የመረጃ መረብ ምንጮች
http://www.usdoj.gov/crt/ada/business.htm
ይህ የአሜሪካውያን የአካል ጉዳተኞች ሕግ የንግድ ድርጅቶች ግንኙነት ድረ ገጽ ስለ ሕጉ የግብር ብድሮች ተደራሽ የመመሪያዎችና የመረጃ ንድፍን ጨምሮ የንግድ ድርጅቶች እንዴት ራሳቸውን ከሕጉ መስፈርቶች ጋር እንደሚያስማሙ ዘዴዎችን ያቀርባል፡፡ ምንም እንኳ ድረ ገጹ የንግድ ድርጅቶችን ለማገልገል የታቀደ ቢሆንም ተመሳሳይ የመመሪያዎች ንድፍ ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞችም ማገልገል ይችላል፡፡
ጃን (JAN) የተባለው ይህ ድረ ገጽ 1) የተለያዩ የሥራ ስፍራ ማመቻቸቶች መፍትሔዎች፤ 2) የአሜሪካውያን የአካል ጉዳተኞች ሕግና አካል ጉዳት ነክ የሆኑ ሌሎች ሕጎችን በሚመለከት የቴክኒክ እርዳታ በመስጠት፤ 3) ለስልክ ደዋዮች የራስን ሥራ ስለ መፍጠር አማራጮች በማስተማር የአካል ጉዳተኞችን ተቀጣሪነት ለማሳደግ የሚሠራ ነፃ የማማከር አገልግሎት ነው፡፡ ድረ ገጹ ለግል አሠሪዎች፣ ለፌዴራል መንግሥት አሠሪዎች፣ ለግዛትና ለአካባቢ መንግሥት አሠሪዎች የተለዩ መግቢያዎችን የሚይዝ ሲሆን በሥራ ቦታ በግል ረዳት አገልግሎቶች ዙሪያ መረጃ ይሰጣል፡፡
ኤብልዳታ የኢንተርኔት «የአጋዥ ቴክኖሎጂ ምንጭ መረጃ» ነው፡፡ ከሰው ሠራሽ አካላት አስከ ሥራ ቦታ መሣሪያ በሚለያዩ ምርቶች የምንጮችና የመረጃ ማእከሎችን ገጽ የሚይዝ ሲሆን ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል ለተወሰኑ አካል ጉዳቶች የድረ ገጽ አድራሻዎች ዝርዝር እንዲሁም ለሥራ ቦታ ምንጮችና ለጠቅላላ የአካል ጉዳት ምንጮች የኢንተርኔት አድራሻዎች የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
http://www.psi.org.uk/publications/DISAB/dissocpol.htm
በኢንተርኔት ላይ የሚገኝ የአካል ጉዳትና የማበራዊ ፖሊሲ መጽሐፍ፣ ከያዛቸው ምዕራፎች ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል «ገቢን ለአካል ጉዳተኞች ቋሚ ማድረግ»፣ «የማኅበራዊ እንክብካቤ አገልግሎቶች ለአካል ጉዳተኞች» እና «የሥራ ስምሪት መሰናክሎችን ማሸነፍ» የሚሉት ይገኛሉ፡፡