የሥልጠና ዝርዝር
3.4 መደበኛ ገለጻ - ተመጣጣኝ ማመቻቸት
ሕይወታቸውን ወይም ሥራቸውን ቀላል ያደረጉላቸውን መሣሪያዎች፣ ድጋፎች፣ ወይም ሰዎች በመጥቀስ ልምዶቻቸውን እንዲያካፍሉ ተሳታፊዎችን በመጠየቅ ይህን ንኡስ ክፍል ይጀምሩ፡፡ መልሶቻቸውን በተገላጭ ወረቀቱ ላይ ይጻፉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ አካል ጉዳት በተለመደው ወይም መደበኛ በሆነው መንገድ ሥራን ለማከናወን የግለሰብን ችሎታ ይነካል፡፡ ተመጣጣኝ ወይም ውጤታማ ማመቻቸትን የማድረግ ግዴታ፣ ወይም ማመቻቸትን የማግኘት መብት፣ በዘመናዊው የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ አዘውትሮ የሚገኝ ነው፡፡ የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ አሠሪዎችና ሌሎች ሰዎች የአንድን ግለሰብ አካል ጉዳት ግምት ውስጥ እንዲያስገቡና የአንድን አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ ወይም የሥራ አመልካች ፍላጎቶች ለማስተናገድ፣ እንዲሁም በተፈጥሮአዊውና ማኅበራዊ አካባቢ የተጋረጡትን መሰናክሎች ለማስወገድ ጥረቶች እንዲያደርጉ በይበልጥ ይጠይቃል፡፡ ይህ ግዴታ ተመጣጣኝ ማመቻቸት የማድረግ መለኪያ በመባል ይታወቃል፤ በሌላም በኩል ተመጣጣኝ ማስተካከያ ወይም ውጤታማ ማመቻቸት/ማስተካከያ ተብሎ ይጠቀሳል፡፡ በሥራ ገበያው መሰናክሎች ለሚያጋጥሙአቸው ሠራተኞች ወይም የሥራ አመልካቾች ተመጣጣኝ ማመቻቸት ለማቅረብ አለመቻል መጥፎ የሥራ ስምሪት አሠራር ብቻ ሳይሆን ተቀባይነት እንደሌለው የሥራ ስምሪት መድልዎ ዓይነት በበለጠ እየታየ ነው፡፡ የተሳሳተ አተረጓጐም እንዲወገድና አሠሪዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲገነዘቡ ሕጉ በተመጣጣኝ ማመቻቸት ምን ማመልከት እንደ ተፈለገ በግልጽ ማብራራት ይኖርበታል፡፡
በመጥቀስ ቡድኖቹ ቀጣዮቹን ጥያቄዎች ለመመለስ፣ ለመወያየትና ለተቀረው ቡድን ለማቅረብ እንዲዘጋጁ ይጠይቁ፡፡ ለቡድን ሥራ 30 ደቂቃ ለተለቀው በቡድን ገለጻ ለማቅረብ ደግሞ 30 ደቂቃ ይፍቀዱ፡፡
«እርስዎ በሚሠሩበት ወይም በሌላ ቦታ ማመቻቸቶቹ በውጤታማ ሁኔታ የተተገበሩበት ጊዜው መቼ እንደ ነበር ይግለጹ»፡፡
- «ተመጣጣኝ ማመቻቸቶቹ» ምን ነበሩ?
- መቼ ነበር የተተገበሩት?
- በሂደቱ ማን ተካተተ?
- አካል ጉዳት ለሌለባቸው ሠራተኞች የተደረጉት ማመቻቸቶች ምን ይመስላሉ - ምን ሊሆኑ ይችላሉ፣ የተሰጡትስ በእርስዎ የሥራ ቦታ ነው?
- በውጤታማ ሁኔታ ያልተተገበሩበት ወቅት ምን ይመስላል. . . ምን ቢደረግ በተሻለ ነበር?
- የገለጻ ማሳያ 52 ተጠቅመው ተመጣጣኝ ማመቻቸት የሠለጠነ አካል ጉዳተኛ ለአንድ የሥራ መደብ እንዲያመለክት፣ የሥራ መደቡን መሠረታዊ እንቅስቃሴ እንዲያከናውን፣ ወይም የሥራ ስምሪት ጥቅም እንዲያገኝ የሚያስችል የሥራ መደብ፣ የሥራ ስምሪት አሠራር፣ ወይም የሥራ አካባቢ ለውጥ ወይም ማስማማት ነው ተብሎ እንደሚብራራ የያስረዱ፡፡ ተሳታፊዎች ለመጀመሪያው ጥያቄ ከሰጡአቸው መልሶች ጋር ሊነፃፀሩ የሚችሉ አንዳንድ ምሳሌዎችን ለማሳየት የገለጻ ማሳያ 53ን ይጠቀሙ፡፡ ተመጣጣኝ ማመቻቸት የተስተካከለ የቢሮ ወንበርን (የጀርባ እክል ላለባቸው ሰዎች)፣ የሥራ ሰዓቶችን ማስማማትን (የተዘወተሩ የእረፍት ጊዜዎች ለሚያስፈልጉአቸው ህክምና ነክ ችግሮች ላሉባቸው ሰዎች)፣ እንዲሁም ብሬል አንባቢ የኮምፒውተር ኪቦርድን (ለዓይነ ስውራን ሰዎች) እና የሥራ መደብ አሠልጣኝን (ሥነ አእምሮአዊ ወይም የአእምሮ ጤና ጉዳት ላለባቸው ሰዎች) ሊያካትት ይችላል፡፡
- የገለጻ ማሳያ 54ን ተጠቅመው በአሜሪካውያን አካል ጉዳተኞች ሕግ በታቀፈው መሠረት ተመጣጣኝ ማመቻቸት የማድረግ ግዴታን ያሳዩ፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተመጣጣኝ ማመቻቸት አንድን አካል ጉዳተኛ እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ለመጠቀም የሚያስችል በሥራ አካባቢ ወይም የሥራ መደብ በሚከናወንበት መንገድ ላይ የሚደረግ ለውጥን እንደሚያመለክት ይታወቃል፡፡ ሦስት «የተመጣጣኝ ማመቻቸት» ፈርጆች አሉ፣ እነርሱም፡- በሥራ መደብ/የቃል ፈተና ላይ የሚደረጉ ለውጦች፤ በሥራ አካባቢ ወይም ሥራው በትከክል በሚካሄድበት መንገድ ላይ የሚደረጉ ለውጦች፣ እንዲሁም ሥልጠና እንደ ማግኘት ያሉ አንድ አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ እኩል የሥራ ስምሪት ጥቅሞችና አጋጣሚዎች እንዲያገኝ የሚያስችሉ ለውጦች ናቸው፡፡
እንደ አውስትራልያ፣ ኒውዚላንድና ደቡብ አፍሪካ ባሉ ሌሎች አገሮች ተመጣጣኝ ማመቻቸትን መስጠት አለመቻል አንድ የመድልዎ ዓይነት እንደሚፈጥር አጥብቀው የሚያሳስቡ የሕግ አንቀጾች እንዳሉአቸው ያስረዱ፡፡ የአውስትራልያው ሕግ «አንድን አካል ጉዳተኛ እንዳይጠቀም የሚያደርጉ ያልተመጣጠኑ መስፈርቶች መወገድ»፣ በኒውዚላንድ «አካል ጉዳትን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ለሠራተኞች ሁሉ ‹ተመጣጣኝ እርምጃዎችን› መውሰድ ሁልጊዜ የአሠሪው ግዴታ» በመሆኑ፣ በደቡብ አፍሪካ ደግሞ «በአንድ የተለየ አሠሪ የሚተገበሩ የአዎንታዊ ተግባር እርምጃዎች . . . ከተለዩ ወገኖች የተውጣጡ ሰዎች በእኩል ዕድሎች እንደሚጠቀሙና በተለየ አሠሪ የሥራ ኃይል ውስጥ በትክክል እንደ ተወከሉ ለማረጋገጥ ተመጣጣኝ ማመቻቸት ማድረግን» የሚያካትቱ በመሆናቸው በጥቂቱ ከዩናይትድ ስቴትስ ሕግ ይለያሉ፡፡
-
የተመጣጣኝ ማመቻቸት አሰጣጥ በዓይነቱ ጊዜያዊ መሆን የማይፈልግ የተለያየ እርምጃ እንደ ሆነ አጽንኦት ይስጡ - እርግጥ ነው ይህ በግለሰቡ የሥራ ስምሪት ቆይታ ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ የገለጻ ማሳያ 55ን ተጠቅመው ተመጣጣኝ ማመቻቸት አዎንታዊ እርምጃ እንዳልሆነ ያስረዱ፡፡ አዎንታዊ እርምጃ ተለቅ ላለ ወገን ወይም ሕዝብ የታቀደ ተስማሚ ወይም ተመራጭ አያያዝ ነው፡፡
የአዎንታዊ እርምጃ ምሳሌ ለመስጠት ያህል አንድ ኩባኒያ በውስጡ ያለው የሥራ ኃይል በአብላጫው በነጭ ወንዶች የተያዘ መሆኑን በመገንዘብ ሴቶችና የዘር አናሳዎችን በንቃት ለመመልመል ሲወስን አዲሶቹ ሠራተኞች ውክልና ከሌላቸው ወገኖች እንዲሆኑ የተወሰነ መቶኛ ግብ ያስቀምጣል፡፡ በተለዋጭ የሚሠሩበት ኩባኒያ ለእድገቶችና ለአመራር ቦታዎች በደፈናው ወንዶችን ይመርጣል የሚል ቅሬታ ባለው የሴቶች ቡድን በአዎንታዊ እርምጃ ሕጎች ስር አቤቱታ ይቀርባል፡፡ ስለ ጠቅላላው የሠራተኞች ቡድን የቀረበው ይህን የመሰለው አቤቱታ ወይም ክስ የመደብ እርምጃ ክስ በመባል ይታወቃል፡፡
-
ተመጣጣኝ ማመቻቸት ግለሰቡ የሥራ መደቡን ወይም መደቧን ለማከናወን በሚኖሩት የድጋፍ ፍላጎቶች ላይ የተመረኮዘ የተለያየ ወይም የተስተካከለ ሂደት እንደ ሆነ ያስረዱ፡፡ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን ለመቅጠር በአዎንታዊ እርምጃ በሚሰማራው ከላይ በተጠቀሰው የኩባኒያ ምሳሌ ከሰዎቹ አንዱ ወይም የሚበዙት የሥራ መደቡን ወይም መደቧን ግዴታዎች ለማከናወን ተመጣጣኝ ማመቻቸት ሊፈልጉ እንደሚችሉ ያስረዱ፡፡ ለምሳሌ የኩባኒያው ደንቦች በሕንፃቸው የእንሰሶችን መታየት ይከለክሉ ይሆናል፡፡ ይሁንና ከአዲሶቹ ሠራተኞች አንዱ ረዳት ውሻ የሚጠቀም ከሆነና ጓደኛ ውሻው መግባት እንዲችል ክልከላው እንዲታገድ የሚጠይቅ ከሆነ ኩባኒያው ተመጣጣኝ ማመቻቸት ማድረግ ያስፈልገዋል፡፡ ተመጣጣኝ ማመቻቸት የመስጠት ግዴታ ለጠቅላላ ተደራሽነት፣ ሙያዊ ጤናና ደህንነት መስፈርቶች ከሚኖረው የተገዢነት ግዴታ ጋር መምታታት አይኖርበትም፡፡
- ተመጣጣኝ ማመቻቸትን የሚጠይቅ አንድ አካል ጉዳተኛ የሥራ አመልካች ወይም ሠራተኛ ሦስት ነገሮችን ማሳየት ያስፈልገዋል፡- 1. ግለሰቡ/ግለሰቧ ለሥራ መደቡ የሠለጠኑ መሆናቸውን (በተለየ ሁኔታ)፤ 2. አሠሪው (ወይም ሌላ ወገን) የግለሰቦቹን ፍላጎቶች እንደሚገነዘብና፤ 3. በአንድ የተወሰነ ማመቻቸት (ደህንነት) ግለሰቦቹ
የዚያን የተለየ የሥራ መደብ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች ማከናወን እንደሚችሉ የገለጻ ማሳያ 56ን , ተጠቅመው ያስረዱ፡፡ -
Follow-up using የገለጻ ማሳያ 57ን ተጠቅመው አንድ አሠሪ በእነርሱ ስር ተመጣጣኝ ማመቻቸትን ከመስጠት ነፃ መሆን የሚችልባቸውን ሦስት ሁኔታዎች ለመግለጽ ክትትል ያድርጉ፡፡ ይህ እርሱ/እርሷ የግለሰቡን የማመቻቸት ፍላጎቶች አለማወቃቸውን ያካትታል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሠራተኛ በድብርት ይሰቃያል ግን ለአሠሪው መንገር ያቅተዋል፣ ከዚያም ለተወሰኑ ወራት የሆስፒታል ቆይታ ያደረገ ሲሆን ባልነበረበት ወቅት የሥራ መደቡን እንደ ያዘ በማቆየት ማመቻቸት እንዲደረግለት አሠሪውን ይጠይቃል፤ ወይም አንድን አካል ጉዳተኛ የሥራ አመልካች ወይም ሠራተኛ የሥራ መደቡን መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች ለማከናወን የሚያስችል ውጤታማ ማመቻቸት በቦታው የለም፡፡ ሌላ ምሳሌ ሲታይ፣ ቀዳሚ ሥራው ካድ የተባለውን ሶፍትዌር በመጠቀም በኮምፒውተር የታገዘ ድዛይን መሥራት የሆነ አንድ መሀንዲስ ከስኳር በሽታ የተነሣ የማየት ችሎታውን ያጣል፡፡ ማመቻቸት እንዲያደርግለት አሠሪውን ይጠይቃል ነገር ግን ሠራተኛው የሥራ መደቡን ቀዳሚ ተግባሮች ማከናውን ስለማይችልና ኩባኒያው የሚያካሂደው ብቸኛ ሥራ ያ በመሆኑ፣ ወይም የተጠየቀው ማመቻቸት በአሠሪው ላይ «ያልተመጣጠነ ሸክም» ስለሚጭን፣ አሠሪው ጥያቄውን አልተቀበለም (የገለጻ ማሳያ 58ን)፡፡ በዚህ የመጨረሻ ሁኔታ አንድ ሠራተኛ በአደጋ ምክንያት የዊልቼር ተጠቃሚ ቢሆንና አሠሪው የመወጣጫ ሊፍት በሌለው ሕንፃ ውስጥ የሚገኝ ቢሆን ይህ አንድ ምሳሌ ይሆናል፡፡ አሠሪው ወደ ሌላ ሕንፃ እንዲዛወር ወይም ሊፍት እንዲያስገጥም መጠበቅ ያልተመጣጠነ ሸክምን ሊያሳይ ይችላል፡፡
የአንድን አካል ጉዳተኛ ፍላጎቶች ላለማመቻቸት የሚቀርብ ‹መከላከያ› ወይም ‹ማረጋገጫ› በጥንቃቄ ሊነደፍ እንደሚያስፈልግ ያስረዱ፡፡ አለበለዚያ ይሉኝታ ቢስ አሠሪዎች ማንኛውንም ግዴታ ለማስወገድ እንደ ማምለጫ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ በአሠራር ሁኔታ ያልተመጣጠነ ሸክምን ምን ይፈጥረዋል የሚለው ጥያቄ በሚመለከተው ጉዳይ ጭብጥ ላይ የሚመረኮዝ ሲሆን በአንድ ማመቻቸት የገንዘብ ወጪዎች ወይም በገንዘብ ማካካሻ ዘዴዎች ላይ ብቻ የሚመረኮዝ አይደለም፡፡ ይልቁን ገንዘብ ነክ እንደምታዎቹን፣ አጠቃላይ የሥራ ሂደት ውጤቶቹን፣ አስቀድመው በተቀጠሩት አካል ጉዳተኛ ሠራተኞቹ ብዛትና በታሰበው የሥራ ስምሪት ውል ርዝመት በመሳሰሉት ጭብጦች ላይ ይመረኮዛል፡፡