የሥልጠና ዝርዝር
7.2 መደበኛ ገለጻ - በሕጉ ስር መብቶችን ማረጋገጥ
የእኩል ሥራ ስምሪት ሕጎችና እነዚህን ሕጎች ለመተግበር የሚወጡ ደንቦች ውጤታማነት የፍትሐዊ እና/ወይም አስተዳደራዊ ሥነ ሥርዓቶች ለግለሰቦች ዝግጁ በመሆናቸውና በተደራሽነታቸው ላይ እንደሚመረኮዝ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ግለሰቦች፣ እንዲሁም የእነርሱን ፍላጎቶች የሚወክሉት የመድልዎ አልባነት መርሆን ለማስፈጸም ወይም ለፍርድ በቶች በሚቀርቡ የተለያዩ ጉዳዮች ወይም የቡድን ክሶች አማካይነት ተገቢ ማካካሻ ለመጠየቅ እንዲችሉ መደረግ አለባቸው፡፡
የገለጻ ማሳያ 120ን በመጠቀም አካል ጉዳት ነክ አቤቱታዎች በተለያዩ ወቅቶች በሕገ መንግሥታዊ የሕግ ደንቦች፣ በወንጀለኛ መቅጫ ደንቦች፣ በፍትሐ ብሔር ወይም በሠራተኛ ሕግ ደንቦች፣ እንዲሁም በወንጀለኛ መቅጫ፣ በፍትሐ ብሔርና በሕገ መንግሥት ጥምረቶች አማካይነት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ይዘርዝሩ፡፡
- በሕጉ ስር መብቶችን ለማረጋገጥ የበለጠው መሣሪያ ወይም ዘዴ የትኛው ነው - የፍትሐ ብሔር ሕግ ወይስ የሠራተኛ ሕግ ወይስ ሕገ መንግሥታዊ ወይስ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ደግሞስ ለምን? በብዙ አገሮች (በክፍለ ትምህርት 2 ክፍል 4 እንደ ተጠቀሰው) በተለምዶ የላቀ ዝርዝር በመስጠታቸውና አድላዊ አሠራርና ጥበቃ የሚደረግላቸውን መደቦች በሚመለከት የሕጉን ጠቅላላ ስፋትና ግልጽ ትርጓሜዎች ጨምሮ ለሥራ ስምሪት መብቶች አጽንኦት የሰጡ በመሆናቸው አንድን አቤቱታ በፍትሐ ብሔርና በሠራተኛ ሕግ ስር ማቅረብ የቀለለና እምብዛም የማያስፈራ ነው፡፡
- አንዱ ዘዴ ከሌላው ለምን ተሻለ? ሕገ መንግሥት ብሔራዊ ቃናን የሚያስቀምጥና የአካል ጉዳተኞችን መብቶች በማረጋገጥ በአንድ አገር ውስጥ የአካል ጉዳት ጉዳዮችን አስፈላጊነት ከፍ አድርጎ የሚመለከት ሆኖ ሳለ ከላይ እንደ ተዘረዘረው እነርሱ በአጠቃላይ በፍትሐ ብሔርና በሠራተኛ ሕግ ውስጥ የተገለጸ የልዩነት ደረጃ የላቸውም፡፡
- ከአካል ጉዳት የሥራ ስምሪት መድልዎ አልባ ሕግ ጋር በሚገናኝ መልኩ ሁለቱም የሕግ ዓይነቶች አማራጮች መሆን ይኖርባቸዋልን? ከላይ እንደ ተባለው ሁለቱም ወሳኝ ናቸው፡፡
የፍትሐ ብሔርና የሠራተኛ ሕጎች አድላዊ አሠራርና ጥበቃ የሚደረግላቸው መደቦችን በሚመለከት ዝርዝሮቹን ሲገልጹ ሕገ መንግሥት ለማይነጣጠሉ መብቶች ዋስትና ይሰጣል፡፡ ጥያቄዎቹን ለመመለስ 15 ደቂቃ እንዲሁም ለቡድን ሪፖርት ማቅረቢያና መግባባትን ለመገንባት 10 ደቂቃ ለቡድኖቹ ይፍቀዱ፡፡ በመጨረሻዎቹ አምስት ደቂቃዎች አስቀድሞ በክፍል 2.4 እንደ ተገለጸው በሕገ መንግሥት ወይም በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስር ከሚቀርብ ይልቅ በብዙ አገሮች አንድን አቤቱታ በፍትሐ ብሔር ወይም በሠራተኛ ሕግ ስር ማቅረብ የቀለለና እምብዛም የማያስፈራ እንደ ሆነ ደግመው በማሳሰብ ይደምድሙ፡፡ የፍርድ ቤት ሥነ ሥርዓቶች አስፈላጊ ሆነው ሳለ እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ለአካል ጉዳተኞች በማሳደግ ረገድ ውጤታማነታቸው ከተገቢው በላይ መገመት እንደማይኖርበት ያስረዱ፡፡ በተነገረ አድላዊ የአያያዝ ዓይነት ምክንያት እንደ ተበደሉ የሚያስቡ ግለሰብ ሠራተኞች ግን ሕጋዊ ክሶቻቸውን ነፃ በሆነ ፍርድ ቤት ፊት እንዲያቀርቡ ዕድሉ መሰጠት ይኖርበታል፡፡