የሥልጠና ዝርዝር

3.3 መደበኛ ገለጻ - የተለያዩ የመድልዎ ዓይነቶች

  • መድልዎን መከልከል በሠራተኞችና በሥራ አመልካቾች መካከል የሚደረጉትን ለይቶ የማወቂያ ዓይቶችን ሁሉ ሕገ ወጥ እንደማያደርጋቸው ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሙያዎችና ብቃቶች ያሉ እንደ መሆናቸው መጠን አመልካቾችና ሠራተኞች እነዚያን ሙያዎች እንደ ያዙ ለመጠየቅ አሠሪዎች መብት አላቸው፡፡ እነዚህ አዘውትረው በሥራው ባህርይ ወይም ሥራው በሚካሄድባቸው ጭብጦች የሚታዩ ናቸው፡፡ የታክሲ ኩባኒያውን ምሳሌ ለማስዳት የገለጻ ማሳያ 45ን ይጠቀሙ፡፡ ለመጀመሪያው ጥያቄ የሚሰጡት መልሶች ዓይነ ስውሮችን፣ የማንቀጥቀጥ ችግሮች ያሉባቸውን ሰዎች ወይም በሌሎች የህክምና ሁኔታዎች ምክንያት መንጃ ፈቃዳቸውን የተነጠቁ ግለሰቦችን ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡ የተረጋገጡ ሙያዊ መስፈርቶች ያሉአቸውን ሌሎች ሙያዎች ለይተው እንዲያመለክቱ ተሳታፊዎችን ይጠይቁ፡፡

    ምሳሌ፡- የመንጃ ፈቃድ ያላቸውን የሥራ አመልካቾች የሚፈልግ አንድ የታክሲ ኩባኒያ ዓይነ ስውሮችን እንዲሁም በህክምና ምክያንት የመንጃ ፈቃድ የማይኖራቸውን ሰዎች ያገልላል፡፡ በታክሲ ኩባኒያው በኩል የቀረበው እንዲህ የመሰለው የመንጃ ፈቃድ መስፈርት ሕጋዊና ተመጣጣኝ ነው ስለዚህም ሀቀኛ ወይም ሊረጋገጥ የሚችል ሙያዊ መስፈርትን ያስከብራል፡፡

  • «አድላዊ ድርጊት መቼ ይከሰታል?» የሚል ጥያቄ ለተሳታፊዎች ያቅርቡ፡፡ እክሉ በሥራው ክንውን ላይ ምንም ተጽእኖ የሌለው፣ ቢኖረውም እምብዛም ሆኖ ሳለ አንድ አሠሪ እክል አለበት በሚል ጭብጥ ላይ በመመሥረት አንድን የሥራ አመልካች ወይም ሠራተኛ በጎጂ መልኩ በሚይዝበት ጊዜ አድላዊ ድርጊት እንደሚከሰት ለተሳታፊዎች በአጽንኦት ይግለጹ፡፡ የተለያዩ የመድልዎ ዓይነቶችን - የተዘረዘሩትን አጉልቶ በማሳየት - መልሰው እንደሚመለከቱ ለተሳታፊዎች በማስረዳት ወደ የገለጻ ማሳያ 46 ይሸጋገሩ፡፡ ይህም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ መድልዎን፣ እንግልትን፣ ትእዛዝና ማነሣሳትን ያካትታል፡፡
  • የገለጻ ማሳያ 47ን, ተጠቅመው ተጨባጭ ማረጋገጫ ሳኖይር እንደ ዘር ወይም ፆታ ባለ በመድልዎ አልባ ሕግ ጥበቃ ከሚደረግለት የታወቀ መለያ ካለው በተመሳሳይ ቦታ ከሚገኝ ሰው ይልቅ ሌላው ሰው ባነሰ ሁኔታ በሚስተናገድበት ጊዜ ቀጥተኛ መድልዎ እንደሚከሰት ያስረዱ፡፡

    ምሳሌ፡- አንድ አሠሪ የሥራ ማስታወቂያ ሲያወጣ የመንጃ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ብቻ ማመልከት እንደሚኖርባቸው ይገልጻል፡፡ ይህ መስፈርት አካል ጉዳተኞችን በግልጽ አያገልልም፡፡ ይሁንና አንዳንድ የአካል ጉዳት ዓይነቶች ያሉባቸው ሰዎች የመንጃ ፈቃድ ማግኘት ስለማይችሉ ለሥራ መደቡ ለማመልከት አይችሉም፡፡ መስፈርቱ ሠራተኛው አንዳንድ ጊዜ ብቻ መኪና እንዲነዳ ስለሚጠይቅና የተሽከርካሪ ጉዞ በሚያስፈልግባቸው ጥቂት ወቅቶች ታክሲዎችን መከራየት ወይም በሕዝብ መጓጓዣ መጠቀም የሚቻል በመሆኑ መንጃ ፈቃድ የመያዝ መስፈርቱ ለሥራ መደቡ የማያስፈልግ ከሆነ ይህ ቀጥተኛ ወዳልሆነ መድልዎ ያዘነብላል፡፡

  • የከሌሎች ጋር ሲነፃፀር በመድልዎ አልባነት ሕግ ጥበቃ የሚደረግለት ወገን ጥቃት ሲደርስበት በግልጽ ገለልተኛ የሆነ የመለያ መስፈርት ጥቅም ላይ ውሎ ተጨባጭ ማረጋገጫ መኖሩን ማሳየት ሳይችል ሲቀር ቀጥተኛ ያልሆነ መድልዎ እንደሚከሰት የገለጻ ማሳያ 48ን በመጠቀም ያስረዱ፡፡ በጽሁፉ የቀረበውን ከምሳሌ ጋር ያብራሩ፡፡

    ምሳሌ፡- አንድ አሠሪ የሥራ ማስታወቂያ ሲያወጣ «የመንጃ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ብቻ ማመልከት ይኖርባቸዋል» በማለት በማስታወቂያው ይገልጻል፡፡ ማስታወቂያው ላይ ላዩን አካል ጉዳተኞችን በግልጽ የማያገልል ሆኖ ሳለ የተረጋገጠ ሙያዊ መመዘኛ ባይሆንም የመንጃ ፈቃድ የሌላቸውን ከማመልከት የሚያግድ በመሆኑ ቀጥተኛ ያልሆነ መድልዎ ያደርጋል፡፡

  • የአንድን ግለሰብ ክብር ለማጉደፍ እና/ወይም ለማስፈራራት፣ ጥላቻ፣ አዋራጅ፣ ዝቅ የሚያደርግ ወይም አስከፊ ሁኔታ ለመፍጠር ዓላማ ወይም ውጤት ጥበቃ ከሚደረግለት ጭብጥ ጋር ተያያዥ የሆነ አላስፈላጊ ድርጊት በሚፈጸምበት ጊዜ እንግልት (ማንገላታት) እንደሚከሰት የገለጻ ማሳያ 49ን በመጠቀም ያስረዱ፡፡

    ምሳሌ፡- እጆቹንና እግሮቹን መጠቀም የተሳነው ግለሰብ የሥራ ባልደረባ የሆነ ግለሰብ አካል ጉዳተኛውን በማዋረድና ዝቅ በማድረግ ስለ «ዊልቼር ተጠቃሚዎች» ይቀልዳል፡፡

  • የገለጻ ማሳያ 50ን በመጠቀም አንድ ሰው ወይም ተቅዋም በመድልዎ አልባነት ሕግ ጥበቃ ከሚደረግለት የታወቀ መለያ ካለው በተመሳሳይ ቦታ ከሚገኝ ሰው ይልቅ ሌላውን ሰው ባነሰ ሁኔታ እንዲያስተናግዱ ሌሎችን በሚጠይቅበት ወይም በሚያበረታታበት ጊዜ መድልዎን ለመፈጸም የሚደረግ ትእዛዝ ወይም ማነሣሳት እንደሚከሰት ያስረዱ፡፡

    ምሳሌ፡- አንድ ሠራተኛ ወራዳና አስጸያፊ በሆኑ ቀልዶች ወይም ማታለሎች አማካይነት በአካል ጉዳተኛ የሥራ ባልደረባው ላይ በሥራ ቦታው ሌሎችን ለጥላቻ ወይም ለዐመፅ ያበረታታል ወይም ያነሣሳል፡፡

  •  
    አማራጭ መልመጃ፡-

    የዚህ መልመጃ ዓላማ ተሳታፊዎች የመድልዎ ዓይነቶችን ለይተው እንዲያሳዩ ዕድሉን መስጠት ነው፡፡ በአባሪ «ሐ» «የተግባራዊ መማር» በተባለው ክፍል የተሰጡትን ጉዳየ ጥናቶች ያከፋፍሉ፡፡ ተሳታፊዎችን ከ3 እስከ 5 ሰዎች በሚይዙ ቡድኖች ይከፋፍሉአቸው፡፡  በየቡድኑ መሥራትና በእያንዳንዱ ጉዳየ ጥናቶች የሚከሰተውን የመድልዎ ዓይነት በሚመለከት ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ያስረዱአቸው፡፡ እያንዳንዱ ቡድን ግኝቶቹን ለማሳወቅና ለመረጠው ዓይነት መንሥኤውን ለመወያየት ዝግጁ መሆን ይኖርበታል፡፡ መልመጃውን ለመሥራት 30 ደቂቃ ለጠቅላላ ተሳታፊዎች መግለጫ ለመስጠት ደግሞ 30 ደቂቃ ይስጡአቸው፡፡ መልሶቹም እንደሚከተለው ይሆናሉ፡-
    ጉዳየ ጥናት 1፡- እንግልት
    ጉዳየ ጥናት 2፡- ቀጥተኛ ያልሆነ መድልዎ
    ጉዳየ ጥናት 3፡- ቀጥተኛ መድልዎ
    ጉዳየ ጥናት 4- ትእዛዝና ማነሣሳት

  • በአካል ጉዳት ጭብጦች ላይ ተመሥርቶ የሚፈጸም መድልዎን የሚከለክሉ ሕጎች አራቱንም የመድልዎ ዓይነቶች (ማለትም እንግልት፣ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ መድልዎ፣ እንዲሁም ትእዛዝና ማነሣሳት) መሸፈን እንደሚኖርባቸውና የሀቀኛ ሙያዊ መስፈርቶች ከዚህ ውጭ መሆን በጥንቃቄ መገለጽና በጥብቅ ሥራ ላይ መዋል እንዳለባቸው አጽንኦት በመስጠት ይህን ንኡስ ክፍል ይደምድሙ፡፡