የሥልጠና ዝርዝር
አጀማመር፡- ዝግጅት
- ሴሚናሩ ከመጀመሩ ጊዜ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በፊት የሥልጠናውን አካባቢ ያዘጋጁ፡፡
- የሥልጠናው ጽሁፎች ቅጂዎች መታደላቸውን ያረጋግጡ፡፡
- ጥቅም ላይ ለመዋል ዝግጁ መሆኑን ለማረጋገጥ የድምጽና ምስል መሣሪያውን ያስተካክሉና ይሞክሩት፡፡ ተሳታፊዎች እየገቡ ሳለ ስክሪኑን አብርተው ይተዉት፡፡
የገለጻ ማሳያ 1 - ሦስት የፖስተር/የተገላጭ ወረቀቶች በግድግዳ ላይ ይስቀሉና በመጀመሪያው ከላይ «መሠረታዊ ደንቦች»፣ ቀጥሎ «የመማር ዓላማዎች»፣ በሦስተኛው ደግሞ «የማቆሚያ ቦታ» ብለው ይጻፉ፡፡
- ለኮርስ ተሳታፊዎች አቀባበል ያድርጉ፣ ሴሚናሩንም በጊዜው ይጀምሩ፡፡