ውጤትን መገምገም
ይህን ክፍለ ጊዜ ከመዝጋትዎ በፊት ተሳታፊዎች በአባሪ «ሀ» የቀረበውን የሥልጠና ፕሮግራም ቅኝት እና በአባሪ «ለ» ያለውን የክፍለ ትምህርት 2 የመማር ዓላማዎች ግምገማ ጊዜ ወስደው እንዲያጠናቅቁ ይጠይቁአቸው፡፡ ሲያጠናቅቁም ለእርስዎ እንዲመልሱ ይጠይቁአቸው፡፡ አጠቃላይ የአስተማሪ ውጤታማነትና የተደረሰባቸውን ልዩ የማስተማር ዓላማዎች መጠን ለመለካት መልሶቻቸውን በየክፍሉ ይመድቡአቸው፡፡ መማርን ለማሳደግ ገለጻውና የመማር ልምዱ የትኛው ቦታ ላይ መበልጸግ ይችል እንደ ነበር በተለይ ማስታወሻ ይያዙ፡፡