ተጨማሪ መረጃዎችን ለይቶ ማወቅና ማሰባሰብ
ጥራት ያላቸው መሣሪያዎች ለማንኛውም የሥልጠና ፕሮግራም ዋነኛ ፍሬ ነገሮች ናቸው፡፡ የኮርስ ተሳታፊዎች ከትምህርቱ አንዳንዱን ወዲያውኑ ሊረሱ ሲችሉ የተሰጡት መረጃዎችና ምንጮች ዘግይተው እንደ ጠቃሚ መሣሪያዎች ያገለግላሉ፡፡ ልብ ይበሉ፣ የማጣቀሻ መሣሪያዎች የተሳታፊው የሥልጠና መመሪያ አይደሉም፣ ግን ደግሞ እንደ ርእስ ነክ ጽሁፎች፣ መረጃ ነክ በራሪ ወረቀቶች፣ የድረ ገጽ ማጣቀሻዎች፣ ዋቤ መጻሕፍትና ሌሎች ፈጣን የማጣቀሻ መመሪያዎች የመሳሰሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡ ሊከተሉት የሚገባው ጥሩ ደንብ ለማንኛውም የታቀደ የመማር ዓላማ ተሳታፊዎች ወደ ቤታቸው ወስደው ወደፊት በማጣቀሻነት የሚጠቀሙበት አንዳች ምንጭ እንዳላቸው ማረጋገጥ ነው፡፡ አስተማሪዎች ለዚህ አዘውተረው በሥልጠና መመሪያ ላይ የሚተማመኑ ሲሆን ከላይ ከተሰጡት ሃሳቦች አንዳንዶቹን በመጠቀም ይህ በተሳካ ሁኔታ መከናወን ይችላል፡፡
ቁሳቁሶችን በአንድ ላይ ሲያሰባስቡ የተሰጠውን መረጃ ተደራሽነትና ጥቅም ላይ ለመዋል መቻል ልብ ይበሉ፡፡ ተመሳሳይ የድምጽና ምስል ቁሳቁሶች በሚያዘጋጁበት ጊዜ ተሳታፊዎች መረጃውን በኋላ መመዘን እንዲችሉ ለቁሳቁሶቹ ሙሉ ጥቅስ ማካተትዎን ያረጋግጡ፡፡ ይህ አካሄድ ሠልጣኙ መረጃውን እንዲሰማና እንዲያይ ብቻ ሳይሆን ግን ደግሞ ጠቅላላውን ቀዳሚ የመማር ዓይነቶች በመሸፈን እንዲያገኘውና እንዲሰማው ያስችለዋል፡፡