የሥልጠናና የማስተማር ዘዴዎች

እንደ ውስብስብ ሰብአዊ ፍጡራን ስሜታዊ፣ አእምሮዊ አንዲሁም ማኅበራዊ ጥምር መለያዎችን ወደ መማር አካባቢው እናመጣለን፡፡ ስብጥር የኮርስ ተሳታፊዎችን ለመቅረብና የተለያዩ የመማር ዓይነቶችን ለማመቻቸት መንገዱ የተለያዩ ትምህርታዊ ቴክኒኮች የሚከናወን ነው፡፡ ይህን ለማድረግ አስተማሪው አስቀድሞ በመሳተፍ ላይ ያሉትን ሰዎች ልዩ የመረጃ ፍላጎት፣ ይህን የሚፈልጉበት ቅደም ተከተል፣ እንዲሁም መማርን ለማሳደግ መረጃውና ትምህርቱ ምን መልክ እንደሚይዝ ማወቅ አለበት፡፡ ዋና አሠልኙ፡-

  • ተገቢ አረባብና ቃና በመጠቀም ቀላል የሆነ ቋንቋ ይጠቀማሉ በግልጽነትም ይናገራሉ፣
  • የፍሬ ነገር መስካቸውን ያውቃሉ፣
  • የመማር ልምዱን ለማበልጸግ አብዛኛው የማሠልጠን ሥራቸውን በግል ልምዶች ላይ ይመሠርታሉ፣
  • ብዛት ያላቸውን የማስተማር ዓይነቶችን የሚጠቀሙ ሲሆን የተሳታፊን ትኩረት ለመጠበቅ አጠቃቀማቸውን ያስተካክላሉ፣
  • እንደ ተጠየቀውና እንደ ተፈለገው ሥልጠናን ያመቻቻሉ፣
  • የተራቀቀ የድምጽና ምስል (ኦዲዮ-ቪዥዋል) ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ቴክኒካዊ ሙያዎች አላቸው፣
  • የሥልጠናውን ተሳታፊዎች የመማር ዓይነቶች ስብጥር ይገነዘባሉ፣
  • በበራሪ ወረቀቱ ከተጠቀሰው ባሻገር ተሳታፊዎቹ በተለይ ለመማር የሚፈልጉትን ለመለካት በሥልጠናው በቀዳሚ ደረጃ የመማር ውል ይፈጥራሉ፣
  • ተሳታፊዎችን ወደ ውይይት ለመሳብ ችሎታ አላቸው፣
  • ውይይቱን ወደ ፍጻሜ ለማምጣት ችሎታ አላቸው፣
  • ራሳቸውን የሚያሞካሹ አይደሉም ለኮርስ ተሳታፊዎችም በቀላሉ ይገኛሉ፣
  • በተሳታፊዎች መካከል መጋራትንና የእርስበርስ ግንኙነትን ያበረታታሉ፣
  • ተሳታፊዎች ወደ ትምህርት አካባቢ የሚያመጡአቸውን እውቀትና ሙያዎች ያውቃሉ አክብሮትም ይሰጣሉ፣
  • ትምህርቱን መቆጣጠርና ሂደቱን ጠብቆ እንዲሄድ ማድረግ ይችላሉ፣
  • ሃሳቦችን፣ የግል እምነቶችና ልምዶች መጋራትን ለማስቻል አስተማማኝና የማያሰጋ የትምህርት አካባቢ ይፈጥራሉ፡፡

መረጃው የሚሰጥበት ቅርጽ እርስዎ እንደሚሰጡት ነገር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አሠልጣኙ ዋነኛውን የአንድ መንገድ ግንኙነት በመጠቀም አዲስ መረጃ በሚሰጥበት ሁኔታ የፖሊሲ ለውጥ በማስገኘት ረገድ አነስተኛ ልምድ ያላቸው ተሟጋቾች ይበልጥ የተለመደውን በማስተማር ላይ የተመሠረተ አቀራረብ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ከፍተኛ እውቀት ኖሮአቸው ከመሠረታዊ መረጃ ጋር በመጠኑ ትውውቅ ያላቸው የኮርስ ተሳታፊዎች አሠልጣኙ አንድ ትምህርት የሚሰጥበትን ግን ለመንታ መንገድ ግንኙነት አልፎ አልፎ ዕድል የሚያስቀምጥበትንና በተለዩ ዓላማዎች ላይ የሚያተኩር ውይይት የሚያቅድበትን ይበልጥ የተመዛዘነ የትምህርት አሰጣጥ አቀራረብ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በመጨረሻ ችሎታዎቻቸውን ለማጣራት የሚፈልጉ በአንጻራዊ መልኩ ልምዱ ያላቸው ተሳታፊዎች በቡድን ውይይትና በመልመጃዎች፣ እንዲሁም ችሎታዎቻቸውን በመፈተንና ስል በማድረግ ዕድሎች ላይ የተመሠረተውን ተማሪ ተኮር አቀራረብ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በየትኛው ጊዜ የትኛውን አቀራረብ መጠቀም እንደሚገባ በማወቅ ረገድ የሠለጠኑ መሆን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ሰንጠረዦች አንዳንድ የተለመዱ አቀራረቦችን፣ እያንዳንዱ ለማሳካት የሚያስቀምጠውን ዓላማ፣ እንዲሁም መወገድ ያለባቸውን እንቅፋቶች ያሳያሉ፡፡

ምን እንደ ሆነ የሚያሳካው ግብ ልብ የሚባሉ ነጥቦች/ አካል ጉዳት ነክ
ገለጻ    

ብዙ ተሳትፎ ሳያስፈልግ በኮርስ ተሳታፊዎች በኩል በጥያቄዎችና በውይይት መልክ የሚደረግ ንግግር፡፡

ከብዛታቸው የተነሣ የተሳታፊዎች ንቁ ተሳትፎ የማይቻል በሆነበት ቦታ ለብዙ አድማጮች ምቹ የሆነ፡፡ መተላለፍ ያለበት መረጃ - ግልጽ የቃላት አመራረጡም ቢሆን - አስቀድሞ በትክክል የሠራ ሊሆን ይችላል፡፡

በሠልጣኞቹ በኩል የሚከሰተው የተሳትፎ ጉድለት ሙሉውን፣ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ፣ ሙሉ በሙሉ ካልታወቀና ካልተስተዋለ ጥቅሙ እንደሚጠፋ ያመለክታል፡፡

የባህርይና አመለካከት ለውጥ በማምጣት ረገድ ውሱን ዋጋ ያለው መሆን፡፡

ልምምድ ለሚጠይቁ የማስተማር ሙያዎች ብቁ አለመሆን፡፡

መስማት ለተሳናቸው ወይም የመስማት እክል ላለባቸው የኮርስ ተታሳታፊዎች አስተርጓሚ ወይም ሌሎች ማመቻቸቶች እንደ ተሰጡ ያረጋግጡ፡፡ ይህ እንደ አሠልጣኝ እርስዎ ለሚያስተምሩበት ፍጥነት፣ አስተርጓሚዎችንም አስመልክቶ በውይይቱ ሂደት ውስጥ እረፍቶችን እንደሚፈቅዱ ጥንቃቄ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ደግሞም በገለጻው ሂደት ከተሳታፊዎች የሚቀርቡ ጥያቄዎች በደንብ እንዲሰሙና መልሰው እንደ ተብራሩ ማረጋገጥ ይኖርብዎታል፡፡

ዓይነ ስውር ወይም የማየት እክል ላለባቸው ተሳታፊዎች ንግግር በሚደረግበት ጊዜ ማየት የሚችሉት ተሳታፊዎች የሚመለከቱትን በአእምሮአቸው መያዝ እንዲችሉ የሚታዩ ምስሎች ጥቅም ላይ ከዋሉ በጥሩ ሁኔታ መብራራታቸው አስፈላጊ ነው፡፡

ተሳታፊዎቹ የከንፈር እንቅስቀሴን በማየት የሚረዱ (የከንፈር አንባቢዎች) ከሆኑ አሠልጣኙ ክፍሉ በበቂ ሁኔታ ብርሃን እንዳገኘና ከንፈሮቻቸውን ከከንፈር አንባቢው እይታ እንደማይጋርዱ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ አሠልጣኞች አዘውትረው ይረሱና አጆቻቸውን አፋቸው ላይ ያደርጋሉ ወይም ምናልባት ከዕቃ ወይም የተሳታፊዎችን እይታ በሚጋረርድ ባለ ድምጽ ማጉያ መድረክ በስተኋላ ይቆማሉ፡፡

በንግግር ላይ የተመሠረተ ይዘት ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ ሌላው ጥንቃቄ የሚደረግበት ጉዳይ ግለሰቦች ስብጥር የመማር ዘዴዎች እንዳሉአቸው ማረጋገጥ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች መረጃን በመስማት በተሻለ ሁኔታ የሚቀበሉ ሲሆኑ ሌሎች ግን ይህን ፈታኝ ሆኖ ሲያገኙት እየተባለ ያለውን ለመሞከር ወይም መልሶ እንዲብራራላቸው ዕድሎችን ይፈልጉ ይሆናል፡፡ እርስዎ ሁሉንም የመማር ዘዴዎች የሚያስተናግዱ ዕድሎችን ለመስጠትዎ እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

ምን እንደ ሆነ የሚያሳካው ግብ ልብ የሚባሉ ነጥቦች/ አካል ጉዳት ነክ
ውይይት    

በአሠልጣኙና በኮርስ ተሳታፊዎች መካከል በአንድ የተለየ ርእስ ዙሪያ በነፃ ስሜት እውቀት፣ ሃሳቦችና አስተያየቶች መለዋወጥ፡፡

የመረጃ አጠቃቀም የአስተያየት ጉዳይ በሆነበት ቦታ አመቺ የሆነ፡፡ ደግሞም በአመለካከቶች ዙሪያ ማግባባት እንዲደረግ ወይም እንዲለወጡ በሚፈለግበት ጊዜ ጠቃሚ የሆነ፡፡ በንግግር ወቅት አመለካከታቸው መለወጥ እንደሚኖርበት ተነግሮአቸው ከነበረው ይልቅ የኮርስ ተሳታፊዎች ከውይይት በኋላ አመለካከቶቻቸውን የመለወጣቸው ዕድል የበለጠ ነው፡፡ ደግሞም የኮርስ ተሳታፊዎች የተማሩትን እውቀት ሊጠቀሙ ስለሚችሉበት መንገድ አስተያየት ለማግኘት አመቺ የሆነ፡፡

የኮርስ ተሳታፊዎቹ ከርእሰ ጉዳዩ ሊወጡና በጠቃሚ መልኩ ሳይወያዩበት ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ መላው ክፍለ ጊዜ የደበዘዘና ትኩረት ያተሰጠው ሊሆን ይችላል፡፡ ለውጥን ለመቀበል ዝግጁ ከመሆን ይልቅ የኮርስ ተሳታፊዎች በአመለካከቶቻቸው የጸኑ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ይህ አቀራረብ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ ዓይነ ስውራን ወይም የማየት እክል ያባለቸው ተሳታፊዎች በመናገር ላይ ያሉትን ግለሰቦች ላያዩ እንደሚችሉ ልብ ማለቱ ወሳኝ ነገር ነው፤ ስለዚህ መናገር ከመጀመር አስቀድሞ ራስን ማስተዋወቅ ለማንኛውም ሰው ጥሩ ልምድ ነው፡፡

መስማት የተሳናቸውንና የመስማት እክል ያለባውን ለመርዳት አስተርጓሚዎች በሚኖሩበት ጊዜ ውይይቱ በአስተርጓሚዎቹ እንዲሰማና መተላለፍ እንዲችል በውይይቱ ውስጥ የገቡት ግለሰበሶች በበቂ ሁኔታ ጮኽ ብለው እንሚናገሩ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡

በውይይቱ የሚካፈሉት ተሳታፊዎች ሁልጊዜ የከንፈር እንቅስቃሴን በሚያነብበው ሰው እይታ ውስጥ ስለማይቆዩ ይህ አቀራረብ የከንፈር እንቅስቃሴ አንባቢዎች ሊሆኑ ለሚችሉ ተሳታፊዎች የተለየ ፈታኝ ሁኔታን ይፈጥርባቸዋል፡፡

በእነዚህ ሁኔታዎች ስር ይህን አቀራረብ በሚጠቀሙበት ጊዜ ክፍሉ በቂ ብርሃን እንደሚያገኝና ጥያቄቴዎች የሚጠይቁት ሆኑ ወይም በውይይቱ ውስጥ የገቡት ሰዎች በቀላሉ ሊታዩ ወደሚችሉበት የክፍሉ መካከለኛ ቦታ እንደ መጡ ያረገግጡ፡፡

አድማጮችዎ የተሰባጠሩ እንደ መሆናቸው መጠን የቃላት ማሳጠሪያዎችና የጥበብ ቃላት በሁሉም ሰዎች ላይታወቁ ይችላሉ፡፡ ተሳታፊዎች የቃላት ማሳጠሪያዎችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡና፣ መጠቀም ያለባቸውም ከሆነ፣ ምንን እንደሚወክሉ እንዲያብራሩ ተሳታፊዎችን ያበረታቱ፡፡

ይህን አቀራረብ በሚጠቀሙበት ጊዜ አድማጮችዎ ለሚያደርጉት ቃል አልባ ግንኙነት ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡ ውይይቶች አዘውትረው ግትርና መላውን ክፍል የማያሳትፉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ውይይት ሁሉንም የኮርስ ተሳታፊዎች እንደሚያካትት ያረጋግጡ፡፡

ግለሰቦች በአስተርጓሚ የሚጠቀሙ ከሆነ ቀጣይ በሆነው ውይይት መካፈል እንዲችሉ አስተርጓሚዎቹ ስለ ተሳታፊው እንዲናገሩ ዕድል እንደ ተሰጣቸው ያረጋግጡ፡፡

ምን እንደ ሆነ የሚያሳካው ግብ ልብ የሚባሉ ነጥቦች/ አካል ጉዳት ነክ
ገጸ ባህርይ መጫወት    

በሥልጠናው ሁኔታ ውስጥ የኮርስ ተሳታፊዎች በሥራቸው ያላቸውን ገጸ ባህርይ እንዲተውኑ ይጠየቃሉ፡፡ ይህ በዋነኛነት ሁኔታዎችን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ያገለግላል፡፡

ርእሱ በሥልጠናው ሁኔታ ውስጥ ላለ ትክክለኛ የሕይወት ልምድ ለኮርሱ ተሳታፊዎች ጠቃሚ መሆን በሚችልበት ቦታ አመቺ የሆነ፡፡ የኮርሱ ተሳታፊዎች «ጥበቃ በሚደረግለት» የኮርስ ሁኔታ ውስጥ ከባልደረቦቻቸው የባለሙያ ምክር፣ ትችትና አስተያየቶችን መቀበልና መሞከር ይችላሉ፡፡ ይህ ልበ ሙሉነትን እንዲሁም መመሪያዎችን ይሰጣል፡፡ የኮርስ ተሳታፊዎቹ የትክክለኛ ሕይወት ጫናዎችን መልመድ ይችላሉ፡፡

የኮርስ ተሳታፊዎች በገጸ ባህርይ ጨዋታ ለመግባት እምቢተኛ ሊሆኑ ሲችሉ አንዳንድ የተሳታፊዎች ቡድኖች የገጸ ባህርይ ጨዋታውን እንደ ጠንካራ የመማር ዘዴ ላይቆጥሩት ይችላሉ፡፡ ከላይ ከተገለጸው ጉልህ ሁኔታ ባሻገር አንዳንድ የአካል ጉዳት ዓይነቶች ያሉባቸው ግለሰቦች በዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ ፈጽመው ላይገቡ እንደሚችሉ ልብ ያድርጉ፡፡ ለምሳሌ፡-

  • የከንፈር እንቅስቃሴን በማንበብ፣ በአስተርጓሚ አገልግሎቶች ወይም በትክክለኛ ጊዜ ቅጂ (Real Time Transcription) የሚጠቀሙ መስማት የተሳናቸው ወይም የመስማት ችግር ያለባቸው ግለሰቦች እነዚህ ድጋፎች አንዲታሰቡላቸው ይፈልጋሉ፤
  • ዓይነ ስውራን የሆኑ ግለሰቦች የሚጠቀሙበት ስፍራ እንዴት እንደ ተቀመጠና በገጸ ባህርይ ጨዋታው ውስጥ ላሉት ሌሎች ግለሰቦች የሚኖራቸውን የቅርበት ስፍራ በአእምሮአዊ እይታ ለማወቅ ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ ሊፈልጉ ይችላሉ፤
  • አንዳንድ የጭንቀት ቀውሶች ወይም የአእምሮ ጤንነት እክሎች ያሉባቸው ግለሰቦች እንዲህ ያሉትን የእንቅስቃሴ ዓይነቶች በጣም አስቸጋሪ ሆነው ያገኙአቸዋል፡፡

የገጸ ባህርይ ተጫዋቾቹ እንዲጠቀሙባቸው ትዕይንቶች የተሰጡ ከሆነ እርስዎ በቅድሚያ እንዲዘጋጁና እንዲሁም ልዩ ማመቻቸትን በሚጠይቀውና ለድርጊቱ ፈቃደኛ በሆነው ግለሰብ እንዳያፍሩ ትዕይንቶቹ በአማራጭ ይዘቶች መዘጋጀታቸውን ያረጋግጡ፡፡ ለምሳሌ የማየት እክል ያለበት ግለሰብ ጉልሀ እትም ይፈልጋል፡፡

እውነታው አንዳንድ የአካል ጉዳት ዓይነቶች ያሉባቸውም ሆኑ ወይም የሌሉባቸው ግለሰቦች የገጸ ባህርይ ጨዋታ እንቅስቃሴዎችን እጅግ አሰልቺና ጭንቀትን የሚፈጥሩ ሆነው ሊያገኘአቸው መቻላቸው ነው፡፡ እርስዎ ለአድማጮችዎ ሁልጊዜ ጥንቁቅ መሆን ሲኖርብዎት ይህን አቀራረብ በሚጠቀሙበት ጊዜ ምናልባት «መድረክ ላይ መውጣት» የሚያስደስታቸውን ፈቃደኞች ይፈልጉ፡፡

ምን እንደ ሆነ የሚያሳካው ግብ ልብ የሚባሉ ነጥቦች/ አካል ጉዳት ነክ
ጉዳየ ጥናት    

የኮርስ ተሳታፊዎቹ የአንድን ድርጊት ታሪክ ወይም ሁኔታዎች አግባብነት ባላቸው ዝርዝሮች ይመረምራሉ፡፡ ጉዳየ ጥናቶች በሁለት ፈርጆች ይመደባሉ፣ እነርሱም፡- የኮርስ ተሳታፊዎቹ የአንድ የተለየ ችግር መንስኤን የሚመረምሩባቸውና፣ እንዲሁም፣ የኮርስ ተሳታፊዎቹ አንድን የተለየ ችግር ለመፍፈታት የሚያቀዱባቸው ናቸው፡፡

ከትክክለኛው ድርጊት ጫናዎች ነፃ ሆኖ አንድ ዓላማ ችግሩን ወይም ሁኔታዎችን በሚመለከትበት ቦታ አመቺ የሆነ፡፡ ይህ የሃሳቦችን ልውውጥና የኮርስ ተሳታፊዎቹ በሥራ ሁኔታው ለሚገጥሙአቸው ችግሮች የሚቻሉ መፍትሔዎችን እንዲመልከቱ ዕድሎችን ይሰጣል፡፡

የኮርስ ተሳታፊዎች ለትክክለኛው የሥራ ሁኔታ የተሳሳተ ግምት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በሥልጠናው ሁኔታ የተሰጡት ውሳኔዎች በቦታው በትክክለኛው ሁኔታ መደረግ ከሚኖርባቸው የተለዩ እንደ ሆኑ መገንዘብ ያቅታቸዋል፡፡

በሥልጠና አካባቢው ያለ ማንኛውም ሰው ሁልጊዜ የተለዩ ትዕይንቶችን ለመመርመር እና/ወይም ቀድሞ ለማወቅ በትክክል ዝግጁ አይሆንም፡፡ በእነዚህ ምክንያቶች ሙያዎች በቡድኖች ዘንድ በደንብ በሚከፋፈሉበት መንገድ ግለሰቦችን በጥንድ ወይም በቡድን እንደሚከፋፍሉ ያረጋግጡ፡፡

ከላይ ከተገለጸው ጉልህ ሁኔታ ባሻገር አንዳንድ የአካል ጉዳት ዓይነቶች ያሉባቸው ግለሰቦች በዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ ፈጽመው ላይገቡ እንደሚችሉ ልብ ያድርጉ፡፡ ለምሳሌ፡-

  • የከንፈር እንቅስቃሴን በማንበብ የሚጠቀሙ መስማት የተሳናቸው ወይም የመስማት ችግር ያለባቸው ግለሰቦች፣ የአስተርጓሚ አገልግሎቶች ወይም ትክክለኛ ጊዜ ቅጂ (Real Time Transcription) ድጋፎች አንዲታሰቡላቸው ይፈልጋሉ፤
  • ዓይነ ስውራን የሆኑ ግለሰቦች ልምምዱ ውሰጥ ለመግባትና ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ድጋፍ ሊፈልጉ ይችላሉ፤
  • አንዳንድ የጭንቀት ቀውሶች ወይም የአእምሮ ጤንነት እክሎች ያሉባቸው ግለሰቦች እነዚህ ዓይነቶቹን የእንቅስቃሴዎች በጣም አስቸጋሪ ሆነው ያገኙአቸዋል፡፡

የጉዳየ ጥናት ትዕይንቶች የተሰጡ ከሆነ እርስዎ አስቀድመው በደንብ እንዲዘጋጁ ትዕይንቶቹ በአማራጭ ይዘቶች እንደ ተዘጋጁ ያረጋግጡ፡፡

እውነታው አንዳንድ የአካል ጉዳት ዓይነቶች ያሉባቸውም ሆኑ ወይም የሌሉባቸው ግለሰቦች በቡድን መሥራት ባለባቸው ቦታ የጉዳየ ጥናት ሁኔታዎችን እጅግ አሰልቺና ጭንቀትን የሚፈጥሩ ሆነው ሊያገኘአቸው መቻላቸው ነው፡፡

ምን እንደ ሆነ የሚያሳካው ግብ ልብ የሚባሉ ነጥቦች/ አካል ጉዳት ነክ
መልመጃ    

በአሠልጣኞች የተቀመጡትን
መመሪያዎች ተከትሎ የኮርስ ተሳታፊዎችን ወደ ተፈለገው ውጤት የሚመራ አንድ
የተለየ ተግባር እንዲያከናውኑ ይጠየቃሉ፡፡
ይህ አዘውትሮ ከመልመጃው በፊት የተገኘው እውቀት፣ ልምምድ ወይም ሙከራ ነው፡፡ መልመጃዎች ተጨማሪ መረጃ ወይም አዳዲስ ሃሳቦች ከመተዋወቃቸው በፊት የኮርስ ተሳታፊዎችን ነባር እውቀት ወይም ሃሳቦች ለማወቅ ሊጠቅሙ ይችላሉ፡፡ መልመጃዎች ለግለሰቦች ወይም ለቡድኖች ሊቀረጹ ይችላሉ፡፡

ወደ ተፈለገው ግብ ለመድረስ ከሚደረግ የተለየ ምሳሌ
ወይም መመሪያ ቀጥሎ የኮርስ ተሳታፊዎቹ መለማመድ በሚፈልጉበት ቦታ ለማንኛውም ሁኔታ አመቺ የሆነ፡፡ የኮርስ ተሳታፊዎቹ እስከ ተወሰነ ደረጃ በራሳቸው የሚመሩ ናቸው፤ ይህም በከፍተኛ ደረጃ ንቁ የመማር ዓይነት ነው፡፡ ተሳታፊው ምን ያህል እንደ ገባው ለማወቅ በመደበኛ ፈተኛዎች ፋንታ መልመጃዎች አዘውትረው ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ይህ ዘዴ ሃሳብ አመንጪ ለሆነው አሠልጣኝ ሰፊ ወሰን ይሰጠዋል፡፡

መልመጃው ተጨባጭና የሚጠበቀውም ውጤት በሁሉም የኮርስ ተሳታፊዎች ሊደረስበት የሚችል መሆን አለበት፣ አለበለዚያ እምነት ያጡና ተስፋ መቁረጥ ያጋጥማቸዋል፡፡

አንዳንድ የአካል ጉዳት ዓይነቶች ያሉባቸው ግለሰቦች በዚህ ዓይነቱ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ለመግባት ተጨማሪ ድጋፍ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ መስማት የተሳናቸው ወይም የከንፈር እንቅስቃሴን የሚያነብቡ የመስማት ችግር ያለባው ግለሰቦች፣ የአስተርጓሚ አገልግሎቶች፣ ወይም የትክክለኛ ጊዜ ቅጂዎች (Real Time Transcription) ድጋፎች አንዲታሰቡላቸው ይፈልጋሉ፤ ዓይነ ስውራን ግለሰቦች በመልመጃው ለመግባትና ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡

እርስዎ በቅድሚያ ዝግጁ እንዲሆኑ መልመጃዎችና የጥያቄ ወረቀቶች የተሰጡ ከሆነ በአማራጭ ይዘቶች መቅረባቸውን ያረጋግጡ፡፡

እንደ አስተማሪ ጥንቃቄ የሚያደርጉበት መስክ ስለ መልመጃው ማብራሪያ ለመጠየቅ የሚያቅዱበት መንገድ ነው፡፡ አንዳንድ ግለሰቦች ለክፍል እንዲያቀርቡ ወይም ግኝቶቻቸውን እንዲያሳውቁ በሚጠየቁበት ጊዜ ሁኔታዎችን እጅግ አሰልቺና ትምህርትን በሚገታ መልኩ ጭንቀትን የሚፈጥሩ ሆነው ያገኙአቸዋል፡፡

ምን እንደ ሆነ የሚያሳካው ግብ ልብ የሚባሉ ነጥቦች/ አካል ጉዳት ነክ
የአጠቀቀም ፕሮጀክት    

ከመልመጃ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ግን ተነሣሽነትና የፈጠራ ሃሳቦችን ለማሳየት ለኮርስ ተሳታፊው ይበልጥ የላቀ ዕድል የሚሰጥ፡፡ አሠልጣኙ ልዩ የሆነውን ተግባር ያስቀምጣል፣ ነገር ግን ዓላማዎቹን ለማሳካት የሚከተሉአቸውን መስመሮች መወሰን ለተሳታፊዎቹ የተተወ ይሆናል፡፡

እንደ መልመጃዎች ሁሉ ፕሮጀክቶች ለግለሰቦች ወይም ለቡድኖች ሊዘጋጁ ይችላሉ፡፡

ተነሣሽነትና ፈጣሪነት ማነቃቃትና ሙከራ በሚፈልጉበት ቦታ አመቺ የሆነ፡፡ ፕሮጀክቶች በኮርስ ተሳታፊዎች የግል መለያዎች፣ እንዲሁም በሥራው ዙሪያ ስላላቸው የእውቀት መጠንና አመለካከት አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ እንደ መልመጃዎች ሁሉ ፕሮጀክቶች በመደበኛ ሙከራ ፋንታ ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡ አሁንም ለሃሳብ አመንጪው አሠልጣኝ መጠነ ሰፊ አማራጮች አሉ፡፡

የዚህ ዓይነቶቹ አቀራረቦች ተሳታፊዎቹ በትክክለኛው መንደርደሪያ ላይ እንዳሉና ፕሮጀክቱን እንደሚያጠናቅቁ ለማረጋገጥ አሰተማሪው የኮርስ ተሳታፊዎቹን ያለ ማቋረጥ እንዲቆጣጠር ይጠይቃሉ፡፡ የራስ ተነሣሽነት ሳይኖራቸው የገቡ ግለሰቦች ከዚህ ዓይነቱ መልመጃ ጋር በደንብ ላይጓዙ ይችላሉ፡፡

አንዳንድ የአካል ጉዳት ዓይነቶች ያሉባቸው ግለሰቦች በዚህ ዓይነቱ ድርጊት ሙሉ በሙሉ ለመግባት ተጨማሪ ድጋፍ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ መስማት የተሳናቸው ወይም የከንፈር እንቅስቃሴን የሚያነብቡ የመስማት ችግር ያለባቸው ግለሰቦች፣ የአስተርጓሚ አገልግሎቶች፣ ወይም የትክክለኛ ጊዜ ቅጂዎች (Real Time Transcription) ድጋፎች አንዲታሰቡላቸው ይፈልጋሉ፤ ዓይነ ስውራን ግለሰቦች በመልመጃው ለመግባትና ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡

የአስተማሪዎችን/የአሠልጣኞችን የመማር ልምድ የሚያጠናክሩ ዝቅተኛ ቴክኖሎጂ ያላቸው መሣሪያዎች አሉ፡፡ እነዚህ የድምጽና ምስል መሣሪያዎች ተገላጭ የቻርት ወረቀቶችን (ፍሊፕ ቻርቶችን)፣ ከተናጋሪው በስተ ጀርባ ማሳያዎች /ምስሎች በጉልህ ማሳያ ፕሮጀክተሮችን፣ ጽሁፎች/ምስሎች የሚለዋውጡ ስላይዶችን ያካትታል፡፡ ተገላጭ ወረቀት (ፍሊፕ ቻርት) መጠቀም ለአሠልጣኙ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፤ ይሁንና ይህን ውጤታማ እንደ ሆነ ለማቆየት የሚከተሉትን ነጥቦች ያስታውሱ፡-

  • የሚነበብ ያድርጉት! በጉልህ ፊደል ይጻፉት (ቢያንስ ግማሽ ኢንች ከፍታና በመስመሮች መካከል የሁለት ቦታዎች ርቀት)፡፡
  • የተገላጭ ወረቀቱን የግርጌ ክፍል ከ1/4 እስከ 1/3 የሚሆነውን ባዶ አድርገው
    ይተዉት፡፡
  • ብዙ የቀለም ዓይነቶችን ይጠቀሙ (ከቢጫ በስተቀር)፡፡
  • ለቁልፍ ቃላት የግርጌ መስመሮችና ሣጥኖችን ይጠቀሙ፡፡የተጠናቀቁ ወረቀቶችን ግድግዳ ላይ ለመለጠፍ ማጣበቂያ ይኑርዎት፡፡
  • በጣም ረጅም ለሆነ ጊዜ ጀርባዎን ለአድማጮቹ አይስጡ፡፡
  • ሊያዩአቸው ለማይችሉ እጅግ ብዙ አድማጮች እነዚህን መሣሪያዎች አይጠቀሙ፡፡
  • የማየት እክሎች ላሉባቸው ሰዎች ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በፍሊፕቻርቱ ላይ ያስቀመጡትን ማንኛውንም ነገር ማንበብዎንና ማብራራትዎን ያረጋግጡ፡፡

የሚከተሉት አካሄዶች የድምጽና-ምስል (ኦዲዮ-ቪድዮ) መሣሪያዎን ውጤታማነት ያረጋግጣሉ፡-

  • ከመጀመርዎ በፊት ዕቃውን ለእይታ አስተካክለው ያስቀምጡ - የሚታዩ መግለጫዎች ንጹህ፣ ጠንካራና ለእይታ የተመቻቹ መሆናቸውን ያረጋግጡ፡፡
  • የክፍሉን መብራት ይመልከቱ (ስክሪኑን ለማየት በደንብ የደበዘዘ፣ ግን ለማስታወሻዎች ለመያዝና ለደህንነት በቂ ብርሃን ያለው፡፡ የከንፈር እንቅስቃሴ አንባቢ ለሆኑ ግለለሰቦች አስተርጓሚ መጠቀምን ልብ ይበሉ)፡፡
  • የእያንዳንዱን የበስተ ጀርባ ማሳያ/ስላይድ አቀማመጥ መልሰው ይቆጣጠሩ፡፡
  • በስክሪኑ ፊት ወዲያና ወዲህ አይመላለሱ ወይም አይቁሙ፡፡
  • በሚናገሩበት ጊዜ ስክሪኑን አይመልከቱ፡፡ ማስታወሻዎችን ከፈለጉ በጽሁፍ ገልብጠው ይያዙአቸው፡፡
  • ምናልባት አድማጮች ማስታወሻዎች እየወሰዱ እንዳይሆን በድምጽና ምስሎቹ መካከል አይንቀሳቀሱ (ወይም የበስተ ጀርባ ማሳያዎቹን ማለትም የስላይዶቹን ግልባጮ በወረቀት ይስጡአቸው)፡፡
  • ፕሮጀክተሩ ድምጽ ያለውና ሃሳብን የሚበታትን ከሆነ ስለ አንድ ርእስ በሚደረጉ ረጃጅም ውይይቶች ያጥፉት (ድምጽ ከሌሌው ግን እንደ በራ ይተዉት)፡፡
  • ትላልቅ የፊደል መጠኖችን (ፎንቶችን) ይጠቀሙ (ከ20 ነጥብ በላይ)፡፡
  • ያለ ከሆነ ቀለም ይጠቀሙ፡፡
  • ከመጠቀምዎ በፊት ቃላትና ፊደሎችን ይመልከቱ/አርትኦት ያድርጉ፡፡
  • ወደ ግርጌ በጣም የተጠጉ ጽሁፎች/ምስሎች አይኑሩዎት፡፡
  • የበስተ ጀርባ ማሳያ/ስላይድ ዝርዝር በሚያካትትበት ጊዜ ሁሉንም በአንዴ በማሳየት ፋንታ በዝግታ ወደ ታች ይልቀቁት፡፡
  • አሁንም የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተጠቀሙባቸው ባሉት የሚታዩ ነገሮች ላይ ያለውን ማንኛውንም ነገር ማንበብዎንና ማብራራትዎን ያስታውሱ፡፡

እርስዎ በአገር ውስጥና በክፍለ አህጉር አካባቢዎች የሚያዳብሩአቸውና የሚተገብሩአቸው እያንዳንዱ አቀራረቦች ልዩ መታወቂያዎችና የተለያዩ ውጤቶች ይኖሩአቸዋል፡፡ ለሥልጠናና ለአቀራረቦች የሚሰጡት የተሳታፊ መልሶች ልክ ሃሳቦችን እንደሚለዋወጡአቸው ግለሰቦች የተለያዩ ናቸው፡፡ ቀደም ካሉ ፕሮግራሞች የተገኙትን ትምህርቶች በእያንዳንዱ አዲስ ፕሮግራም ውስጥ ማዋሃድ ይኖርብዎታል፡፡