የመረጃ መረብ ምንጮች

«ዓለም አቀፍ የሕግ መዐቀፎች ለአካል ጉዳት ሕግ አጠቃላይ እይታ» በተባለው በዚህ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድረ ገጽ ላይ የሚገኝ ጽሁፍ የአካል ጉዳት ሕግ፣ ዓለም አቀፍ የሕግ መዐቀፍ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች፣ መስፈርቶችና ደንቦች በአገር ውስጥ ሕግ ጥቅም ላይ የመዋልን ሚና በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ይዞአል፡፡  ለምሳሌ ዓለም አቀፍ የሕግ መዐቀፍ በተባለው ክፍል ውስጥ የዘር መድልዎን ወይም ከአገር ወደ አገር የሚዘዋወሩ ሠራተኞች መብቶች ጥበቃን በሚመለከት ከድንጋጌ ሥነ ሥርዓቶች ጋር ድረ ገጻዊ ትስስሮች (ሊንኮች) አሉት፡፡ በተጨማሪም ከ«አካል ጉዳተኞች መብቶች መግለጫ» እና «አካል ጉዳተኞችን በሚመለከት የዓለም የድርጊት ፕሮግራም» ጋር ድረ ገጻዊ ትስስሮች (ሊንኮች) አሉት፡፡

በተመረጡ ብሔራዊ የአካል ጉዳት ሕጎች ውስጥ የተመጣጣኝ ማመቻቸት ጽንሰ ሃሳብ፡፡ ይህ ጽሁፍ እንደ ስብሰባ መነሻ ሰነድ በተመድ የኤኮኖሚና ማኅበራዊ ጉዳዮች መምሪያ የተዘጋጀ ሲሆን ብሔራዊ ሕግ «የተመጣኝ ማመቻቸት» ጽንሰ ሃሳብ ከአካል ጉዳተኞች ጋር እንዴት እንደሚጠቃለል መግለጫ ይሰጣል፡፡ ጽሁፉ ለጽህፈት ቤቱ ባላቸው ዝግጁነትና ገላጭ ዕሤት ላይ ተመርኩዞ የተመረጡ አገሮች/ድርጅቶች ሕጎችን መሠረት ያደረገ ነው፤ እነርሱም አውስትራልያ፣ ካናዳ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ አየርላንድ፣ እስራኤል፣ ኒውዚላንድ፣ ፊሊፒንስ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስፔይን፣ ታላቋ ብሪታኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስና ዚምባብዌ ናቸው፡፡