የሥልጠና ዝርዝር

7.3 መደበኛ ገለጻ - ፍትሐዊ አሠራሮችን ማጠንከር

  • የፍትሕ ሥነ ሥርዓቶች የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ መጠናከር እንደሚችሉ ያስረዱ፡፡ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ለማሳየትና ለማወያየት የገለጻ ማሳያዎች 122-123ን ይጠቀሙ

    • ብሔራዊ ሕግ በመድልዎ ላይ አቤቱታ ባቀረበ ግለሰብ ላይ በአሠሪዎች የሚፈጸም ቅጣት ወይም አጸፋ ሠራተኞችን ሰለባ ከመሆን ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን መያዝ ይኖርበታል፡፡
    • እንደ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም አንድ ሥርዓት ወይም ቅድመ ችሎት ሂደት፣ እንደ ሽምግልና ወይም ሌሎች የሁከት ማስወገድና የማስማማት መንገዶች ባሉ የእርቅ አሠራሮች በባለጉዳዮች መካከል ባለ የእርስበርስ ግንኙነት ላይ የሚደርስ ጉዳት አዘውትሮ ሊወገድ፣ ቢያንስ ሊቀንስ፣ ይችላል፡፡
    • በሰብአዊ መብቶች ሕግ መሆን እንዳለበት የመብቶቻቸውን መከበር ለሚሹ ግለሰቦች የሚያጋጥማቸው የገንዘብ ግዴታ ግለሰብ አመልካቾቹ ክሶቻቸውን በትክክልና በአጥጋቢ ሁኔታ ለፍርድ ቤት እንዲያቀርቡ ለማስቻል እንደ ገንዘብ ድጋፍ ወይም የሕግ ባለሙያዎች ማቅረብ ባሉ በመንግሥት በሚወሰዱ አዎንታዊ እርምጃዎች ሊቀንስ ይችላል፡፡
    • እምብዛም የማያስፈሩ በመሆናቸው እንደ ፍትሐ ብሔርና ሠራተኛ ፍርድ ቤት ክሶች ያሉ ቀላልና ቀጥተኛ የፍርድ ቤት አሠራሮች መመረጥ ይኖርባቸዋል፡፡
    • ጥብቅ የጊዜ ገደብ በመጣልና በቂ የዳኞች ብዛት እንዳለ በማረጋገጥ ሕጋዊ ሥነ ሥርዓቶች የሚፈጁት ጊዜ ሊቀነስ ይችላል፡፡
    • መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ወይም የሠራተኛ ማኅበራት ግለሰብ አመልካቾችን ለመደገፍ በሚያደርጉት እገዛ በክሱ ሂደት ከአመልካቾቹ ጋር እንዲተባበሩ ወይም በእነርሱ ቦታ ሆነው ክሱን እንዲያቀርቡ በማድረግ የተከላካዩ ስሜታዊ ሸክም ሊቀንስ ይችላል፡፡
    • መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የሠራተኛ ማኅበራት አቤቱታዎችን በራሳቸው ስም እንዲያቀርቡ መብቱ ሊሰጣቸው ይችላል (የወል አቤቱታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት)፡፡
    • የማስረጃ ማቅረብ ግዴታን በከፊል በተገለቢጦሽ እንዲፈጸም በማድረግ  የአመልካቹን ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ ማቅለል ይችላል፡፡ ይህም ለአመልካቹ (አካል ጉዳተኛው ግለሰብ) በአካል ጉዳት ምክንያት በደል እንደ ተፈጸመ የሚያሳዩ ጭብጦችን ማቅረብ ይበቃል ማለት ነው፡፡ ይህ አንዴ ከሆነ በኋላ ተከላካዩ ወገን እርምጃው አድላዊ እንዳልነበረ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
    • በመጨረሻ በፍርድ ቤቶች አማካይነት የእኩል ሥራ ስምሪት ዕድሎች ሕጎችና ደንቦች መተግበርና ተፈጻሚ መሆን በዳኝነት አባላትና በሕግ አማካሪዎች ዘንድ ስለ መድልዎ ጉዳዮች እውቀትና የሁኔታዎቹን አሳሳቢነት መረዳትን በቅድመ ሁኔታነት ይጠይቃል፡፡ ይህም ሁኔታ በተለይ ለዳኞች፣ ለጠበቆችና ለሕግ አማካሪዎች ገለጻ ለመስጠትና ግንዛቤን ለማሳደግ በበቂ ሁኔታ የታቀዱና በሀብት (የሰው ኃይል፣ ገንዘብ ወ.ዘ.ተ) የተጠናከሩ ፕሮግራሞች መኖርን ይጠይቃል፡፡

    የእኩል ሥራ ስምሪት ሕግ በሚያጸድቁበት ወይም በሚያሻሽሉበት ጊዜ የሕግ አውጪዎች የፍርድ ቤት አፈጻጸም ሥነ ሥርዓቶችን ማውጣት ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን የሕጉን ውጤታማ አተገባበር ለማረጋገጥ እንዲህ ባሉት የተለያዩ የማስፈጸሚያ ዘዴዎች ላይ ብቻ መተማመን የለባቸውም፡፡

     
    አማራጭ መልመጃ፡- ተሳታፊዎች ከ3 እስከ 5 ግለሰቦችን በሚይዙ አነስተኛ ቡድኖች እንዲከፋፈሉና እነዚህ የአሠራር ዓይነቶች መብቶቻቸውን ለማረጋገጥ በሚሹ አካል ጉዳተኛ ግለሰቦች ላይ ሊኖሩአቸው የሚችሉትን ጫናዎችና ጭንቀቶች የሚቀንሱ ሆነው ሳለ የፍትሕ ሥነ ሥርዓቶችን ያጠናክራሉ ብለው በሚያስቡቸው ስትራቴጂዎች ዙሪያ እንዲወያዩ ይጠይቁአቸው፡፡ የተለመዱ የመጀመሪያ መልሶች የገለጻ ማሳያዎች 122-123 ሊገኙ የሚችሉ ሲሆን ተሳታፊዎች አስቀድሞ ውይይት ከተደረገባቸው ስትራቴጂዎች ባሻገር እንዲያስቡ መበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡