የሥልጠና ዝርዝር

አጀማመር፡- ትውውቅ

  • ይህን ክፍለ ጊዜ ለመጀመር ስክሪኑን ያብሩ፡፡ የገለጻ ማሳያ 113
  • «መሠረታዊ ደንቦች» የሚለው ወረቀት በግልጽ እንደሚታይና ሌሎቹ የተገላጭ ወረቀቶች እንዳልሸፈኑት ያረጋግጡ፡፡
  • የገለጻ ማሳያዎች 114-115ን በመጠቀም የዚህን ክፍለ ጊዜ አጠቃላይ ገጽታ ለተሳታፊዎች ያቅረቡ፡
  • በሴሚናሩ ሂደት ሊነሡ የሚችሉና ለመወያያ ርእሱ አግባብነት ያላቸው ወይም የሌላቸውን ጥያቄዎች «የማቆሚያ ቦታ» በተባለው ወረቀት ላይ እንደሚያሰፍሩ ለተሳታፊዎች ያሳስቡ (ገጽ 19 መ)፡፡