአካል ጉዳተኞችን ሥልጠናና የሥራ ስምሪት በሚመለከት የብሔራዊ ሕጎችን ውጤታማነት በማሻሻል ረገድ ለመርዳት እንዲዳብሩ ተደርገዋል፡፡ ይህ ፕሮጀክት በአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት ዙሪያ አንድም በሕጎች መልክ፣ ወይም ነባር ሕጎችን በማሻሻል፣ ወይም ደግሞ ሕጎችን ለመተግበር ደንቦችና ፖሊሲዎች በማውጣት አማካይነት ውጤታማ ሕግ እንዲተገብሩ የተመረጡ አገሮች መንግሥታትን አቅም ለማሳደግ ያቅዳል፡፡ ደግሞም ፕሮጀክቱ ለተመረጡ ብሔራዊ መንግሥታት በሕጎቻቸው ውስጥ አስፈላጊ ማሻሻያዎችን በመተግበር ረገድ የቴከኒክ እርዳታ ይሰጣል፡፡ ይህን የቴክኒክ አማካሪነት ሚና ለመርዳት እነዚህ የማርቀቂያ መመሪያዎች ዋጋ ያላቸው መሣሪያዎች ናቸው፡፡

    መመሪያዎቹ በእንግሊዝኛ በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ፡-
    http://www.ilo.org/global/publications/ilo-bookstore/order-online/books/
    WCMS_091340/lang--en/index.htm

  • Gubbels, A.; Kemppainen, E. (2002). A review of legislation relevant to accessibility in Europe. Europe Accessibility Group.

    ሪፖርቱ በአንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ከኢንተርኔት ተደራሽነት አኳያ አውሮፓዊና ብሔራዊ ሕግን አስመልክቶ የተደረገ ውይይትን ያካትታል፡፡

    ሪፖርቱ በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-
    http://www.inst-informatica.pt/servicos/informacao-e-documentacao/biblioteca-digital/sociedade-da-informacao-1/2005-e-anos-anteriores/eacc_rev_leg.pdf/view

  • Herr, Stanley, S.; Gostin, Lawrence, O.; Koh, Harold, Hongju, (eds); The Human Rights of Persons with Intellectual Disabilities; Oxford University Press; New York and Oxford.

    የአእምሮ ጉዳቶች ያሉባቸው ሰዎች መብቶች ለረጅም ጊዜ በሰብአዊ መብቶች መስክ ችላ ተብለው ቆይተዋል፡፡ ይህ የአእምሮ ጉዳቶች ባሉባቸው ሰዎች ዙሪያ የተበረከቱ ጽሁፎች ስብስብ መታሰቢያነቱ በዚህ መስክ እውቅ ተሟጋች ለነበሩት ስታንሊ ኤስ. ሄር የተሰጠ ነው፡፡ መጽሐፉ በዩናይትድ ስቴትስ በዬል የሕግ ትምህርት ቤት በመጋቢት 1995 የአእምሮ እድገት መዘግየት ባለባቸው ሰዎች ዙሪያ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ዐውደ ጥናት (ሲምፖዚየም) በተረቀቀውና በተፈረመው «የዬል መግለጫ» ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህ አእምሮአዊ ጉዳቶች ላሉባቸው ሰዎች በመብት ላይ የተመሠረተ አቀራረብን በማሳደግ ረገድ ለመሥራት ተጨባጭ መሠረት የሚሰጥ በጣም ትልቅ የሆነ ጥራዝ ነው፡፡

  • Lunt, N.; Thornton, P. (1994). Disability and employment: Towards an understanding of discourse and policy. Disability & Society, 9(2), 223-238.

    ይህ ጽሁፍ ከአሥራ አምስት አገሮች ማስረጃ በመውሰድ የአካል ጉዳት የሥራ ስምሪት ፖሊሲን ባህርይ ይዳስሳል፡፡ ከቀደሙት የኅብረተሰባዊ ጥናት አቀራረቦች ጋር በሚስማማ መልኩ በጉዳዩ መስክ ፖሊሲ የሚቀረጽባቸውን ሁለት መንገዶች ይገልጻል፡፡ ሁለቱ ተምሳሊቶች በርእሶቹ ስር የሥራ ስምሪት ፖሊሲን፤ የሕግ እርምጃዎችን፣ ገላጣ የሥራ ስምሪት-በገንዘብ የሚደገፍ የሥራ ስምሪት የድጋፍ አገልግሎቶች እና ባለ መጠለያ/የሚደገፍ አሰጣጥን በወሳኝ መልኩ ለመገምገም የተቀረጹና የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ በፖሊሲ ትግበራ ወቅት ሊነሡ የሚችሉ አጣብቂኞችና ችግር አቅላይ የሥራ ስምሪት ፖሊሲ በመገንባት የሚገኙት ውጤቶች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በመጨረሻም ጽሁፉ አንድ ግልጽ የአካል ጉዳት ፖሊሲ ሊኖሩት የሚገቡትን ርእሶች ወይም መለኪያዎች ሃሳብ ያቀርባል፡፡

    ሪፖርቱ በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-
    http://taylorandfrancis.metapress.com/(3dkun1z5cbtwvg45jmeuwxri)/app/home/contribution.asp?
    referrer=parent&backto=issue,6,16;journal,73,100;linkingpublicationresults,1:100641,1

  • Mabbett, Deborah. (2005) "The Development of Rights-based Social Policy in the European Union: The Example of Disability Rights". JCMS
    Vol. 43 No. 1. 97-120.

    ይህ እትም አካል ጉዳትን በተለየ መንገድ በመጥቀስ በአውሮፓ ኀብረት የመድልዎ አልባ መብቶች መፈጠርን ይመረምራል፡፡ መድልዎን ለመዋጋት የማኅበረሰብ ተቅዋሞችን ብቃት ያራዘመውን የአንቀጽ 13 TEC መነሻዎችን የሚዘረዝር ሲሆን በአካል ጉዳት መስከ የሌሎች ተነሣሽነቶችን ታሪክ ይቃኛል፡፡
  • አርተር ኦሬሊ፣ በመጀመሪያ በጥናታዊ ጽሁፍነት The Right to Decent Work of Persons with Disabilities በሚል ርእስ በ2003፣ በተሻሻለ መልክ በ2007 በዓለም ሥራ ድርጅት በጄኔቫ የታተመ፣ በዚሁ ዓመት አካል ጉዳተኞች ምቹ ሥራ ለማግኘት ያላቸው መብት በሚል ርእስ በአማርኛ ተተረጕሞ የታተመ

    የተባበሩት መንግሥታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ድንጋጌ በሚዘጋጅበት ጊዜ ይካሄዱ ለነበሩት ውይይቶች የድርሻውን ለማበርከት ዓሥድ ይህ ጽሁፍ እንዲዘጋጅ ፈቅዶአል፡፡ ጽሁፉ በድንጋጌው ውስጥ በተለይ የሥራ ስምሪትና ሥራን የሚመለከቱትን ደንቦች አርቃቂዎች ለመርዳት የታሰበ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍ በጊዜ ሂደት የአካል ጉዳተኞችን የመሥራት መብትና እስከዚያ ጊዜ ድረስ በዓለም አቀፍ ሰነዶችና በብሔራዊ ሕግ ጉዳዩ ይታይ የተነበረበትን መንገድ መርምሮአል፡፡ ይህ ጽሁፍ የተሻሻለው የ2007 እትም ነው፡፡

    ጽሁፉ በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-
    http://www.ilo.org/public/english/employment/skills/disability/download/right.pdf

  • Parker, Sarah. (2006). International justice: The United Nations, Human Rights and Disability. Journal of Comparative Social Welfare, 22(1), 63-78.

    ይህ እትም በአካል ጉዳት መነጽር አማካይነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች አሠራርን ይዳስሳል፡፡ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ የሚያነሣሱትን ሦስት ቁልፍ መስኮች ማለትም መድልዎ አልባነትን፣ ማኅበራዊ ዋስትናና የሥራ ስምሪትን በመጥቀስ ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ መብቶች ቃል ኪዳን እና ዕድሎችን ለአካል ጉዳተኞች እኩል የማድረግ መደበኛ ደንቦች የተባሉት ሁለት የሰብአዊ መብቶች ሰነዶች ዙሪያ ትንተና ተካሂዶአል፡፡

    እትሙ በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-
    http://taylorandfrancis.metapress.com/(tj3ukh55lh2xgm55vcnwle55)/app/home/contribution.asp?
    referrer=parent&backto=issue,6,8;journal,1,1;linkingpublicationresults,1:119819,1

  • Quinn, G; Degener, Theresia; Bruce, Anna; Human Rights and Disability: The current use and future potential of United Nations human rights instruments in the context of disability; Office of the High Commissioner for Human Rights; United Nations; New York; 2002.