ማጣቀሻዎችና ምንባቦች
-
Shrey, D., & Hursh, N. (1999). Workplace disability management: International trends and perspectives. Journal of Occupational Rehabilitation, 9(1), 45-59.
በሥራ ቦታ የሚያጋጥም ጉዳትና አካል ጉዳት ማኅበራዊና ኤኮኖሚያዊ ወጪ በመላው ዓለም በአሠሪዎችና በኅብረተሰቦች ላይ አፍራሽ ተጽእኖ አለው፡፡ በሥራ ቦታ የአካል ጉዳት አመራር ፖሊሲዎችና አሠራሮች ዓለም አቀፍ አዝማሚያዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደረገባቸው ቅኝት መሠረት በዚህ ጽሁፍ ተዳስሰዋል፡፡ ለአካል ጉዳት አመራር አስተባባሪዎች የሚሰጠው መደበኛ ሥልጠና አላስፈላጊ የሆነ የጊዜ መባከንን እና በሥራ ቦታ የሚያጋጥም አካል ጉዳት ወጪዎችን ከመቀነስ ጋር የሚገናኝ በመሆኑ ውይይት
ተደርጎበታል፡፡ የአካል ጉዳት አመራር ቁጥጥር አሠራር ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች ወደ ሥራ የመመለስ ፕሮግሞችን ለማዳበር እንደ ስልታዊ የዕቅድ አሠራር በጽሁፉ ውስጥ ተጠቃልሎአል፡፡በሚከተለው ድረ ገጽ ይገኛል፣
http://linkresolver.library.cornell.edu:4550/resserv?sid=google&auinit=DE&issn=1053-0487 -
Thornton, P., & Lunt, N. (1997). Employment policies for disabled people in eighteen countries: A review. Social Policy Research Unit, University of York, United Kingdom.
ይህ ጽሁፍ በፖሊሲና በተቅዋማዊ ጭብጥ፣ በአካል ጉዳት ትርጓሜዎች፣ በስታቲስቲክስ፣ በሥራ ስምሪት ድጋፍ አገልግሎቶች፣ በገላጣ የሥራ ስምሪትና ባለ መጠለያ የሥራ ስምሪት፣ በማጠቃለያ፣ በማጣቀሻዎችና በሕጋዊ ግዴታዎች፣ በገንዘብ እርምጃዎችና በአገሮች ረጅም የመብቶች ዝርዝር ዙሪያ የተዘጋጀ ነው፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ እንደ አውስትራልያ፣ ስዊድን፣ ኢጣልያ፣ ፊንላንድና ግሪክ ያሉትን ጨምሮ ብዛት ያለው የአካል ጉዳት የሥራ ስምሪት ፖሊሲ ጠቃሚ መረጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝግጁ ሆኖ ይገኛል፡፡