የሥልጠና ዝርዝር
5.2 መደበኛ ገለጻ - የሥራ ስምሪት ድጋፍ እርምጃዎች
- የሥራ ስምሪት ድጋፍ እርምጃዎች አንድም ለአሠሪው ወይም ለአካል ጉዳተኛው ግለሰብ አለዚያም ለሁለቱም መሰጠት እንደሚችሉ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ገና ውሳኔ ላላገኘ ማንኛውም ሕግ ስኬት ወሳኝ በሆነ መልኩ እነዚህ ድጋፎች ሕጉ ተፈጻሚ ከሚሆንበት ጊዜ ጀምሮ የታቀዱና በበቂ ሁኔታ የተደገፉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንደ ገንዘብ ማትጊያዎች፣ እንደ ልዩ መሣሪያ ያሉ በዓይነት የሚሰጡ ጥቅሞች፣ የቴክኒክ ምክርና የድጋፍ አገልግሎቶችን የመሳሰሉ እነዚህ ድጋፎች ሊይዙ የሚችሉአቸውን ብዙ የተለያዩ መልኮች ለማሳየት የገለጻ ማሳያ 83 ይጠቀሙ፡፡
-
የሥራ ስምሪት ድጋፍ እርምጃዎች የገንዘብ ድጋፍ መልክ በሚይዙበት ጊዜ ገንዘቡ
ከአካል ጉዳተኛው ሠራተኛ የሥራ ስምሪት ጋር ተያያዥ የሆኑ ተጨማሪ ወጪዎችን (ለምሳሌ ተመጣጣኝ ማመቻቸትን የማድረግ ወጪዎች) ለመሸፈን ብቻ ሊውል ይችላል፣ ወይም የገንዘብ ድጋፉ የገንዘብ ማትጊያ እንዲሆን ለአካል ጉዳተኛው ግለሰብ፣ ወይም ይበልጥ አዘውትሮ ለአሠሪው ሊሰጥ ይችላል፡፡ እነዚህን አመራጮች ለማስረዳት የገለጻ ማሳያ 84ን ይጠቀሙ፡፡ለአሠሪዎች የሚሰጠው ማትጊያ አንድን አካል ጉዳተኛ ከመቅጠር ጋር ተያያዥነት ካላቸው ተለይተው ሊታወቁ ከሚችሉ ከማናቸውም ተጨማሪ ወጪዎች እንደሚያልፍ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ይህን የመሰሉት ማትጊያዎች ለአሠሪዎች የሚሰጡ «ወሮታዎች» ተብለው መመደብ የሚችሉ ሲሆን አካል ጉዳተኞችን ከመቅጠር ጋር የሚያያዙ ማናቸውም ወጪዎችን ለመሸፈን ወይም በተለይ እንዲገናኙ ሆነው የታቀዱ አይደሉም፡፡ ይሁንና አካል ጉዳተኞችን እንዲቀጥሩ አሠሪዎችን የመሸለም ልማድን ብዙ የአካል ጉዳት ተሟጋቾች የሚቃወሙት ሲሆን ትችታቸውም ልማዱ አካል ጉዳተኞች ዝቅተኛ ሠራተኞች ናቸው የሚለውን አስተሳሰብ የሚያጠናክር ብቻ ሳይሆን በዝቅተኛ ክፍያና በአነስተኛ የእድገት ዕድል ሠራተኞችን በሚይዙ አሠሪዎች ዘንድ አዘውትሮ ማደናገሪያ ይሆናል ከሚለው ጭብጥ ይመነጫል፡፡ መሠረታዊ ሃሳቡ አካል ጉዳት ከሌለባቸው ሠራተኞች ይልቅ አካል ጉዳተኛው ሠራተኛ ዝቅተኛ አምራች ነው የሚል ከሆነ አሠሪዎች እንዲህ ላሉት ሠራተኞች ዝቅተኛ ክፍያ እንዲከፍፈሉ ሊፈቀድላቸው ይገባል፣ ድጎማው ግን ለአሠሪው ከሚሰጥ ይልቅ ደመወዙን ለሌሎች ሠራተኞች ከሚከፈለው ጋር ከፍ አድርጎ ለማስተካከል ለሠራተኛው መሰጠት ይኖርበታል ብለው ያምናሉ፡፡
ወደ የገለጻ ማሳያ 85 ይሸጋገሩና የተለዩ የሥራ ስምሪት ድጋፍ እርምጃዎች ዓይነቶችን እንደሚመለከቱ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡
ከሥራ ጋር ተያያዥ የሆኑ ዘመናዊ መሣሪያዎች አቅርቦት፡፡
የዐውደ ንባቡን ክፍል 5.2.1 በመጥቀስ የገለጻ ማሳያ 86 የቀረቡትን ምሳሌዎች በመከለስ ይጀምሩ፡፡«ዓይነ ስውር የሆነች ግለሰብ በኮምፒውተር ለመጠቀም ብሬል አንባቢ የሆነ ኪቦርድ ሊያስፈልጋት
ይችላል፡፡»«ሴሬብራል ፓልሲ የተባለ አካል ጉዳት ያለበት ግለሰብ በእርሻ ቦታው ለመሥራት ተስማሚ የግብርና መሣሪያ ሊያስፈልገው ይችላል፡፡»
እነዚህ አንድ አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ ሥራውን/ሥራዋን በውጤታማ ሁኔታ ለማከናወን ሊያስፈልጉአቸው የሚችሉ ከሥራ ጋር የተያያዙ ዘመናዊ መሣሪያዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በብዙ ሁኔታዎች በተዘጋጀ መልክና በርካሽ ዋጋ ሊሠሩ ወይም ተስማሚ ሊደረጉ የሚችሉ ሲሆን አቅርቦታቸውም ችግር አይፈጥርም፡፡ አንዳንድ ጊዜ መሣሪያዎቹን ለማግኘት እና/ወይም ለእነርሱ ለመክፈል ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኛውም ሆነ ወይም ለአሠሪው ውድና ችግር ፈጣሪ ሊሆን እንደሚችል አጉልተው ያሳዩ፡፡ በእነዚህ ሁኔታዎች አማራጮችን ለማየት መልሰው የገለጻ ማሳያ 86 ይጥቀሱ፡፡
መሣሪያዎቹ ለአሠሪው ወይም ለግለሰብ ሠራተኛው በስጦታ የተገኙ ወይም በውሰት የቀረቡ እንደ ሆኑ ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ያድርጉ፡፡ ለግለሰብ ሠራተኞቹ በስጦታ የተገኙ ከሆነ ሥራቸውን ቢለውጡ ዘመናዊ መሣሪያዎቹን ይዘው መሄድ ይችላሉ፡፡ ለአሠሪው በውሰት የቀረቡ ከሆነ ግለሰቡ የሥራ መደቡን በሚለቅቅበት ጊዜ ምን ይሆናል የሚለው ጥያቄ መታሰብ አለበት፡፡ በመጨረሻም መሣሪያዎቹ ከክፍያ ነፃ ሆነው ይቀርቡ እንደ ሆነ አለዚያም ጥቂት ክፍያ ወይም ተቀማጭ ገንዘብ ይከፈል እንደ ሆነ ለሚቀርበው ጥያቄ ዘዴው በሚቀረጽበት ጊዜ መወሰን ያስፈልገዋል፡፡
ከሥራ ጋር ተያያዥ በሆኑ ዘመናዊ መሣሪያዎች ዙሪያ የሚደረገውን ውይይት የሚከተለውን ከታላቋ ብሪታኒያ የተገኘውን ምሳሌ በመጥቀስ ይደምድሙ፡፡ በታላቋ ብሪታኒያ ዘመናዊ መሣሪያ የአገልግሎቶች የተቀናጀ ስብስብ አንድ ክፍል ሆኖ እንደሚሰጥ ለተሳታፊዎች በአጽንኦት ይንገሩ፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የድጋፍ ዘዴዎች በሚቀረጹበት ጊዜ የተለያዩ ፍላጎቶችን ለማስተናገድ በተለዋዋጭ ሁኔታ የተዋሃዱ የግልጽ አገልግሎቶችን ስብስብ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ዙሪያ አጽንኦት ያድርጉ፡፡
«በታላቋ ብሪታኒያ የሥራ ስምሪት አገልግሎት የተባለው መሥሪያ ቤት አንድ አካል ጉዳተኛ ሥራ እንዲይዝ ለመርዳት በተለይ የተቀረጸ የሥራ ስምሪት ተሀድሶ የሚባል የሥራ ዝግጅት ፕሮግራም
ይሰጣል፡፡ ፕሮግራሙ ከግለሰቦቹ አካል ጉዳት የሚነሡና በወቅቱ ወደ ሥራ ስምሪት ለመግባት ወይም በአማራጭ ማንኛውንም ምቹ ሥልጠና ከማግኘት የሚከለክሉ ከሥራ ስምሪት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶችን ይዳስሳል፡፡ የሥራ ዘዴ ማግኘት የተሰኘው ተጨማሪ የብሪታኒያ ዕቅድ ከአካል ጉዳት ጋር የተያያዙ እንቅፋቶችን ለማሸነፍ እንዲረዳ ተግባራዊ ምክር ይሰጣል፡፡ ለሥራ ስምሪት የሚሆኑ ልዩ ድጋፎችን ወይም መሣሪያዎችን፣ በሕንፃዎች ወይም በነባር መሣሪያዎች ላይ ማስተካከያዎችን፣ በሕዝብ ትራንስፖርት ለመጠቀም የማያመች ሲሆን የጒዞ እርዳታን፣ በሥራ ቦታ እርዳታ እንዲሰጥ የድጋፍ ሠራተኛና ቃለ መጠይቅ በሚኖርበት ጊዜ የማግባባት ድጋፍ የሚያደርገውን ጨምሮ በሥራ ስምሪት የሚከሰቱ ተጨማሪ ወጪዎችን በከፊል ለመሸፈን የታቀዱ እርዳታዎችን ይሰጣል፡፡»ለዕለታዊ ኑሮ የሚሆን የዘመናዊ መሣሪያ አቅርቦት፡፡
የዐወደ ንባቡን ክፍል 5.2.2 በመጥቀስ ብዙ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞች በየዕለቱ ሕይወታቸው ራስን የመቻል ደረጃን ለመቀዳጀትና የመንቀሳቀስ ችሎታቸውን ለመጨመር ዘመናዊ መሣሪያ እንደሚያስፈልጋቸው ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ዊልቸሮችና የመስሚያ ድጋፎችን ጨምሮ እንዲህ ያሉትን መሣሪያዎች ምሳሌዎች ለማሳየት የገለጻ ማሳያ 87 ይጠቀሙ፡፡ያለ እነዚህ መሣሪያዎች አካል ጉዳተኞች ሥራ ለማግኘትና ይዘው ለማቆየት አስቸጋሪ እንደሚሆንባቸው አጽንኦት ይስጡ፡፡ በዚህ ምክንያት በሁሉም የሕይወት ገጽታዎች ለመንቀሳቀስ አስፈላጊ የሆኑት የእነዚህ መሠረታዊ መሣሪያዎች አቅርቦት አካል ጉዳተኛ ግለሰቦች የሥራ ስምሪት እንዲይዙ በማስቻል ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ያስረዱ፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለተሳታፊዎች ያቅርቡ፡፡
- «ግለሰቦች በቤታቸው ውስጥ ለመንቀሳቀስ ዓላማ በግድግዳ ላይ የተገጠሙ የሚያዙ ድጋፎችን የሚፈልጉ ሆነው ግን እነዚህ ድጋፎች በማኅበረሰባቸው ወይም በሥራ ቦታቸው ባይኖሩ እንደምታዎቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?»
- «ይህን የግለሰቦቹን ፍላጎት በሌሎች አካባቢዎች ማሟላት የሚችሉ ሌላ ዓይነት መሣሪያዎች አሉን?»
- «እንደዚያ ከሆነ መሣሪያዎቹ በቦታው እንዲገኙ ለማድረግ ምን ትኩረቶች ይደረጉ ዘንድ ያስፈልጋሉ?»
- «አንድ ግለሰብ የሚፈልገው ዘመናዊ መሣሪያ አገልግሎቱ ለሥራ ስምሪት ብቻ ካልሆነ አሠሪው እንዲያቀርብ መጠበቅ ተገቢ ነውን?»
ለመጨረሻው ጥያቄ የሚሰጡት መልሶች ብዙ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያስረዱ፡፡ መልሱ እንዲህ ያለው መሣሪያ አገልግሎት ከሥራ ስምሪት ውጭ በመዋሉ ላይ ይመረኮዛል፣ ምክንያቱም በዚያ ሁኔታ አሠሪው አቅራቢ እንዲሆን መጠበቅ የተገባ ባለመሆኑ ነው፡፡ ይልቁን ከሥራ ጋር ተያያዥ በሆኑ ዘመናዊ መሣሪያዎች እንደ ሆነው ሁሉ ይህ ተግባር ከዕለታዊ ሕይወት ጋር ተያያዥ የሆነውን ይህን መሣሪያ ለማምረትና ለመጠገን የሚችሉ ክፍሎችን ማቋቋም በሚችሉት በመንግሥት ባለሥልጣኖች መቀናጀት ይኖርበታል፡፡ ከሥራ ጋር ተያያዥ በሆኑት መሣሪያዎች እንደ ሆነው ሁሉ ይህ መሣሪያ ከክፍያ ነፃ ሆኖ ይሰጥ ወይም ጥቂት ገንዘብ ያስከፍል እንደ ሆነ የመንግሥት ባለሥልጣኖች መወሰን ይኖርባቸዋል፡፡ በአንዳንድ አገሮች ለመክፈል ከሚጠየቀው ደረጃ በላይ ገቢ ላላቸውና እንዲሁም ከዚህ ደረጃ በታች የሆነ ገቢ ኖሮአቸው መሣሪያውን ከክፍያ ነፃ ለሚያገኙ ሰዎች የሙከራ ዘዴ ያገለግላል፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎቶች አቅርቦት፡፡
የዐውደ ንባቡን ክፍል 5.2.3 በመጥቀስ አካል ጉዳተኞችን ከሚያጋጥሙቸው የተለመዱ ችግሮች አንዱ ትራንስፖርትን እንደሚመለከት ያሳስቡ፡፡ ያጋጠሙ ቀዳሚ እንቅፋቶችና ጉዳዮች አንዳንዶቹን ለተሳታፊዎች መልሶ ለመመልከት የገለጻ ማሳያ 88 ይጠቀሙ፡፡ ይህ ውይይት የተጓደሉ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወደ ሥራና ወደ ሌሎች ቦታዎች የመሄድና የመመለስን ችሎታ መገደብ የመቻሉን እውነታ ያካትታል፡፡ ከዚም በላይ የሕዝብ የመጓጓዣ ዘዴዎች አንዳንድ የአካል ጉዳት ዓይነቶች ላሉባቸው ሰዎች አዘውትረው ተደራሽ ያልሆኑ ናቸው፡፡ በመጨረሻም ብዙ አካል ጉዳተኞች የራሳቸው የሆነ መኪና ገዝተው ለመንዳት ወይም ውድ ታክሲዎችን ለመጠቀም የማይችሉ ናቸው፡፡የአካል ጉዳተኞችን ወደ ሥራ የመሄድና የመመለስ አስተማማኝና ተገቢ ጉዞ ለማሳደግ የተለያዩ እርምጃዎች ሊጀመሩ እንደሚችሉ ያስረዱ፣ እነርሱም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-
- ተደራሽ የሕዝብ ትራንስፖርት ሥርዓት መፍጠር - ይህም አውቶቡሶች፣ ባቡሮች፣ ኤሌክትሪክ ባቡሮች፣ የምድር ውስጥ ማመላለሻዎችና ታክሲዎች ሁሉ ዊልቼር የሚጠቀሙ ሰዎችን ጨምሮ ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ መሆናቸውን ማረጋገጥን ያጠቃልላል፡፡
- አካል ጉዳተኞች አንዳንድ የግል ታክሲዎችን መጠቀም እንደሚችሉ ማረጋገጥ - ወደ ሥራ ለመሄጃና ለመመለሻ ጉዞዎች በአሠሪው ወይም በመንግሥት ባለሥልጣኖች ሊመነዘሩ የሚችሉ ደረሰኞችን በመስጠት፡፡
- የራሳቸውን ትራንስፖርት ለማስተካከል እንዲያስችላቸው ለአካል ጉዳተኛ ግለሰቦች የገንዘብ ድጋፍ መስጠት - ለታክሲ ጉዞ፣ ለተስማሚ መኪና ግዢ ወይም ለመንዳት ወይም ሌላ ሰው ወደ ሥራ እንዲያደርሳቸው ለመክፈል ድጎማ መስጠት፡፡ ደግሞም በብራዚል እንደሚደረገው አካል ጉዳተኛ ግለሰቦች የሕዝብ ማመላለሻዎችን ያለ ክፍያ እንዲጠቀሙ ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡
- ለዊልቼር ተጠቃሚዎች ተደራሽ መሆን የሚችሉ አዘውትሮ ተስማሚ በተደረጉ ሚኒ-ባስ መኪናዎች አካል ጉዳተኞችን ወደ ሥራ መሄድና መመለስ የሚያስችሉ ልዩና የተናጥል ትራንስፖርት ሥርዓቶችን መዘርጋት፡፡
Conclude this section by illustrating with the following example from Australia provided on page 56 of the Primer.«በአውስትራልያ የእንቅስቃሴ አበል የተባለው ድርጅት ደመወዝ በሚከፈልበት ሥራ ስምሪት ላይ ሆነው፣ በበጎ ፈቃደኛነት ሥራ፣ በሙያዊ ሥልጠና፣ ራስን ችሎ የመኖር/ሕይወት ችሎታዎች ሥልጠና ወይም የክፍያ ሥራና ሥልጠና በጥምረት እየወሰዱ ጠቀም ያለ እርዳታ ላላገኙ በሕዝብ ማመላለሻ መጠቀም ለማይችሉ አካል ጉዳተኞች የገንዘብ እርዳታ ያደርጋል፡፡ ተረጂ ግለሰቦች የእንቅስቃሴ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ገንዘቡን እንዴት እንደሚጠቀሙበት ለመወሰን ነፃ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገንዘቡ ለተስማሚ ተሽከርካሪ መግዣ፣ ወይም ሌላ ሰው በግል ተሽከርካሪ የማመላለስ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ለመክፈል፣ ወይም ለታክሲ ጒዞዎች ክፍያ ሊውል ይችላል፡፡»
- ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጡ የገንዘብ ድጋፎች/የገንዘብ ማትጊያዎች፡፡
ወደ የገለጻ ማሳያ 89 በመሸጋገርና የዐውደ ንባቡን ክፍል 5.2.4 በመጥቀስ የሥራ ስምሪት እንዲይዙ ለማስቻል ወይም ለማበረታታት አንዳንድ አካል ጉዳተኞች የገንዘብ ድጋፍ ወይም የገንዘብ ማትጊያዎች ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ እንዲህ ያሉት የገንዘብ ድጋፍና ማትጊያዎች አስፈላጊ ሊሆኑ የሚችሉባቸውን ምክንያቶች አጉልተው ያሳዩ፡፡- ሥራ በሚይዙበት ጊዜ ግለሰቦች ዋስትና ያለውና መደበኛ ገቢ የሚያስገኝላቸውን የአካል ጉዳት ማኅበራዊ ዋስትና ጥቅም የመጠየቅ መብትን ሊተዉ ይችላሉ፡፡
ሥራው ለወደፊት አስተማማኝነቱ እስካለተረጋገጠ ድረስ ይህ አስቸጋሪ ውሳኔ ሊሆን ይችላል፡፡ የአካል ጉዳት ጥቅሞች አሠራር ባላቸው አገሮች ያሉ ፖሊሲ አውጪዎች አካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት በሚይዙበት ጊዜ የማኅበራዊ ዋስትና አሠራር ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር እንደማይፈጥርባቸው ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ - የሥራ ስምሪት አንዱ ማበረታቻ ዘዴ አካል ጉዳተኛ ግለሰቦች በአንድ ምክንያት በሥራ ስምሪት ለመቆየት የማይችሉ ከሆነ ወዲያውኑ የአካል ጉዳት ጥቅማቸውን እንዲጠይቁ መፍቀድ ነው፡፡ ይህ መብት በጊዜ ገደብ የተወሰነ ሊሆን ይችላል - ለምሳሌ አንድ ዓመት፡፡ በብዙ አገሮች ለአካል ጉዳት ጥቅሞች ብቁ ሆኖ ለመታየት ጊዜ የሚወስድና ወደ ሥራ ስምሪት ለመግባት ከጥቅሙ የሚወጡት በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ሥራቸውን ቢያጡ ያ የመጠበቂያ ወቅት ሊቀር እንደሚችል ለተሳታፊዎች በአጽንኦት ያስረዱ፡፡
- የሥራ ስምሪትን ለማሳደግ ሌላው መንገድ ግለሰቦች የሚያገኙት አበል ሳይነካ በማኅበራዊ ዋስትና አበላቸው ላይ እንደ ማሟያ የሚታይ አስከ ተወሰነ ደረጃ ገቢ ለማግኘት ብቁ የሚሆኑበትን «የመሸጋገሪያ» ማስተካከያ መጀመር ነው፡፡ ከዚያም ከዚህ እርከን በላይ ላለው ገቢ እስከ ተወሰነ ደረጃ ከዚህ አበል ላይ ተመጣጣኝ ቅነሳ ይደረግና ከከፍተኛ ደረጃ በላይ ላለው አበሉ ይቋረጣል፡፡ የገንዘብ ድጋፎችና ማትጊያዎች የተፈለጉበት ሌላው ምክንያት ብዙ አካል ጉዳተኞች ዝቅተኛ ክፍያ የሚያስገኝ ሥራ ብቻ ለማገኘት የሚችሉ መሆናቸው ነው፡፡ ከገንዘብ እይታ አኳያ ሲታይ ይህ ክስተት የአካል ጉዳት ጥቅሞችን ከመጠየቅ ሌላ በተሻለ ሁኔታ ላይ እንዳይገኙ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ ዝቅተኛ ክፍያን ወደ ላይ የሚያወጣ የገንዘብ ማትጊያ ግለሰቦች እጅግ የተጓደለ ክፍያ የሚገኝበትን ሥራ መያዝ ሙያን ለማዳበር እንደ መጀመሪያ እርምጃ አድርገው እንዲወስዱት ለማበረታታት ሊረዳ ይችላል፡፡
- ሌላው ነጥብ አዲስ ሥራ የሚጀምሩ ሰዎች አዘውትሮ ሥራውን ከመጀመራቸው አስቀድሞ አንዳንድ ወጪዎችን መሸፈን ያለባቸው መሆኑ ነው፡፡ እነዚህ ወጪዎች አዳዲስ ልብሶች፣ ለዘመናዊ መሣሪያ ወይም ለሥልጠና፣ ወይም ቅድመ ክፍያ የትራንስፖርት ትኬቶችን ከመግዛት ፍላጎት የመጡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ውሱን ገቢ ላላቸው አካል ጉዳተኞች የሚሰጥ የአንድ ጊዜ ወይም ቀጣይ ክፍያ ያሉባቸውን ወጪዎች ለመሸፈን የሚረዳ ሲሆን ሥራውን ለመያዝ የዚህን ወጪ እንቅፋት መሆን ይከላከላል፡፡
በዐውደ ንባቡ ገጽ 52 የቀረቡትን ከኒውዚላንድና ከፊንላንድ የተገኙትን ምሳሌዎች በመግለጽ ይህን ክፍል ይደምድሙ፡፡
«በኒውዚላንድ የአካል ጉዳት ውሎ አበል የተባለው ድርጅት ሰዎች ለሚያጋጥሙአቸው ቀጣይነት ያላቸው መደበኛ ወጪዎች አካል ጉዳት ስላላቸው ማካካሻ ይሰጣቸዋል፡፡ የሚከፈለው ገንዘብ መጠን በግለሰቦቹ ወጪና በገቢአቸው ደረጃ ላይ ይመረኮዛል፡፡»
«በፊንላንድ ዕድሜአቸው በ14 እና በ64 መካከል የሆነ አካል ጉዳተኞች በሥራም ሆነ በትምህርት የየዕለቱ ሕይወታቸውን በተሻለ ለመወጣት እንዲረዳቸው የአካል ጉዳት አበል ይከፈላቸዋል፡፡ አበሉ በአካል ጉዳት ወይም በተዛባ ጤንነት ምክንያት ለሚከተሉ ወጪዎች እንደ ማካካሻ የታቀደ ነው፡፡ አበሉ በአካል ጉዳቱ ጽኑነት ላይ ተመርኩዞ በሦስት ደረጃዎች ይከፈላል፡፡ የተቀባዩ ገቢ ወይም ንብረቶች ግብር የማይከፈልበት በሆነው በአበሉ ላይ ተፅእኖ አያደርጉም፡፡»
- ሥራ በሚይዙበት ጊዜ ግለሰቦች ዋስትና ያለውና መደበኛ ገቢ የሚያስገኝላቸውን የአካል ጉዳት ማኅበራዊ ዋስትና ጥቅም የመጠየቅ መብትን ሊተዉ ይችላሉ፡፡
- ለአሠሪዎች የሚሰጡ የገንዘብ ድጋፍ/የገንዘብ ማትጊያዎች፡፡
የገንዘብ እርዳታዎችን፣ የግብር ብድሮችን፣ ግብር ቅነሳዎችንና የደመወዝ ድጎማዎችን ጨምሮ ለአሠሪዎች የሚሰጡ የገንዘብ ማትጊያዎች የተለያዩ መልኮችን ሊይዙ እንደሚችሉ ለማስረዳት የገለጻ ማሳያ 90 ይጠቀሙ፡፡ ለአሠሪዎች የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ሁለት መልኮችን ሊይዝ እንደሚችል ለተሳታፊዎች አጽንኦት ይስጡ - እነርሱም መልካም አሠራርን ለመደገፍ የሚሰጥ ማትጊያ፣ ወይም ከአንድ አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ ጋር ለተያያዙ ዝቅተኛ ምርታማነት ወይም ተጨማሪ ወጪዎችን ለማካካስ ለአሠሪው የሚሰጥ ድጎማ ናቸው፡፡
አንድን አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ ከመቅጠር ጋር ተያያዥ የሆኑ ተጨማሪ ወጪዎችን ለመሸፈን የመንግሥት ባለሥልጣኖች በእርዳታ ወይም በግብር ማትጊያ መልክ ለአሠሪዎች የገንዘብ ድጎማዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ያስረዱ፡፡ ለምሳሌ በአንዳንድ ሁኔታዎች ተጨማሪ ሥልጠናን በመስጠት ወይም በመገልገያዎች ላይ አስፈላጊ ማስማማቶችን ከማድረግ የተነሣ አሠሪው አንዳንድ ወጪዎች ሊያጋጥሙት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ወጪዎች ተስፋ የሚያስቆርጡ ወይም አንድን አካል ጉዳተኛ ላለመቅጠር ምክንያት እንደማይሆኑ ለማረጋገጥ የመንግሥት ባለሥልጣኖች እነዚህን ወጪዎች በሙሉ ወይም በከፊል ማሟላት ይችላሉ፡፡ ዳሩ ግን በብዙ ሁኔታዎች አሠሪዎች ተጨማሪ ወጪዎችን የማያስከትሉ ሲሆን የገንዘብ ድጎማዎችም የሚያስፈልጉ አይሆኑም፡፡ ይህንን በዐውደ ንባቡ ገጽ 53 ከቤልጂየምና ከጀርመን በተገኙት ምሳሌዎች ያስረዱ፡፡«በቤልጂየም በማኅበራዊ አጋሮች መካከል የተፈጸመ የኅብረት ስምምነት በአንዳንድ ሁኔታዎች ከአካል ጉዳተኛ ሠራተኛ ጠቅላላ የደመወዝና ጥቅማጥቅም ክፍያ አሠሪው ከፊሉን ብቻ አንደሚከፍልና የተቀረው በመንግሥት አካል እንደሚከፈል ይገልጻል፡፡ በተለዩ ሁኔታዎች በኅብረት ስምምነቶች ወይም በግብር ቢሮ የተቀመጠውንና ከዝቅተኛ ደረጃ በታች የሆነውን የደመወዝ ክፍያ አካል ጉዳት እንዳለባቸው ለታወቁት ሠራተኞች አሠሪው እንዲከፍል የሥራ ተቆጣጣሪዎች ሊፈቅዱለት ይችላሉ፡፡ ይህ ቅናሽ -ከመደበኛው የደመወዝ ክፍያ ፈጽሞ ከ50 ከመቶ በታች የማይወርደው- ዝቅተኛ ለሆነው የሠራተኛው ምርታማነት ማካካሻ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ከዚያም አሠሪው እንዲከፍል በተፈቀደለትና በመደበኛው የደመወዝ ክፍያ መካከል ያለው ልዩነት በመንግሥት ባለሥልጣኖች ለአካል ጉዳተኛው ይከፈላል፡፡»
«በጀርመን የተመጣጣኝ ማመቻቸት ግዴታዎችን ለማሟላት አሠሪዎች ለብድር ወይም ለእርዳታ ማመልከት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ለአካል ጉዳተኞች ሁሉ የደመወዝ ድጎማዎችና ሙያዊ ሥልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡ ለተመጣጣኝ ማመቻቸት ወይም ለኮታ ግዴታዎች ተገዢ ያልሆኑ አሠሪዎችም የመስክ ሥራዎቻቸውን ወይም የሥራ ቦታዎቻቸውን ተደራሽ ለማድረግ እርዳታ ለመጠየቅ ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡ የደመወዝ ድጎማዎች አንድ አካል ጉዳተኛ ዝቅተኛ የምርታማነት ደረጃ በሚኖረው ጊዜ ይሰጣሉ፡፡ የሚሰጠው ገንዘብ መጠን በአካል ጉዳቱ ጽኑነትና እንደ ዕድሜ ባሉ መካተትን በሚገቱ ሌሎች ጭብጦች ላይ ይመረኮዛል፡፡ የደመወዝ ድጎማዎች በተለያዩ ጭብጦች ላይ በመመሥረት በከፍተኛው ከሦስት አስከ ስምንት ዓመታት ለሚደርስ የተወሰነ የጊዜ ቆይታ ይሰጣሉ፡፡»
«በኔዘርላንድስ ድጎማዎች ከውህደትና ከመልሶ ውህደት ጋር ለሚያያዙ የቁሳቁሶች/አገልግሎቶች ወጪዎች እንዲውሉ ለአሠሪው ወይም ለአካል ጉዳተኛው ሠራተኛ ይሰጣሉ፡፡ እነዚህም ከልዩ የቢሮ ዕቃዎች ጀምሮ እስከ ትራንስፖርት መገልገያዎች፣ ትምህርት ወይም የሥልጠና ቁሳቁሶች ሊለያዩ ይችላሉ፡፡» ምልመላን ለማበረታታት የሚሰጡ የገንዘብ ድጋፍ/የገንዘብ ማትጊያዎች
ወደ ኋላ ተመልሰው የገለጻ ማሳያ 90 በመጥቀስ አንድን አካል ጉዳተኛ እንዲቀጥሩ ለማበረታታት ለአሠሪዎች የሚሰጡ የገንዘብ ማትጊያዎች እርዳታዎችን፣ የደመወዝ ድጎማዎችን ወይም የግብር ማትጊያዎችን ጨምሮ የተለያዩ መልኮችን እንደሚይዙ ለተሳታፊዎች ያሳስቡ፡፡ከላይ ከተጠቀሰው የገንዘብ ድጎማ ጋር በማይመሳሰል መልኩ የዚህ ማትጊያ ዋጋ አንድን የተለየ አካል ጉዳተኛ በመቅጠር አማካይነት በአንድ አሠሪ ላይ ከሚደርሱ ማናቸውም ተጨማሪ ወጪዎች ጋር እንደማይያያዝ፣ በእነርሱም እንደማይወሰን ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ የገንዘብ ማትጊያው አሠሪዎች አካል ጉዳተኛ ግለሰቦችን እንዲወስዱ እንደ ማበረታቻ የታሰበ ሲሆን በሥራው ገበያ የተለዩ ችግሮች ለሚያጋጥሙአቸው አካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪትን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ የማትጊያው ዋጋ ሠራተኛውን በመቅጠር ረገድ ከታሰበው ችግር ጋር ሊያያዝ ይችላል፡፡
ከዚህ ምሳሌ ጋር ለማስረዳትና የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመጠየቅ የገለጻ ማሳያ 91 ይጠቀሙ፡፡
«ቀለል ያለ አካል ጉዳት ካለበት ወይም የተረጋገጠ የሥራ ታሪክ ካለው ሰው ይልቅ ጽኑ አካል ጉዳት ያለበትን ወይም የተረጋገጠ የሥራ ታሪክ የሌለውን ሰው መቅጠር ይበልጥ አስቸጋሪ ሆኖ ሊታይ
ይችላል፡፡»- «ይህን/ይህችን ግለሰብ እንዲቀጥሩ ለአሠሪዎች የገንዘብ ማትጊያ መስጠት ለምን በተለየ ሁኔታ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል?»
- «ለአካል ጉዳተኛ ግለሰቡ አንዳች ጥቅም አለ?»
- «ለአሠሪው የገንዘብ ማትጊያ በመስጠት ረገድ እርስዎ አሉታዎች ወይም እንከኖች ያያሉን?»
- «ለዚህ ዓይነቱ የገንዘብ ማትጊያ ማንን ብቁ እንደሚያደርጉ እንዴት ይወስናሉ?»
ማትጊያው ሠራተኛው ሥራ አጥ ሆኖ ከቆየበት ጊዜ መጠን ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ለአንድ ዓመት ወይም ከዚያ ለበለጠ ጊዜ ሥራ አጥ ሆኖ የቆየውን ሠራተኛ ለመቅጠር ከፍ ያለ ማትጊያ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ማትጊያው ከግለሰቡ የሥራ አቅም ጋር የተያያዘ ከመሆኑ ይልቅ ይህ አቀራረብ የማግለል አጋጣሚው ያነሰና ለማስተዳደር የቀለለ ነው፡፡ ማትጊያው ጊዜያዊ (ለምሳሌ በአንድ ወይም በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚሰጥ ወርሃዊ ክፍያ) ወይም የጊዜ ገደብ የሌለው ሊሆን ይችላል፡፡
የገለጻ ማሳያ 92ን በመጠቀም የገንዘብ ማትጊያ እርምጃዎች በሚቀረጹበት ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉትን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ችግሮች ለመከላከል ወይም ለመቀነስ እርምጃዎች መወሰድ እንደሚኖርባቸው ለተሳታፊዎች ያሳስቡ፡፡
- ዘዴዎቹ ጊዜያዊ በሚሆኑበት ጊዜ አሠሪዎች በዘዴው ስር የተቀጠሩትን ሠራተኞች ወዲያውኑ ለማባረርና ለገንዘብ ድጋፍ ብቁ የሆነ አዲስ አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ ለመቅጠር ያዘነብላሉ፤
- ይህን በመሳሰሉ ዘዴዎች ስር የተቀጠሩ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞች ሊገለሉና ችሎታቸው ያነሰ ወይም ዝቅተኛ አምራች ተደርገው ሊታዩ ይችላሉ፤
- ለሥራዎቻቸው አስጊ ናቸው ብለው የሚያስቡ ከሆነ አካል ጉዳተኛ ያልሆኑ ሠራተኞች የተደጓሚ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን የሥራ ስምሪት ሊቀየሙ ይችላሉ፡፡
የገለጻ ማሳያ 92 እንደ ታየው እነዚህ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች እንዴት እንደሚወገዱ ተሳታፊዎችን ይጠይቁ፡፡ መፍትሔው በተሳታፊዎች ካልተገኘ ክፍያው ጊዜያዊ በሚሆንበት ጊዜ የማትጊያ ክፍያው ካቆመ በኋላ አሠሪው ሠራተኛውን ይዞ ለማቆየት ሊገደድ እንደሚችል አጽንኦት ያድርጉ፡፡ የአካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን ችሎታ ለማሳየትና የተዛቡ አመለካከቶችን ለመቅረፍ የመረጃ ዘመቻዎች ሊቀረጹ ይችላሉ፡፡ አካል ጉዳተኛ ያልሆኑ ሠራተኞች ስለ ዘዴው ሊኖራቸው የሚችለውን ድምጸ ተዐቅቦ ለማሸነፍ ለገንዘብ ማትጊያ ዘዴው የሚደረግ የሠራተኛ ማኅበራትን ድጋፍ ደግሞ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በዐውደ ንባቡ ገጽ 55 የቀሩትን ከኔዘርላንድስ፣ ከካናዳና ከአውስትራልያ የተገኙ የሚከተሉትን ምሳሌዎች በማሳየት ይህን ክፍል ይደምድሙ፡፡
«በኔዘርላንድስ አካል ጉዳተኛ ሠራተኛን ቢያንስ ለስድስት ወር አለዚያም በቋሚነት በሚቀጥሩበት ጊዜ «የምደባ በጀት» (Placement Budget) የተባለ ስምምነት የተደረገበት ድጎማ ለአሠሪዎች ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም ከመጀመሪያው ተቀጥረውበት የነበረውን የሥራ መደብ ማከናወን ላቃተው/ላቃታት ሠራተኛ አዲስ የሥራ መደብ ለሚያደላድሉ አሠሪዎች «የመልሶ ድልድል በጀት» (Reallocation Budget) የተባለ ድጎማ ሊሰጥ ይችላል፡፡ በአማራጭ የመልሶ ውህደት ወጪዎች ከምደባ በጀት ወይም ከመልሶ ድልድል በጀት በሚበልጡበት ጊዜ የተመቻቸ የድጎማ አሠራር ለጠየቁ አሠሪዎች የመንግሥት ድጎማዎች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
በካናዳ የሥራ ስምሪት ዋስትና ባለ መብት ሆነው በሥራ ስምሪት መሰናክሎች ምክንያት ሥራ የማግኘት ችግር ያለባቸው ሥራ አጥ ግለሰቦች ከካናዳ የሰው ኃይል ቢሮ ጋር ስምምነት ያደረጉ አሠሪዎችን እንዲያገኙ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ ከአሠሪው ጋር የሚደረገው ስምምነት በ78 ሳምንታት ውስጥ ሊጸድቅ ይችላል፡፡
በአውስትራልያ በክፍቱ የሥራ ገበያ ለአካል ጉዳተኞች የሥራ መደቦች ለሚሰጡ አሠሪዎች የደመወዝ ድጎማ ዘዴ እንደ ማበረታቻ ያገለግላል፡፡ ዘዴው በትንሹ ለ13 ሳምንታት ቢያንስ በቀን የ8 ሰዓት የሥራ ስምሪት በማግኘት የአካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ያቅዳል፡፡»የአካል ጉዳት መድልዎ አልባ ሕግ ውጤታማ እንዲሆን የገንዘብ ማትጊያዎችና ከሥራ ስምሪት ጋር የተያያዘ ድጋፍ አገልግሎቶች ጥምረት መጀመር እንዳለበት እንዲሁም እነዚህን ማትጊያዎችና አገልግሎቶች በተቀናጀና ግልጽ በሆነ መንገድ መስጠት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ያድርጉ፡፡ እነዚህ ድጋፎች ወደ ሥራ የመሄጃ ወጪዎችን በማካካስ፣ ልዩ የማመቻቸት ዓይነቶችን በማድረግ ረገድ ሊከሰቱ ሚችሉ ወጪዎችን ለአሠሪዎች በማወራረድና አካል ጉዳተኞችን በመመልመልና ይዞ በማቆየት ረገድ አሠሪዎችን በማስተባበር አካል ጉዳተኛ ሥራ ፈላጊዎችን ሥራ በማግኘት ረገድ ይረዳሉ፡፡ እነዚህ ማበረታቻዎችና ድጋፎች ውጤታማ የኮታ ዘዴዎችን በመቅረጽ ረገድ ደግሞ ወሳኝ እንደ ሆኑ ያስረዱ፡፡
አማራጭ መልመጃ፡- የዚህ መልመጃ ዓላማ ለአካል ጉዳተኞች እና/ወይም ለአሠሪዎች ልዩ የገንዘብ ማትጊያዎችን የመስጠት ጥቅሞችና ጉዳቶች እንዲመዝኑ ለተሳታፊዎች ዕድሉን ለመስጠት ነው፡፡ ተሳታፊዎቹን በስድስት ቡድኖች ይከፋፍአቸው፣ ለእያንዳንዱም ቡድን አቋም ይመድቡ፡፡
- ለአካል ጉዳተኞች ሥራን ለማበረታታት ከገንዘብ ማትጊያዎች ጋር የተያያዙ አዎንታዊ ጎኖች፡፡
- ለአካል ጉዳተኞች ሥራን ለማበረታታት ከገንዘብ ማትጊያዎች ጋር የተያያዙ አሉታዊ ጎኖች፡፡
- አካል ጉዳትና ተደራሽነት ነክ የሆኑ ወጪዎችን ለመሸፈን ለአሠሪዎች የገንዘብ ማትጊያዎችን ከመስጠት ጋር የተያያዙ አዎንታዊ ጎኖች፡፡
- አካል ጉዳትና ተደራሽነት ነክ የሆኑ ወጪዎችን ለመሸፈን ለአሠሪዎች የገንዘብ ማትጊያዎችን ከመስጠት ጋር የተያያዙ አሉታዊ ጎኖች፡፡
- ለመመልመል፣ ለመቅጠርና ይዞ ለማቆየት ለአሠሪዎች የገንዘብ ማትጊያዎችን ከመስጠት ጋር የተያያዙ አዎንታዊ ጎኖች፡፡
- ለመመልመል፣ ለመቅጠርና ይዞ ለማቆየት ለአሠሪዎች የገንዘብ ማትጊያዎችን ከመስጠት ጋር የተያያዙ አሉታዊ ጎኖች፡፡
የተመደቡበትን አቋም የሚወክል መከራከሪያ መፍጠር እንደሚያስፈልጋቸው ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ እያንዳንዱ ቡድን አቋሙን ለመወሰን 20 ደቂቃ ከዚያም ግኝቶቹን ለማጋራት 10 ደቂቃ ይኖረዋል፡፡
የሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን ማማከከር፡፡
ባለፉት 20 ዓመታት ወደ ሥራው ገበያ የሚገቡት የአካል ጉዳተኛ ግለሰቦች ብዛት እየጨመረ መሄዱን ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ እድገቱ ለሥራ ቦታ መሠረታዊ ድጋፎችን በመስጠት መስኮች የተገቢ የሆኑትን እድገቶች አካትቶአል፡፡ ቅድመ ሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን፣ የሥራ ምደባ አገልግሎቶችና የሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን ጨምሮ ቴክኒካዊ ማማከርና የምክክር የሥራ ስምሪት ድጋፍ መስጠት የሚችሉአቸውን የተለያዩ መልኮች ለማሳየትየገለጻ ማሳያ 93 ይጠቀሙ፡፡የገለጻ ማሳያ 94ን ተጠቅመው ሊገኙ የሚችሉ ቅድመ ሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን ለተሳታፊዎች ይዘርዝሩ፡፡ ሙያዊ ግምት አንድ አካል ጉዳተኛ ያሉትን/ያሏትን ከተወሰኑ የሥራ መደቦች ጋር መስማማት የሚችሉ ልዩ ሙያዎች፣ መለያዎችና ችሎታዎች በማወቅ ረገድ ለመርዳት የታሰበ አገልግሎት ሲሆን ልዩ የድጋፍ ፍላጎቶችና አንድ ግለሰብ በሥራው ገበያ ስኬታማ እንዲሆን ሊፈልጋቸው የሚችሉትን ማመቻቸቶች ለይቶ በማወቅ ረገድ ደግሞ ይረዳል፡፡ በመሠረቱ ሙያዊ ግምት በመፈተን ላይ ላለው ግለሰብ መደበኛ መዐቀፍ ለመፍጠር የሚያገለግል የተወሰነ የስጦታና የሌሎች ሙከራዎች ኃይል ነው፡፡ የሥራ ሙከራዎችና ተግባራዊ ግምት በትክክለኛ ሁኔታዎች በሥራዎች ዙሪያ የሚያተኩሩ በመሆናቸውና ግለሰቡ በአካባቢውና በባህሉ ውስጥ ሥራውን በትክክል በሚያከናውንበት ወቅት ለሚኖረው መስተጋብር በመገመታቸው ይበልጥ በእንቅስቃሴ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ የአንድን ግለሰብ ራስን ችሎ የመንቀሳቀስ እንዲሁም በክንውኑ ወቅት ማመቻቸቶችና ለውጦችን ለመሞከር የላቀ ዕድል የመስጠት ችሎታን በመወሰን ረገድ የተሰበሰበው መረጃ ወሳኝ ሊሆን ይችላል፡፡ የቅድመ ሥራ ስምሪት ሙያዎች ሥልጠና የተወሰነ ሙያን ለመከተል ሊያስፈልጉአቸው የሚችሉትን ሙያዎች እንደይዙ ወይም፣ ይበልጥ በአጠቃላይ፣ መጠይቅ እና/ወይም የሥራ ፍለጋ ችሎታዎችን በማዳበር አማካይነት አካል ጉዳተኛ ግለሰቦችን በመርዳት ዙሪያ ያተኩራል፡፡ አዘውትሮ ሙያዊ የምክር አገልግሎት ቅድመ ሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን አሰባስቦ የሚይዝ «ሙጫ» ነው፣ ምክንያቱም የቅድመ ሥራ ስምሪት ሂደት የግለሰቡን፣ ለእርሱ ወይም ለእርሷ ፍላጎት ተስማሚ የሆኑትን የሥራ አካባቢ ዓይነቶችና በሁለቱ መካከል የሚኖረውን የሥራ መስማማት የተሻለ ግንዛቤ ለማግኘት ቀጣይ ውይይት በመሆኑ ነው፡፡
የገለጻ ማሳያ 95 በመጠቀም የሥራ ምደባን ለመደገፍ ሊኖሩ የሚችሉ የአገልግሎቶችን ስፋት ለተሳታፊዎች ይዘርዝሩ፡፡ የሥራ ልማት የሥራ ምደባ ድርጅቶች በአካባቢያቸው ያለውን የሥራ ገበያና ሊኖሩ የሚችሉ የሥራ ስምሪት ዕድሎችን በማወቅ ረገድ እንዲረዳቸው የሚሰማሩበት ልዩ ተግባር ሲሆን ከሥራው ገበያና ለአካል ጉዳተኛ አመልካቾች የሥራ ዕድሎችን ከመፍጠር ጋር ግንኙነት በመፍጠር ዙሪያ ያተኩራል፡፡ የተለዩ የሥራ ስምሪት ግቦቻቸውን አንዴ ከወሰኑ የሥራ ፍለጋ ድጋፍ ለአካል ጉዳተኛ ግለሰቦች ይሰጣል፡፡ ድጋፉ በሥራ ምደባ ድርጅቱና በግለሰቡ መካከል የሚደረግ የድርድር ሂደት ነው፡፡ ግለሰቡ ራሱን ችሎ ማከናወን የሚችላቸውን የሥራ ፍለጋ ሂደቱ ክፍሎች ለይቶ ማወቅን እንዲሁም የሥራ ዕድሎችን እንደ ማግኘት ያለ ግለሰቡ/ግለሰቧ ሊፈልጉ የሚችሉትን ተጨማሪ ድጋፍ ያካትታል፡፡ የሥራ ማስማማት የሥራ ምደባ ሂደቱ ወሳኝ ክፍል ነው፡፡ ይህ ሂደት ስለ አካል ጉዳተኛ ግለሰቡ የታወቀውን የሙያዊና ተግባራዊ ግምት ክፍል አድርጎ መውሰድና ያንንም ከተወሰነ ሥራና የሥራ አካባቢ እንዲሁም ባህል ትንታኔ ጋር ማጣመርን ያካትታል፡፡ ይህን እርምጃ የግለሰቡ ሙያዎችና ችሎታዎች ሥራውን የት ቦታ ላይ እንደሚመጥኑ ለመወሰን እንደ ማስተካከያ ድርጊት አድርገው ይመልከቱት፡፡ እነዚህ ሙያዎችና ችሎታዎች በማይመጥኑበት ቦታ የሥራ ምደባ ድርጅቱ ተጨማሪ ድጋፎች መሰጠት እንዳለባቸው ያውቃል፡፡ ይህ ክፍተት ለውጤታማ የሥራ ክንውን አስፈላጊ በሆኑት ማመቻቸቶችና ማስማማቶች ዙሪያ አካል ጉዳተኛው ግለሰብና አሠሪው እንዲደራደሩ ድጋፍ መስጠትን ያስከትላል፡፡ አዘውትሮ በዚህ የሥራ ምደባ ሂደት ወቅት የሥራ ምደባ ድርጅቱ ማመቻቸቶችን በማድረግ አለዚያም ከተቻለ ሥራውን ወይም የሥራውን ልዩ ተግባሮች መልሶ በማዋቀር ረገድ ለአሠሪዎች የቴክኒክ ምክር ሊሰጥ ይችላል፡፡
የሥራ ስምሪት አገልግሎቶች የመስጠትን ብዙ ገጽታዎች ለማስረዳት የገለጻ ማሳያ 96 ይጠቀሙ፡፡ በጣም በተለመደ ሁኔታ አንድ አካል ጉዳተኛ ግለሰብ አንዴ ሥራ ላይ ከተመደበ የሥልጠናውን ዓይነትና ግለሰቡ ለልዩ አካል ጉዳቱ ለማመቻቸት ሊፈልጋቸው የሚችለውን ተጨማሪ ድጋፎች በሚመለከት የተወሰነ ስምምነት ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ ከሚቻሉ ማሻሻያዎች ጋር በአሠሪው የሚሰጥ የሥራ ላይ ሥልጠናን፣ እንዲሁም በሥራ ምደባ ድርጅቱ ሊሰጥ የሚችለውን የሥራ አሠልጣኝነትን ያካትታል፡፡ አንድ አካል ጉዳተኛ ግለሰብ አንዴ ከተቀጠረ የሥራ ምደባ ድርጅቱ ለሥራ እድገት፣ ለቀጣይ የሙያ ማማከርና ለችግር መፍታት ድጋፍ ለማድረግ ቀጣይ አገልግሎቶችን መስጠት ሊቀጥል ይችላል፡፡
ውይይት የተደረገባቸው አገልግሎቶችና ድጋፎች በአንድ የሥራ ምደባ ድርጅት ሊሰጡ ወይም ላይሰጡ እንደሚችሉ ለተሳታፊዎች በአጽንኦት በማሳሰብ ይህን ክፍለ ትምህርት ይዝጉ፡፡ የሥራ ስምሪቱን ሂደት ለመደገፍ ሊኖሩ የሚችሉ የቴክኒክ ምክርና የማማከር ድጋፎችን መጠን ከየትኛዎቹ ድርጅቶች እንደሚገኙ ከጅምሩ ማረጋገጥ ወሳኝ ነው፡፡