የሥልጠና ዝርዝር

5.1 መደበኛ ገለጻ - የመረጃ ሚና

  • የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ስምሪት የሚያሳድጉ ሕጎችን በመተግበርና አዎንታዊ የሥራ ስምሪት ልምዶችን በማበረታታት ረገድ የመረጃ ዘመቻዎች ጠቃሚ ሚና እንደሚጫወቱ ለተሳታፊዎች አጽንኦት በመስጠት ይጀምሩ፡፡ ልዩ መልእክቶችን ለተለዩ አድማጮች ለማድረስና በእነርሱም ላይ ጫና ለማሳደር የታቀዱ ዘመቻዎች በተለይ ጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ከሥራ ሁኔታ የተነሣ ቋሚ አካል ጉዳት ለአጋጠማቸው ሠራተኞች አንዳንድ ጥበቃዎችን ለመስጠት የወጡ ሕጎችና ፖሊሲዎች በነባር ኢንዱስትሪዎችና የሥራ ቦታዎች ዘልቆ የሚደርስ በጣም ልዩ የማዳረስ ዘመቻ ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ ምሳሌ እነዚህ ሠራተኞች ከሥራ ነክ ጉዳት ወይም አደጋ የተነሣ አካል ጉዳተኞች የመሆናቸው አደጋ የሰፋ በመሆኑ ይህ መልእክት ለመላው የሥራ ኃይል እንደሚደርስ ማወቅ ወሳኝ ይሆናል፡፡ ከዚህ ሌላ በኢንዱስትሪ ውስጥ ጉዳት የደረሰባቸውና አካል ጉዳተኛ ሠራተኞች የሚገናኙባቸው የተለመዱ ልዩ ቦታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ መልእክቱ በግልጽ እንደ ተሰራጨ ወይም አንደ ደረሰ ለማረጋገጥ እነዚህ ቦታዎች ማገልገል እንደሚኖርባቸው የተወሰኑ የግንኙነት ነጥቦች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

    ከታች በ«ለ» የተዘረዘረውን አማራጭ መልመጃ ለመሥራት የማይመርጡ ከሆነ የገለጻ ማሳያ 81ን በመጠቀም ለምሳሌ በደንብ ተዘጋጅቶ አሠሪዎችን ዒላማ ያደረገ የመረጃ ዘመቻ የሥራ ቦታ ስብጥር ጥሩ የድርጅት ስሜት የሚፈጥር መልእክት መላክ እንደሚችል ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ስብጥር የአካል ጉዳተኞችን የመሥራት አቅምና ብዙ አሠሪዎች አካል ጉዳተኛ ሠራተኞቻቸውን የላቁና የኩባኒያው ሀብት ሆነው ያገኙበትን እውነታ አጉልቶ በማሳየት ከአካል ጉዳት ጋር የተያያዘ መገለልን ይቀንሳል፡፡ ሌላው ጥሩ የመረጃ ዘመቻ አካል ጉዳተኞች በሥራ ስምሪት ሕግ ስር ስላሉአቸው መብቶች፣ ወይም አካል ጉዳተኛ ሠራተኞች በመብቶቻቸው እንደሚጠቀሙ በማረጋገጥ ረገድ የሠራተኛ ማኅበራት ስላላቸው ሚና የሚያሳውቀው ነው፡፡

    ኩባንያዎች የድርጅት ትምህርት ቤቶችን በመምራት አዘውትሮ ጠቅላላ ማኅበራዊ ኃላፊነት ተብሎ ለሚጠራው ጽንሰ ሃሳብ በይበልጥ መልስ በመስጠት ላይ እንደ ሆኑ ያስረዱ፡፡ ጠቅላላ ማኅበራዊ ኃላፊነት አካል ጉዳተኞችን በመቅጠር፣ ይዞ በማቆየት፣ እንዲሁም እድገት በመስጠት አማካይነት ጨምሮ የጸዳ አካባቢን ለማሳደግ ሆነ ወይም ለሠራተኞች ልጆች የየዕለት እንከክብካቤን ለመስጠት፣ ወይም በሥራ ኃይል ውስጥ ማኅበራዊ ስብጥርን ለማቀድ ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመውሰድ ኩባኒያዎችን የሚያሳድግ ሰፋ ያለ ሃሳብ ነው፡፡ ከተሰባጠሩ የኋላ ዳራዎች የተገኙ ሰዎች እምቅ ኃይል ያላቸው ደንበኞች በመሆናቸው በአሁኑ ጊዜ ኩባኒያዎች በፆታ፣ በዘር፣ በባህል፣ በወሲባዊ ምርጫ፣ ወዘተ. ኅብረተሰባዊ ልዩነቶችን የሚያንጸባርቅ ስብጥር የሥራ ኃይል እየተገነዘቡ ናቸው፡፡

  •  
    አማራጭ መልመጃ፡- ተሳታፊዎቹን በስድስት ቡድኖች ይከፋፍሉአቸው፡፡ እያንዳንዱን ቡድን በሥራ ስምሪት ሂደት እንደ ወሳኝ ባለ ድርሻ (ለምሳሌ አሠሪ፣ አካል ጉዳተኛ ሥራ ፈላጊ፣ እና የሥራ ባልደረቦች) አድርገው ይመድቡአቸው፡፡ አዲስ የወጣ የመድልዎ አልባነት ሕግን ትግበራ ለመደገፍ የታቀደ የመረጃ ግብይት ዘመቻን ጽንሰ ሃሳብ ለማመንጨት እያንዳንዱ ቡድን 30 ደቂቃ እንደሚኖረው ያስረዱ፡፡  የገለጻ ማሳያ 82ን በመጠቀም መድረስ ያለባቸው ልዩ መልእክቶች ለምን አስፈላጊ እንደ ሆኑና የቡድኑ አባላት መልእክታቸው ይኖረዋል ብለው የሚያስቡትን ማንኛውንም የተጠበቀ ውጤት ማረጋገጥ እንደሚኖርባቸው ለእያንዳንዱ ቡድን ያሳውቁ፡፡ የመረጃ ዘመቻውን ከመላው ተሳታፊዎች ጋር ለመጋራት እያንዳንዱ ቡድን የራሱን ሪፖርት አቅራቢ መምረጥ
    ይኖርበታል፡፡ ሪፖርቱን እንዲያቀርብና በእያንዳንዱም ጉዳይ ዙሪያ ጥያቄዎችና መልሶች ለማስከተል ለየቡድኑ አሥር ደቂቃ ይፍቀዱ፡፡

    እንደ ፖስተሮች፣ ኪዮስኮች፣ ተጓዥ ተውኔቶች፣ ተከታታይ የሬድዮ ድራማዎች፣ ወዘተ. የመሳሰሉት ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቁ የመረጃ ዘመቻዎች አማራጮችን እንዲያስቡ ተሳታፊዎችን ያበረታቱ፡፡ ደግሞም መረጃው ሰፋ ላለ የአካል ጉዳት ቡድኖችና ባለ ድርሻዎች እንደሚደርስ ለማረጋገጥ መልእክቱ ሊይዛቸው የሚችለውን ይዘቶች ለማረጋገጥ ምን እርምጃዎችን ሊወስዱ እንደሚችሉ ተሳታፊዎችን ይጠይቁ፡፡

  • አጠቃላይ የመረጃ ዘመቻን ለማሳደግ የሚኖሩ አማራጮችን ዝርዝር እንዲፈጥሩ ተሳታፊዎችን ይጠይቁ፡፡ መልሶቹ ሬድዮን፣ ጋዜጦችና የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎችን፣ በሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች ላይ የሚለጠፉ ጽሁፎችን፣ ወዘተ. ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡ መልሶቻቸውን በተገላጭ ወረቀቱ ላይ ይጻፉ፡፡
  • በትንሹ አቅጣጫ ይለውጡና በበለጠ ታቀደውን የመረጃ ዘመቻ ለማሳደግ ሊያገለግሉ የሚችሉ የአማራጮች ዝርዝር በመፍጠር ረገድ ተሳታፊዎች እንዲረድዎት ይጠይቁአቸው፡፡ ዕቅዱ መልእክቱን በተለይ ለአሠሪዎች ወይም ለአካል ጉዳተኞች ወይም ደግሞ ለሠራተኛ ማኅበራት ለማዳረስ ቢሆንስ? ነባር አቀራረቦች ልክ ሆነው ይቆያሉ ወይስ የተገኙት አዲስ ስልቶች መስተካከል ያስፈልጋቸዋል?

  • በደንብ የታቀዱ የመረጃ ዘመቻዎች ወሳኝ እንደ ሆኑና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚመለከታቸውን የተለያዩ ባለ ድርሻዎች ልዩ ፍላጎቶች የሚያሟሉ ሆነው መቀረጽ እንዳለባቸው ለተሳታፊዎች በማሳሰብ ይህን የገለጻ ክፍል ይዝጉ፡፡ ከአጠቃላይ የመረጃ ዘመቻዎች በተጨማሪ ለባለ ድርሻዎች የታቀዱ መረጃና በቴክኒካዊ ማስማማቶች ዙሪያ የማማከር አገልግሎቶች፣ የሥራ ምደባ፣ የገንዘብ ማትጊያዎችና ሌሎች አስፈላጊ ሊሆኑ ለሚችሉ የሥራ ስምሪት ድጋፎችን ለመሳሰሉት በዕቅድ ደረጃ ላይ እያለ ደንብ መቀረጽ እንደሚኖርበት አጽንኦት ይስጡ፡፡ ይህ በሚቀጥለው ክፍለ ትምህርት በስፋት እንደሚዳሰስ ይግለጹ፡፡

    ውጤታማ የመረጃ ዘመቻ ምሳሌ

    «በፖላንድ ኢንቴግራስያ የተባለው ድርጅት የደረሰበትን አደጋ ተከተሎ እጆቹና እግሮቹ በመጎዳታቸው ፈጽሞ መሥራት እንደማይችል በዶክተሮች በተነገረው በፕዮትር ፓቭሎቭስኪ ከ20 ዓመት በፊት የተቋቋመ ነበር፡፡  ፕዮትር አሁን አርባ ሠራተኞች ያሉት በአንጸባራቂ ወረቀት የሚታተም መጽሔት የሚያዘጋጅ ድርጅት የሚያካሂድ ሲሆን በ90 ገጾች የሚታተመውም መጽሔት ከ15,000 በላይ በሆኑ ቅጂዎች በመዘጋጀት ከዚህ ዓይነቶቹ የፖላንድ መጽሔቶች ከፍተኛውን ስርጭት ይዞአል፡፡ ሥራ እንዴት እንደሚገኝ በመሳሰሉ ሰፊ ምርጫ ባላቸው ርእሶች ዙሪያ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ መረጃ የሚያቀርበው መጽሔቱ የዚህ ዘርፈ ብዙ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አንድ ክፍል ነው፡፡ ኢንቴግራስያ የሕዝብ አመለካከቶችን ለመለወጥ፣ ከአካል ጉዳት ጋር የተያያዙ የተዛቡ እምነቶችን ለማጥፋት፣ እንዲሁም የአካል ጉዳተኞችን ችሎታዎች በአጽንኦት ለማሳየት የትምህርት ዘመቻዎችን ያካሄዳል፡፡ ከብዙዎቹ ሌሎች እንቅስቃሴዎች መካከል የሥልጠና ኮርሶችን ያካሄዳል፣ በመንግሥት ቴሌቪዥን የራሱ ፕሮግራም አለው፣ ሌሎች የሬድዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን አብሮ ያዘጋጃል እንዲሁም የአካል ጉዳተኛ ግለሰቦችን መረጃዎች ይይዛል፡፡ ከእንቅፋት ነፃ የሆነ ጉዞን በማሳደግ ረገድ ከስኬታማ ዘመቻዎቹ አንዱ በፖላንድኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የታተሙ ስለ ዋርሶና ካርኮቭ ከተሞች ሁለት የቦታዎች ማሳያ መጻሕፍትን አስገኝቶአል፡፡ በትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲዎች በሚደረጉ ንግግሮች አማካይነት ተማሪዎችን ለማንቃት ይሠራል፡፡ «ከእንቅፋቶች ነፃ የሆኑ መድኃኒት ቤቶች» እና «ከእንቅፋቶች ነፃ የሆኑ ሆቴሎች» በሚሉ ርእሶች ስር ውድድሮች እንዲዘጋጁ በመርዳት ለተለያዩ ድርጅቶች የተሻለ ተደራሽነትን የሚያሳድግ ሲሆን እነዚህን ውድድሮች ለማስፋፋት ከሠራተኞች ማኅበራት ጋር አብሮ ይሠራል፡፡»