ሊገኙ የሚችሉ ሌሎች ምንጮች

የተለያዩ አገሮች የአካል ጉዳት ፖሊሲዎች ጉዳየ ጥናቶች

  • Comprehensive Disability Policy Framework for Kosovo
    አጠቃላይ የአካል ጉዳት ፖሊሲ መዐቀፍ ለኮሶቮ
    http://www.see-educoop.net/education_in/pdf/compr_disability_policy_frmwrk_kos-yug-kos-enl-t02.pdf

    ዓላማው ፖሊሲ በሚቀረጽበት ጊዜ የአካል ጉዳተኞች ፍላጎቶች ግምት ውስጥ እንደ ገቡ ለማረጋገጥ በኮሶቮ የሚገኙ የአካል ጉዳት ቡድኖች ፖሊሲ በሚታቀድበት ጊዜ ድምጽ እንዲኖራቸው ለማስቻል ነው፡፡ በሀብቶች መኖር ላይ ተመርኮዞ በኮሶቮ በሁሉም የመንግሥት ደረጃዎች አጠቃላይ የአካል ጉዳት ፖሊሲ የመተግበር ተግባር ያለው መምሪያ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ለማቋቋም ዕቅዶች ተዘጋጅተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኮሶቮ ባለው የተመድ ጊዚያዊ አስተዳደር ተልእኮ ውስጥ በአካል ጉዳት ዙሪያ የሚሠራውን ግብረ ኃይል በአካል ጉዳት ጉዳዮች ዙሪያ እንደ መመካከሪያ፣ አማካሪና ተቆጣጣሪ መዋቅር እንዲያገለግል ወደ አካል ጉዳት ምክር ቤት እንዲለወጥ ደግሞ ታስቦአል፡፡

  • Country Profile on Disability (Sri Lanka)
    በአካል ጉዳት ዙሪያ አጭር አገራዊ መረጃ (ስሪ ላንካ)
    http://www.ilo.org/public/english/region/asro/bangkok/ability/activitiesinsc.htm#SriLanka

    ስሪ ላንካ አካል ጉዳተኞች በመብቶቻቸው ለመጠቀም ለሚፈልጉአቸው አገልግሎቶችና የሥራ ቦታ መብቶች መልስ ለመስጠት በምታደርጋቸው ጥረቶች ወደ ፊት እየተራመደች ነው፡፡ የዓለም ሥራ ድርጅት ይህን ጥረት ለመርዳት ለተለያዩ የመንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ ለሲሎን የአሠሪዎች ፌዴሬሽንና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ከአሠርት ዓመታት በላይ የቴክኒክ እርዳታ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን የሚካሄዱ ስብሰባዎችና እንቅስቃሴዎችን ከሌሎች ጋር አብሮ ደግፎአል፡፡

  • Disability and Citizenship in Post-Soviet Ukraine: An Anthropological Critique
    አካል ጉዳትና ዜግነት በድኅረ ሶቭዬት ዩክሬይን፤ ነገረ-ሰብአዊ (አንትሮፖሎጂካል) ትንታኔ
    http://www.ukrainianstudies.uottawa.ca/pdf/P_Phillips_Danyliw05.pdf

    ጽሁፉ በመለወጥ ላይ ባለው የደህንነት ሁኔታ የተወሰኑ ሰዎች የተለዩ ዜጎች ወደ መሆን፣ በመለወጥም ላይ - እየተለወጡም - ያሉባቸውን ውስብስብ ሂደቶች ለመግለጽ በፍጥነት እያደገ ያለውን የዩክሬይን የአካል ጉዳት እንቅስቃሴን በዜግነት መነጽር አማካይነት ይመረምራል፡፡

  • Disability Law in Germany: An Overview on Employment, Education and Access
    የአካል ጉዳት ሕግ በጀርመን፡- በሥራ ስምሪት፣ በትምህርትና በተጠቃሚነት ዙሪያ አጠቃላይ እይታ
    http://www.germanlawjournal.com/article.php?id=515

    በጀርመን ሕግ ስር አካል ጉዳተኞች አካል ጉዳታቸውን ለመከላከል፣ ለማጥፋት ወይም ለማሻሻል እርዳታና ድጋፍ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ አጠቃላይ ግቡ በተቻለ መጠን የአካል ጉዳት ውጤቶችን ለማሸነፍና አካል ጉዳተኞችን በሁሉም የኅብረተሰብ መስኮች፣ በተለይም በሥራው ገበያና በማኅብረሰብ ሕይወት እንዲሳተፉ ለማስቻል ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ በሕዝባዊ ሕንፃዎች፣ በመንገዶች፣ ወዘተ. በግንባታ ከመሰናክል ነፃ የሆኑ ዲዛይኖችን እንዲያቀርብና በተለይ በአስተዳደራዊ የኢንተርኔት ድረ ገጾች፣ ይፋ ቅጾችና ማስታወቂያዎች ከመሰናክል ነፃ የሆነ የመገናኛ ተጠቃሚነትን የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ በሕዝብ ማመላለሻው ዘርፍ ሁሉም የትራንስፖርት ዘዴዎችና መገልገያዎች (አውቶቡስ፣ ባቡር፣ ወዘተ.) ከመሰናክል ነፃ እንዲሆኑ የሚጠየቁ ሲሆን አነዚህ ከመሰናክል ነፃ የመሆን ደንቦች ለምግብ ቤቶችም ያለግላሉ፡፡

  • The Right to Equal Opportunity and Treatment: Employment of Persons with Disabilities in Slovenia.
    የእኩል ዕድልና አያያዝ መብት፤ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት በስሎቤንያ
    http://www.intjrehabilres.com/pt/re/intjrr/abstract.00004356-200412000-00011.htm

    ጽሁፉ በ2002/2003 በተሀድሶ ተቅዋም የተደረገውን ምርምር አጭር መግለጫ ያቀርባል፡፡ በጽሁፉ የመጀመሪያ ክፍል ከ1999 እስከ 2002 ባለው ወቅት የአካል ጉዳተኞችን ተሀድሶና የሥራ ስምሪት ለማሰደግ በስሎቬንያ የጸደቁ ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞችና እርምጃዎች ተተንትነዋል፡፡ ቁልፍ ግኝቱ አካል ጉዳት ከሌለባቸው ሰዎች ይልቅ አካል ጉዳተኞች በሥራው ገበያ የሚገኙበት ሁኔታ በጐላ ደረጃ ደካማ መሆኑ ነው፡፡ ሁለተኛው ክፍል የምርምሩን ተግባራዊ ክፍል የሚያካትት ሲሆን አሠሪዎች ለአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት ያሉአቸውን የአመለካከቶች ችግሮች ይዳስሳል፡፡