ውጤትን መገምገም

ክፍለ ጊዜውን ከመዝጋትዎ በፊት ተሳታፊዎች ጊዜ ወስደው በአባሪ «ሀ» የቀረበውን የሥልጠና ፕሮግራም ቅኝትና በአባሪ «በ» የሚገኘውን የክፍለ ትምህርት 7 የመማር ዓላማዎች ግምገማ እንዲያጠናቅቁ ይጠይቁአቸው፡፡ ሲያጠናቅቁም ወረቀቶቹን ለእርስዎ እንዲመልሱ ይጠይቁአቸው፡፡ አጠቃላይ የአስተማሪ ውጤታማነትና የተደረሰባቸውን ልዩ የማስተማር ዓላማዎች መጠን ለመለካት መልሶቻቸውን በየክፍሉ ይመድቡአቸው፡፡ መማርን ለማሳደግ ገለጻውና የመማር ልምዱ የትኛው ቦታ ላይ መበልጸግ ይችል እንደ ነበር በተለይ ማስታወሻ ለመያዝ ጊዜ ይኑርዎት፡፡