የሥልጠና ዝርዝር

የኮርስ ማጠቃለያ

  • የገለጻ ማሳያ 131ን ያንሡና በዐውደ ንባቡ የቀረቡት መመሪያዎች ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለቀስቃሾችና እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ስምሪት በሚመለከት ብሔራዊ ወይም ፌዴራል ሕግ በማርቀቅ ለተሰማሩት የተዘጋጁ እንደ ሆኑ ለተሳታፊዎች ያሳስቡ፡፡ በተግባር ይበልጥ ውጤታማ ይሆን ዘንድ ከመመሪያዎቹ ጋር በመዳበል በሥልጠናው ውስጥ የተሰጡት መልመጃዎች እነዚህን ሕጎች በማውጣት ወይም በማሻሻል ረገድ ጠቃሚነታቸው እንደሚረጋገጥ ተስፋ ይደረጋል፡፡

    በተጨማሪም የመመሪያዎቹ ቀዳሚ ትኩረት በአሁኑ ወቅት የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ስምሪት ለማሳደግ በቦታው ባሉ የፍትሐ ብሔር፣ የሠራተኛ ሕግና ተያያዥ የፖሊሲ ዓይነቶች ላይ ሆኖ ሳለ እንዲሁም ትኩረቱ ተግባራዊ ውጤቱን ለማሳደግ በተመጣጣኝ ማመቻቸትና በኮታ ሕጎች አማካይነት የመድልዎ አልባነት ሕግ ይበልጥ በሚሻሻልበት ሁኔታ ዙሪያ ሆኖአል፡፡

  • የገለጻ ማሳያ 132ን በመጠቀም ለአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን የሚያሳድግ ሕግ መጽደቅ ወይም እንዲህ ያለውን ሕግ ለመተግበር የሚሹ ፖሊሲዎች መቀረጽ በሚታሰብበት ጊዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ውሳኝ መርሆዎች እንደ ሆኑ ያስረዱ፡-

    • የአካል ጉዳት ሕጎችና ፖሊሲዎች ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕጎች ጋር ሙሉ በሙሉ መስማማት ይኖርባቸዋል፤
    • ደንቦች ከሌሎች ብሔራዊ ሕጎችና ፖሊሲዎች ጋር መጣጣም ይኖርባቸዋል፤
    • አገልግሎት ላይ የዋለ የአካል ጉዳቶች አተረጓጐም ወይም አተረጓጐሞች በግለሰባዊ ወይም በአካባቢያዊ መሰናክሎች የተነሣ አካል ጉዳተኞች በክፍቱ የሥራ ስምሪት ገበያ ከመሳተፍ ሊገቱአቸው የሚችሉበትን እውነታ ማንጸባረቅ ይኖርባቸዋል፤
    • የተጎዱ ግለሰቦችን የሚጠቅሙ አንዳንድ ጊዜያዊ አማራጭ አያያዞችን የሚያቀርቡ የአዎንታዊ ተግባር እርምጃዎች ደንቦች መውጣት ይኖርባቸዋል፤
    • የአካል ጉዳት የሥርዓተ ፆታ መለኪያ ሁልጊዜ ግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል፤
    • የአሠሪዎችን ማኅበራት፣ የሠራተኞችን ማኅበራት፣ የአካል ጉዳተኞችን ማኅበራትና ፍላጎቱ ያላቸውን ወገኖች ጨምሮ ሕጎችና ፖሊሲዎች የማውጣት ሂደት ከሁሉም ባለ ድርሻዎች ጋር በሚደረግ ምክክር አማካይነት አሳታፊ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • የገለጻ ማሳያዎች 133-134ን በመጠቀም በሥራው ገበያ በአካል ጉዳት ጭብጦች ላይ ተመሥርቶ የሚፈጸም መድልዎን ለመከልከል የታቀደ ሕግን ለማጽደቅ በሚጤንበት ጊዜ የሚከተሉት መመሪያዎችና መርሆዎች ወሳኝ መሆናቸውን ያስረዱ፡፡

    መድልዎን የሚከለክል ሕግ፡-

    • አካል ጉዳት ጥበቃ የሚደረግለት ጭብጥ መሆኑን በግልጽ መጥቀስ ይኖርበታል፤
    • ለአካል ጉዳት ትርጓሜ በሚሰጥበት ጊዜ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል፤
    • ለአራቱ የመድልዎ ዓይነቶች ሁሉ ማለትም ቀጥተኛ መድልዎ፣ ቀጥተኛ ያልሆነ መድልዎ፣ እንግልት፣ መድልዎ ለመፈጸም ትእዛዝ መስጠት ለሚባሉት ሽፋን መስጠት ይኖርበታል፤
    • «ለማይመጣጠን ሸክም» መከላከያ ግንዛቤ የሚሰጥ ሆኖ ሳለ ለተመጣጣኝ ማመቻቸት ደንብ ማውጣትና ይህም ምንን እንደሚያጠቃልል ማብራራት ይኖርበታል፤
    • በጥንቃቄ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን ሀቀኛ ሙያ ነክ መስፈርቶችን መፍቀድ ይኖርበታል፤
    • አቤቱታ አቅራቢው ወገን የመድልዎ መኖር ሊገመት የሚችልባቸውን ጭብጦች እስካቀረበ ድረስ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ መድልዎ ፈጽሞአል ወደ ተባለው ግለሰብ እንደሚዛወር መደንገግ ይኖርበታል፤
    • በማኅበራዊ የፖሊሲ እርምጃዎች መታገዝ ይኖበታል፣ እንዲሁም
    • የአዎንታዊ ተግባር እርምጃዎችን መፍቀድ ይኖርበታል፡፡
  • የገለጻ ማሳያዎች 135-136ን በመጠቀም የኮታ ሕጎች መጽደቅ በሚጤንበት ጊዜ የሚከተሉት መርሆዎች ወሳኝ እንደ ሆኑ ያስረዱ፡፡ የኮታ ሕጎች፡-

    • አካል ጉዳተኛ ሥራ ፈላጊዎች ሥራ እንዲያገኙ ለመርዳት የታቀዱ መሆን ይኖርባቸዋል፤
    • የአሠሪዎችን ተገዢነት ለማበረታታት እንደ ማካካሻ ቀረጥና ውጤታማ የማስፈጸሚያ አሠራር ባለ ማበረታቻ የተደገፉ መሆን ይኖርባቸዋል፤
    • አካል ጉዳተኞችን ከመመልመል እና/ወይም ቀረጥ ከመክፈል በተጨማሪ የኮታ ግዴታን የሚያሟሉባቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን ለአሠሪዎች መስጠት ይኖርባቸዋል፤
    • በግልጽ በታወቁ የፖሊሲ ግቦች ላይ መመሥረትና በግልጽ በተለዩ የአካል ጉዳተኞች ቡድን ላይ ማተኮር ይኖርባቸዋል፤
    • አካል ጉዳት እንዳለባቸው ለታወቁት ግለሰቦች እርግጠኛ ጥቅሞች የማግኘት ዋስትናን በሚያረጋግጠው የምዝገባ/ለይቶ የማወቅ አሠራር ላይ የተመሠረቱ መሆን ይኖርባቸዋል፤
    • በጥያቄ ውስጥ ላለው መንግሥት ኤኮኖሚያዊ ሁኔታና የሥራ ስምሪት ምሳሌ ተስማሚ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • የእኩል ዕድሎች ሕግና የፖሊሲ እርምጃዎች ውጤታማ ስኬት አዘውትሮ የሚመሠረትባቸውን ሁኔታዎች ለመመልከት የገለጻ ማሳያ 137ን ይጠቀሙ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎችና ምልከታ የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

    • ጠቅላላና ቴክኒካዊ መረጃና ምክርን ጨምሮ የመረጃ ዘመቻዎች፤
    • የሥራ ስምሪት ድጋፍ  እርምጃዎች፤
    • ሕጎችና ፖሊሲዎች በኅብረተሰቡ ውስጥ ያሉ ተጎጂ ወገኖችን የተለያዩ ፍላጎቶች የሚያንጸባርቁበት መጠን፤
    • ከቁልፍ ባለ ድርሻዎች - ከአካል ጉዳተኞች ማኅበራት፣ ከአሠሪዎችና ከሠራተኞች ማኅበራት፣ ከአገልግሎት ሰጪዎችና እንዲሁም አግባብነት ካላቸው የመንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ጋር ሰፊ ስልታዊ ምክክር፤
    • በነባር አካላት አማካይነት ወይም ለዚህ ዓላማ በተቋቋሙ ግብረ ኃይሎች አማካይነት በተስማሚ ሁኔታ መደበኛ የተደረጉ ምክክሮች፡፡
  • የሕጉ ውጤታማ ተፈጻሚነት ግለሰቦች ሕጋዊ ክሶቻቸውን ወደ ፍርድ ቤት እንዲያመጡ ለማስቻል የሥነ ሥርዓቶች ደንብ ማውጣት እንደሚጠይቅ ለተሳታፊዎች ያሳስቡ፡፡ በተጨማሪም እንደ እንባ ጠባቂ ተቅዋሞች ወይም የመብቶች ኮሚሽኖች በመሳሰሉት አማካይነት አፈጻጸሙን ማራመድ አስፈላጊ ነው፡፡ የተፈጻሚነት አሠራሮች ከጅምሩ የታቀዱና በበቂ ሁኔታ የዳበሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • በክፍሉ ውስጥ እየተዘዋወሩ ተሳታፊዎች የገለጻ ማሳያ 138 ለቀረቡት ጥያቄዎች መልሶችን እንዲያጋሩ በመጠየቅ ፕሮግራሙን ይዝጉ፡

    • በዚህ ፕሮግራም ከመሳተፍ ምን ግንዛቤዎችን አገኙ?
    • ይህን መረጃ በመጠቀም ረገድ እርስዎ የሚያጤኑት የመጀመሪያ እርምጃ ምንድን ነው?