የሥልጠና ዝርዝር

7.1 መደበኛ ገለጻ - ሕጉ በተግባር ሲተረጐም

  • ሕጎችና ፖሊሲዎች በመረቀቅ ደረጃ ላይ እያሉ ተፈጻሚ የሚሆኑባቸውን መንገዶች ማቀድ በጣም አስፈላጊ እንደ ሆነ አጽንኦት ይስጡ፡፡ ተፈላጊ የሆኑ ቀዳሚ ተግባሮች ያሉ ሲሆን እነርሱም ማእከላዊ አስተዳደራዊ መረጃ አሰባሰብን፣ ቁጥጥርና ምርመራዎችን፣ ክርክር አፈታትና አቤቱታዎችን፣ እንዲሁም ውሳኔ አሰጣጥና ፍርዶችን ያካትታሉ፣ ግን በእነዚህ የተወሰኑ አይደሉም፡፡ የአንድ ሕግ ተፈጻሚነት በእነርሱ አማካይነት አስቀድሞ ሊታዩ የሚችሉባቸውን መንገዶች ለመዘርዘር የገለጻ ማሳያ 116ን ይጠቀሙ፣ እነርሱም የሥራ ቁጥጥር መሥሪያ ቤት፣ እንደ ብሔራዊ የአካል ጉዳት ምክር ቤት፣ የእንባ ጠባቂ (ኦምቡስማን) ተቅዋም ወይም የእኩልነት ኮሚሽን ያለ አስተዳደራዊ የቁጥጥር ሥርዓት፤ በወንጀለኛ፣ ፍትሐ ብሔር ወይም የሠራተኛ ሕግ ፍርድ ቤቶች ያለ የፍትሕ አሠራር፣ ኢንዱስትሪያዊ የሥራ ስምሪት ልዩ ፍርድ ቤቶች ወይም ከላይ የተጠቀሱት አቀራረቦች ጥምረት ሊሆን ይችላል፡፡ ኦምቡድስማን (Ombudsman) ከስዊድን ቋንቋ የተገኘ ቃል ሲሆን ትርጓሜው የሕግ ተወካይ ማለት ነው፡፡
  • የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ስምሪት በሚመለከት የሚወጣ ሕግ በአጠቃላይ ለሕጉ ተፈጻሚነት ኃላፊነት ከተሰጣቸው ተቅዋማዊ መዋቅሮች ጋር የሚገናኙ ክፍሎችን ይይዛል፤ መዋቅሩ (ለምሳሌ ብሔራዊ የአካል ጉዳት ምክር ቤት) አዲስ ከሆነ ምሥረታውን ማስተዋወቅ፣ አወቃቀሩን፣ ሚናውንና ተግባሮቹን መዘርዘር እንደሚያስፈልግ ለማስረዳት የገለጻ ማሳያ 117ን ይጠቀሙ፡፡  ከአቤቱታ ሥነ ሥርዓቶች፣ ከእገዳዎች (አስተዳደራዊ ወይም የወንጀል ቅጣቶች፣ እስራት፣
    የፍትሐ ብሔር እርምጃዎች) ጋር የሠራተኛ ፍርድ ቤቶች ሚና ደግሞ በሕጉ ውስጥ ሊገለጽ ይችላል፡፡
  • ለእኩል የሥራ ስምሪት ፖሊሲዎችና ሕጎች ተገዢነትን የመቆጣጠርና የመገምገም ተግባሮች ለሚመለከታቸው አስፈጻሚ ድርጅቶች ሊተው እና/ወይም ለልዩ አካላት ወይም ነፃ ለሆኑ ተመራማሪዎች ሊሰጡ እንደሚችሉ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡

    ፖሊሲዎችና ሕጎች አዘውትረው የተቀጠሩ አካል ጉዳተኞችን ብዛት መረጃዎች እንዲሰበስቡና እነዚህን መረጃዎች ለልዩ ድርጅት እንዲያሳውቁ በአሠሪዎች ላይ ግዴታን ይጥላሉ፡፡ ይህን መሰሎቹ መረጃዎች በድርጅቱ ውስጥ እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ለማሳደግና ለማኅበራዊ አጋሮች እንዲሁም የሠራተኛ የኅብረት ስምምነቶችን በሚያረቅቁበት ወይም በሚያሻሽሉበት ወቅት ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡ አካል ጉዳት ቢኖርም ወይም ባይኖር በእነዚህ ሰዎች ዙሪያ የሚሰጠው መረጃ የሚሰበሰብና ለሌሎች የሚተላለፍ እስከ ሆነ ድረስ እንዲህ ያሉት መረጃዎች አሰባሰብ በሚመለከታቸው አካል ጉዳተኞች የግል ምሥጢር መብት ላይ ገደብን ይፈጥራል፡፡

    ይህ የመረጃ ፍላጎት ለተጎዱና ውክልና ላጡ ወገኖች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድሎችን ከማሳደግ ጋር ሊመጣጠን የሚችልበትን ሁኔታ በሚመለከት ጥንቃቄ የተሞላ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ያስረዱ፡፡ የመረጃ አሰባሰቡን ከግል ምሥጢር መብት ጋር ማስታረቅ የግለሰቦች መረጃ ሊሰበሰብና ሊተላለፍ የሚችልባቸው ትክክለኛ ዓላማዎችና በግልጽ የተብራሩ ዓላማዎች አጥብቀው የሚያዝዙ ሕጎችን መጽደቅ በቅድመ ሁኔታነት ይጠይቃል፡፡

     
    አማራጭ መልመጃ፡- ተሳታፊዎች ከ3 እስከ 5 ግለሰቦችን በሚይዙ አነስተኛ ቡድኖች እንዲከፋሉና (የገለጻ ማሳያ 118 እንደ ተብራራው) የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንዲመልሱ ይጠይቁአቸው፡፡
    • የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ስምሪት ሁኔታ በሚመለከት መረጃ መሰብሰብ ለምን አስፈላጊ ሆነ?
    • የመረጃ አሰባሰብ አካል ጉዳተኞችን እንዴት ያስማማል?
    • ይህን ስጋት ለመቀነስ ግን ደግሞ በጣም የሚፈለገውን መረጃ ለማቅረብ የትኛዎቹ አቀራረቦች ሊወሰዱ ይችላሉ?

    ለእያንዳንዱ ጥያቄ መልስ ለመስጠትና ግኝቶቻቸውን ለጠቅላላው ቡድን ለማሳወቅ እንዲዘጋጁ 10 ደቂቃ ይፍቀዱ፤ እንዲሁም ለማጠቃለል 15 ደቂቃ ይፍቀዱ፡፡ ፈረንሳይ ይህን ጉዳይ እንዴት እንደ ፈታችው የሚያሳየውን ከፈረንሳይ የሠራተኛ ሕግ የተወሰደ ምሳሌ በማቅረብ ገለጻ ይስጡ፡፡

    «ለምሳሌ በፈረንሳይ የሠራተኛ ሕግ (L. 520) የግለሰቦችን ስሞች ሳይሆን በሥራ ስምሪት ላይ ያሉትን አካል ጉዳተኞች ብዛት መመዝገብ እንደሚገባ ለስታቲስቲክስ አሰባሰብ ደንብ ወጥቶለታል፡፡»

  • የመረጃ አሰባሰብ እና/ወይም የአስፈጻሚነት ኃላፊነቶች ሊኖሩአቸው የሚችሉ ሌሎች ድርጅቶች ለመዘርዘር የገለጻ ማሳያ 119ን ይጠቀሙ፡፡ ቁጥጥር መሥሪያ ቤቱ በተለመደው የመረጃ መሰብሰብ ግዴታዎች መዐቀፍ ውስጥ የሥራ በአካል ጉዳት ሕግ ወይም ከአካል ጉዳት መለኪያ ጋር በእኩልነት ሕግ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች ወይም ጥሰቶች መረጃ እንዲሰበስብ ጥሪ ሊደረግለት እንደሚችል ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡

    ለእኩል ዕድሎች ፖሊሲዎችና ሕጎች ተገዢነትን የመቆጣጠርና ውጤቶቻቸውንም የመገምገሙ ተግባር እንደ ሰብአዊ መብቶች፣ የእኩል ዕድል ወይም የአካል ጉዳት ኮሚሽን ለመሳሰሉት አካላት ሊመደብ ይችላል፡፡ እነዚህ አካላት አብዛኛውን በግለሰብ አሠሪዎች በሚሰጡ መረጃዎች ላይ ጥገኛ ሲሆኑ ነገር ግን አዘውትረው በራሳቸው ተነሣሽነት ምርመራዎችን የመጀመር ሥልጣን አላቸው፡፡

    የእንባ ጠባቂ (ኦምቡድስማን) ተቅዋሞች አዘውትረው በመንግሥት ባለሥልጣኖች የሚፈጸሙ የሥልጣን መባለጎችን የመቆጣጠር አስተዳደራዊ ተግባሮች ያሉአቸው ሲሆን ለአካል ጉዳት ደንቦች ተገዢነትን ለመቆጣጠር ደግሞ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡

    ተገዢነትን የመቆጣጠር ተግባሩ አካል ጉዳተኞችን የሚወክሉ ድርጅቶችን በመሳሰሉ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በከፊል ሊካሄድ ይችላል፡፡ እነዚህ አካላት እኩል የሥራ ስምሪት ፖሊሲዎችና ሕግ ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በመመርመር ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይሁንና አቤቱታዎችን ለመመርመርና የግለሰብ አሠሪዎችን ተገዢነት ለመለካት ሥልጣኑ - አዘውትሮም ዘዴው - ያንሳቸዋል፤ ከዚህም የተነሣ የቁጥጥሩ ተግባር ለእነዚህ አካላት ብቻ ሊተው አይችልም፡፡

    እነዚህን ተግባሮች የማከናወን ኃላፊነት ለተለያዩ ድርጅቶችና አካላት ሊመደብ እንደሚችል አጽንኦት በመስጠት ይህን ንኡስ ክፍል ይዝጉ፡፡ ይሁንና ውጤታማ ለመሆን እነዚህ ድርጅቶችና አካላት እንደ መረጃ፣ ሠራተኛና ሀብት የመሰለ በቂ አቅምና እነዚህን ተግባሮች ለማካሄድ አስፈላጊ ችሎታዎች እንዲኖሩአቸው ይገባል፡፡