ማጣቀሻዎችና ምንባቦች
-
McFarlin, D. B., Song, J., & Sonntag, M. (1991). Integrating the disabled into the work force: A survey of fortune 500 company attitudes and practices. Employee Responsibilities and Rights Journal, 4(2), 107-123
አሠሪዎች ለአካል ጉዳተኞች ያላቸውን አመለካከት ለመወሰን ፣ እንዲሁም የአሠሪዎችን የቅጥርና የማመቻቸት አሠራሮች በተጨማሪ ለመዳሰስ በ500 ኩባኒያዎች የተካሄደ የዕድል ቅኝት፡፡ ማጣራቱ ጥቂት መረጃ በሚገኝለት ርእስ ዙሪያ ብርሃን ለማሳረፍ የተደረገ ነበር፡፡
ጽሁፉ በሚከተለው ድረ ገጽ ለግዢ ቀርቦአል፡- http://www.springerlink.com/(1jd1thvzqgwtgam1q11km445)/app/home/contribution.asp?
referrer=parent&backto=issue,2,7;journal,44,57;linkingpublicationresults,1:105548,1 -
Merilainen, A., & Helaakoski, R. (2001). Transport, poverty and disability in developing countries. 1-29.
አካታች ትራንስፖርት በማደግ ላይ ባሉ አገሮች አካል ጉዳተኞችን በሚያካትተው አጠቃላይ ስትራቴጂ ውስጥ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ እንዲህ ያሉት አሠራሮች ትምህርትን ሊያግዱ፣ በሥራው ገበያ መሳተፍን ሊከለክሉና እንዲሁም በጤናና በሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶች መጠቀምን ሊገድቡ የሚችሉ እስከ ሆኑ ድረስ አካል ጉዳተኞችን የሚያገልሉ የትራንስፖርት አሠራሮች አካል ጉዳተኞች ድሆች ይሆናሉ ብለው በደፈናው ያረገግጣሉ፡፡ በአካል ጉዳተኞች ላይ «የገቢ ድህነት» ከመፍጠራቸው ሌላ አግላይ የትራንስፖርት አሠራሮች አካል ጉዳተኞችን ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ዕድሎችን ይነፍጋሉ፡፡ ትራንስፖርትና አካል ጉዳትን አስመልክቶ አካባቢው በሚተነተንበት ጊዜ ሁለት ዋነኛ እይታዎች ሊታዩ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ እይታዎች በተሠራው አካባቢ መጠቀምና ተደራሽነት ናቸው፡፡
በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል http://web.worldbank.org/WBSITE/EXTERNAL/TOPICS/EXTTRANSPORT/EXTTSR/0,,
contentMDK:21268763~menuPK:2970912~pagePK:210058~piPK:210062~theSitePK:463716,00.html -
Barbara Kolucki & Barbara Duncan; Working Together with the Media: A Practical Guide for People with Disabilities; International Labour Office and Rehabilitation International; 1994; Geneva
ይህ እትም «ከመገናኛ ብዙኀን ጋር አብሮ መሥራት፣ ለአካል ጉዳተኞች የተዘጋጀ ተግባራዊ መመሪያ» በሚል ርእስ በ2005 በአማርኛ ተተርጉሞአል፡፡
-
Verick, S. (August 2004). Do financial incentives promote the employment of the disabled? Discussion Paper no. 1256, Institute for the Study of Labor, University of Bonn.
በጀርመን በጥቅምት 1999 ጽኑ አካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ሥራ አጥነት አካል ጉዳት ከሌለበት ሕዝብ ከእጥፍ በላይ ነበር፡፡ ይህን ሁኔታ ለማሻሻል ጽኑ አካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ወደ ሥራ ኃይሉ እንዲገቡና አሠሪዎችም እንዲህ ያሉትን ሠራተኞች እንዲቀጥሩ ማትጊያዎችን ለመጨመር የጽኑ አካል ጉዳተኞች ሕግ ተሻሽሎ ነበር፡፡ በ2003 ዓ/ም የፌዴራል መንግሥቱ በዚህ ማሻሻያ አማካይነት
ወደ 45,000 ግለሰቦች የሚወክሉትን የሥራ አጦቹን ብዛት በ25 ከመቶ ለመቀነስ እንደ ተሳካለት አስታውቆአል፡፡ ይሁንና በዚህ ለጽኑ አካል ጉዳተኞች በሥራ ገበያ ውጤቶች ለማስገኘት በወጣ የማሻሻያ ፖሊሲ ተጽእኖ ላይ የተካሄደ አንድ ግምገማ ይህ ስኬት ግለሰቦቹን ወደ ሥራ ስምሪት በማስገባት የተገኘ እንዳልነበር ያመለክታል፡፡ ከዚህም በላይ የቅርብ ጊዜው የሥራ አጦች ብዛት መባባስ የ2003ቱ ስኬት ጊዜያዊ እንደ ነበረ ያሳያል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ በሕጉ ላይ የተደረጉት የገንዘብ ማትጊያዎች ለውጦች በጽኑ አካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት ላይ የረጅም ጊዜ አዎንታዊ ተጽእኖ እንደ ነበረው ምንም ማስረጃ የለም፡፡በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል
http://opus.zbw-kiel.de/volltexte/2005/2455/pdf/dp1256.pdf -
Walls, R., Hendricks, D., Dowler, D., & Hirsch, A. (2000). Job accommodation resources: Lessons from the global neighborhood. Journal of Rehabilitation, 68(4), 34.
ይህ ጽሁፍ የሥራ ስምሪትን ለማመቻቸት ሊገኙ የሚችሉ ዘዴዎችን፣ የሥራ ስፍራ ማመቻቸት፣ የመረጃ ስርጭት ዓይነቶችን፣ እንዲሁም አካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት በማግኘት ረገድ የሚያጋጥሙአቸውን ነባር እንቅፋቶች ከዓለም አቀፍ እይታ አንፃር ያብራራል፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት አካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በማካተት ረገድ አስደናቂ እርምጃዎች ታይተዋል፡፡ ምንም እንኳ የተለያዩ መንግሥታት የሚለያዩ የሥልጣኔ ደረጃዎችን ቢቀዳጁም ግቦቹ፣ ሂደቶቹና ለሙሉ እንቅስቃሴ የሚያጋጥሙት እንቅፋቶች በዓለም ዙሪያ ተመሳሳይ ናቸው፡፡