ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦች
መድልዎን የሚከለክል ሕግ በአሁኑ ጊዜ በሥራ ስምሪት መድልዎ ጉዳይ እንደ መሠረታዊ ነገር እየታየ ነው፡፡ ይህ አካል ጉዳተኞችን ከሥራ ቦታና ከማኅበረሰቦቻቸው ለማግለል አካል ጉዳት አዘውትሮ እንደ መንሥኤ ያገለግላል በሚለው ግምት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ውጤታማ መድልዎ አልባ ሕግ አግላይ ልማድን የሚዋጋ ሲሆን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ መድልዎን እንዲሁም እንግልትን፣ ትእዛዝና ማነሣሳትን ጨምሮ ብዙ መልኮችን መያዝ ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በሥራ ቦታ ማመቻቸትን ለመስጠትና ልዩነትን ለመቀበል በማንሻበት ጊዜ መድልዎ በራሱ ሂደት ይኖራል ብለው ያስባሉ፡፡ ተመጣጣኝ ማመቻቸት አዲስ ጽንሰ ሃሳብ አይደለም፡፡ ከፍተኛ መደርደሪያ ላይ የተቀመጡ ሳህኖችን ለማውረድ ሰዎች ለምን ወንበር ላይ ይወጣሉ? ሰዎች ለምን የኤሌክትሪክ እርሳስ መቅረጫ ይጠቀማሉ? ሰዎች ለምን በብቃት የተሠሩ የቢሮ ወንበሮችና የሥራ ጣቢያዎች ይጠቀማሉ? በቀላሉ ሲቀመጥ እነዚህ አንድ ተግባር የቀለለ እንዲሆን የሚደረጉ ማስማማቶች ናቸው፣ እንዲሁም ጊዜን ለመቆጠብ ይረዳሉ፡፡ እነዚህ ይበልጥ አምራች ለመሆንና የሥራ ጫናቸውን ለማቅለል ሰዎች ሊያደርጉ የሚችሉአቸው የቀላል ማመቻቸት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ተመጣጣኝ ማመቻቸት አካል ጉዳት ያለበት የሠለጠነ ሰው ለአንድ የሥራ መደብ እንዲያመለክት፣ የመደቡን መሠረታዊ እንቅስቃሴ እንዲያከናውን፣ ወይም የሥራ ስምሪት ጥቅም ማግኘቱን የሚቻል ለማድረግ በሥራ፣ በሥራ ስምሪት ልምምድ፣ ወይም በሥራ አካባቢ የሚደረግ ለውጥ ወይም ማስተካከል ተብሎ ይብራራል፡፡ ይህ እየተወያየንባቸው ካሉት እንቅስቃሴአዊ ድጋፎች ወይም ማኅበራዊ ውቅር ጋር የሚስማማ ሲሆን አንዳንድ ሁኔታዎች የሚኖሩ ከሆነ የአካል ጉዳት አጋጣሚ መቀነስ እንደሚችል ያውቃል፡፡ ይሁንና ማመቻቸቶች እያሉም ቢሆን መድልዎ መከሰት ይችላል፡፡ መድልዎን በሚመለከት ምንም እንኳ ብዙ አገሮች ማስረጃ የማቅረብ ግዴታን ከአቤቱታ አቅራቢ መድልዎ እንደ ፈጸመ ወደ ተነገረለት አካል ወይም ግለሰብ ያዛወሩ ቢሆንም ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ መድልዎ እንደ ተፈጸመበት በተነገረለት ግለሰብ ላይ ያርፋል፡፡