የሥልጠና ዝርዝር

3.2 መደበኛ ገለጻ - የአካል ጉዳት ሕግ አድማስ

  • ቁጥራቸው በዛ ያለ መንግሥታት አንድም በሕዝቡ ውስጥ ለተለያዩ ወገኖች በሚያገለግሉ ሕጎች አማካይነት ወይም አካል ጉዳት ነክ በሆኑ ሕጎች አማካይነት በተለይ በሥራ ስምሪት መስክ በአካል ጉዳት ላይ ተመሥርቶ የሚፈጸም መድልዎን ይከለክላሉ፡፡ ምንም እንኳ የተለዩ ሁኔታዎች እንዲህ ያለውን አያያዝ ባያረጋግጡም ይህ ለውጥ አካል ጉዳተኞችን ለማግለልና እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ለመንፈግ አካል ጉዳት አዘውትሮ እንደ ምክንያት እንደሚያገለግል ያለውን የላቀ ግንዛቤ በይበልጥ ያንጸባርቃል፡፡ አካል ጉዳትን በሕግ ስር ጥበቃ እንደሚደረግለት ሁኔታ ማስከበር ጥበቃን በአድላዊ ጠባይ ላይ የሚያሰፍን ሲሆን መድልዎ አልባ ደንቡን የሚጥሱትን ሰዎች ይቀጣል፡፡
  • መንግሥታት የአካል ጉዳት መድልዎ አልባነትን ከሁለቱ መንገዶች እንደ አንዱ ለማካተት መምረጥ እንደሚችሉ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ይኸውም በመጀመሪያ አካል ጉዳትን በመጥቀስ ለጠቅላላው ሕዝብ የሚያገለግል አጠቃላይ መድልዎ አልባ ሕግ በመቅረጽ እና፣ ሁለተኛም፣ ለአካል ጉዳተኞች ብቻ የሚያገለግል ሕግ በማጽደቅ ነው፡፡ ለሕዝብ የሚያገለግል አጠቃላይና በተናጥል አካል ጉዳትን የሚጠቅስ መድልዎ አልባ ሕግ ያላቸውን መንግሥታት ለማሳየት የገለጻ ማሳያዎች 40-41ን tይጠቀሙ፡፡ በገለጻ ማሳያ 42 ያሉትን ለአካል ጉዳተኞች ብቻ መድልዎ አልባ ሕግ ባላቸው መንግሥታት ምሳሌዎች ያንን ያሟሉ፡፡

    አካል ጉዳትን በተናጥል በመጥቀስ ለጠቅላላው ሕዝብ አጠቃላይ መድልዎ አልባ ሕግ ያላቸው መንግሥታት ምሳሌዎች፡-
    ካናዳ፡- በዘር፣ በብሔራዊ ወይም በጐሣዊ ማንነት፣ በቀለም፣ በሃይማኖት፣ በዕድሜ፣ በፆታ፣ በፆታዊ ዝንባሌ፣ በጋብቻ ሁኔታ፣ በቤተሰብ ሁኔታ፣ በአካል ጉዳት ወይም ይቅርታ በተደረገለት ጥፋት ላይ ተመሥርቶ የሚፈጸም መድልዎን የሚከለክል የሰብአዊ መብቶች ሕግ፣ 1985፡፡

    አየርላንድ፡- በፆታ፣ በጋብቻ ሁኔታ፣ በቤተሰብ ሁኔታ፣ በፆታዊ ዝንባሌ፣ በሃይማኖታዊ እምነት፣ በዕድሜ፣ በአካል ጉዳት፣ በዘርና ከቦታ ወደ ቦታ ተጓዥ በሆነ ማኅበረሰብ አባልነት ላይ ተመሥርቶ የሚፈጸመውን መድልዎ ሕገ ወጥ የሚያደርገው የሥራ ስምሪት ሕግ፣ 1998፡፡
    ናሚብያ፡- የአዎንታዊ እርምጃ ሕግ፣ 1998፣ በዘራቸው ምክንያት ለተጨቆኑ ሰዎች፣ ዘርን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች (አካላዊ ወይም አእምሮአዊ ውሱንነቶች፣ ማለትም ዘርን ወይም ፆታን ሳይለይ) ያገለግላል፡፡
    ለአካል ጉዳተኞች ብቻ  የሚያገለግል መድልዎ አልባ ሕግ ያላቸው መንግሥታት ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
    ኮስታ ሪካ (ሕግ 7600 ለአካል ጉዳተኞች እኩል ዕድሎች በመስጠት ዙሪያ፣ 1996)
    ጋና (የአካል ጉዳተኞች ሕግ፣ 1993)
    ማልታ (እኩል ዕድሎች ለአካል ጉዳኞች ሕግ፣ 2000)

    ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ (የተሀድሶ ሕግ፣ 1973፤ የአሜሪካውያን አካል ጉዳተኞች ሕግ፣ 1990
  •  
    አማራጭ መልመጃ፡- የዚህ መልመጃ ዓላማ የአጠቃላይና የተናጥል መድልዎ አልባ ሕግን ገንቢና አፍራሽ ጎኖች እንዲመለከቱ ለተሳታፊዎች ዕድሉን ለመስጠት ነው፡፡ ተሳታፊዎችን በሁለት ቡድኖች ይክፈሉአቸው፡፡ አንዱን ቡድን ለጠቅላላው ሕዝብ ለሚያገለግል ሙሉ የመድልዎ አልባነት ሕግ መቀረጽ ተሟጋቾች፣ ሌላውን ግማሽ ደግሞ ለተናጥል መድልዎ አልባ ሕግ ተሟጋቾች አድርገው ይመድቡአቸው፡፡ እያንዳንዱ ቡድን አቀራረቡ ለምን የተሻለ እንደ ሆነ የጋራ መከራከሪያውን ለማስረዳት 30 ደቂቃ ይኖረዋል፤ ከዚያም እያዳንዱ ቡድን ሁለት ግለሰቦች ይመርጥና በክርክሩ የየራሱን ቡድን እንዲወክል ያደርጋል፡፡ አስተማሪው እንደ አወያይ የሚያገለግል ሲሆን የትኛው ቡድን አስቀድሞ ጉዳዩን እንደሚያቀርብ ሳንቲም ወደ ላይ ወርውሮ በማሽከርከር ይወስናል፡፡ አቅራቢዎቹ መከራከሪያቸውን ለማቅረብ 10 ደቂቃ ይኖራቸዋል፣ ከዚያም ተመሳሳይ ሁኔታዎች የሚኖሩት ሌላው ቡድን ይከተላል፡፡ ንግግሮቹን ተከትሎ የትኛው ቡድን ጠንካራ መከራከሪያ እንዳቀረበ ክፍሉ ድምጽ ይሰጣል፡፡
  • የሕግ አወጣጥ በሕግ የተሸፈነውን የአካል ጉዳተኞች ፈርጅ በግልጽ ለማብራራት በሚሻበት ጊዜ በማወቅ ወይም ባለማወቅ ጥበቃ የሚደረግላቸውን የግለሰቦች ቡድን እንደማይገድብ ለማረጋገጥ ጥንቃቄ መደረግ እንደሚኖርበት ለተሳታፊዎች በአጽንኦት ያስረዱ፡፡ የአካል ጉዳት መድልዎ ለሚያጋጥማቸው ግን በሕጋዊው የአካል ጉዳት አገላለጽ ውስጥ አንዳንድ መመዘኛዎችን ማሟላት ለሚያቅታቸው ግለሰቦች የሕግ ጥበቃ በማይሰጥበት ጊዜ ይህ መከሰት ይችላል፡፡ አካል ጉዳት የሚለውን ቃል በሕጋቸው ያላብራሩ ግን በዚህ ፋንታ በአካል ጉዳት ላይ ተመሥርቶ ለሚደረግ ያልተረጋገጠ ጎጂ አያያዝ አካል ጉዳት ላለባቸውና ለሌለባቸው ሰዎች ጥበቃ የሚሰጠውን የኔዘርላንድስ ሕግ ምሳሌ ይግለጹ፡፡ እንዲህ ከሆነ ትክክለኛ በሆኑ ወይም በተገመቱ የእክል ጭብጦች ላይ ተመሥርቶ በአንድ ሰው ላይ መድልዎ በመፈጸሙ ዙሪያ አገሮች ትኩረት ማድረግ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ልዩነቶች መቼ መደረግ እንደሚኖርባቸው ግልጽ ለማድረግ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለተሳታፊዎች ያቅረቡ፡- በጣም ውሱን፣ ልዩ የሆነ የአካል ጉዳት አገላለጽ የሚያስፈልገው መቼ ነው? ሰፋ ያለ፣ ይበልጥ አካታች አገላለጽ ተመራጭ የሚሆነው መቼ ነው?

  • እስካሁን የተወያየንባቸውን የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ፣ በሕግ ውስጥ ይህን የማጠቃለያ አቀራረቦች፣ ጥበቃ ለሚደረግላቸው የሕዝብ መደቦች እስካገለገለ ድረስ የአካል ጉዳት አገላለጽ፣ እንዲሁም ባሁኑ ጊዜ ሕጉ በትክክል ሽፋን ሊሰጠው ያሰበው ማን የመሆኑን ምክንያቶች ለተሳታፊዎች ማጠቃለያ ይስጡ፡፡ በአብዛኞቹ የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕጎች ሁሉም አሠሪዎች እንዳልተሸፈኑ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ማን በሕግ ይሸፈናል የሚለው ጥያቄ ጥበቃ የሚደረግለት የግለሰቦች ወገን የትኛው መሆን እንደሚኖርበት ለይቶ ከማወቅ ጋር ተመሳሳይ ሂደት ነው - በሥራው ገበያና ተለይተው በታወቁት ፍላጎቶች ይመራል፡፡ በታላቋ ብሪታኒያና በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በየሕጎቻቸው የሚሸፈኑትን ሠራተኞች እንዴት ለይተው እንደ አወቁ ለማሳየት የገለጻ ማሳያዎች 43-44ን ይጠቀሙ፡፡

    ለምሳሌ በታላቋ ብሪታኒያ የ1995ቱ የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ ከመሠረቱ 20 ወይም ከዚያ በላይ ሠራተኞችን ያቀፈ የሥራ ኃይል ላላቸው አሠሪዎች የሚያገለግል ነው፡፡ ከአሠሪዎች 95 ከመቶውና 4.5 ሚልዮን ሠራተኞች፣ ከአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች ሩብ የሚሆኑትን ጨምሮ፣ ከሽፋኑ መገለላቸውን የመንግሥት ጥናት ይፋ አድርጎአል፡፡ በውጤቱም በ1998 ይህ እርከን ወደ 15 ወይም ከዚያ በላይ ሠራተኞች ዝቅ ተደርጎአል፡፡ በሥራ ስምሪትና በሙያ እኩል አያያዝን በሚመለከት የአውሮፓ ኮሚሽን ባወጣው መመሪያ (2000/78/EC)  መሠረት የአነስተኛ አሠሪዎች ከታክስ ነፃ መሆን በጥቅምት 2004 ሙሉ በሙሉ ተወግዶአል፡፡

    በዩናይትድ ስቴትስ በአሜሪካውያን የአካል ጉዳተኞች ሕግ (እንዲሁም በሌሎች የፌዴራል መድልዎ አልባ ሕጎች) ስር ከ15 በታች ሠራተኞች ያሉአቸው ድርጅቶች ከሕጉ ሽፋን ውጭ ተደርገዋል፡፡ ለዚህ ከግዴታ ነፃ መሆን ምክንያቱ አነስተኛ አሠሪዎች በግዛቶች መካከል ባለው የንግድ ግንኙነት እንዲገቡ ስለማይገደዱ፣ በዚህም የሥራ ስምሪት ፖሊሲዎቻቸውን ከመቆጣጠር የፌዴራል ሕግ አውጪ ክፍሉን ብቁነት ስለሚከለክለው ነው፡፡ አዘውትሮ የቃላት አገባቡ ተመሳሳይ በሆነው በግዛቶች የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕጎች ­ስር አነስተኛ አሠሪዎች ሽፋን ይደረግላቸዋል፡፡