መማርና ውጤትን መገምገምና መመዘን

የአንድን የሥልጠና ፕሮግራም ውጤታማነትና ተጽእኖ መገምገምና መመዘን ወሳኝ ነገር ነው፡፡ አጠቃላይ ግምገማ የተሰጠው የትምህርት ውጤት ሆኖ የተከሰተውን የመማር መጠን ብቻ ሳይሆን ከሥልጠናው ጋር የሚዛመዱ አካባቢያዊ ተለዋዋጭ ነገሮችን እንዲሁም የአስተማሪውን ውጤታማነት ለመለካት ይሻል፡፡ በዚህ መመሪያ ያለው እያንዳንዱ ክፍለ ትምህርት አስተማሪዎቹ ከእያንዳንዱ ክፍለ ትምህርት ጋር ከሚዛመደው የሥልጠና ጥረት የተገኘውን እውቀት ለመመዘን ወዲያውኑ መጠቀም የሚችሉበትን ናሙና መሣሪያ ይሰጣል፤ ይህም ከእያንዳንዱ ክፍለ ትምህርት የመማር ዓላማዎች ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው፡፡ የመማር ልምዱን ውጤታማነት በመለካት ረገድ አስተማሪውን ለመርዳት አጠቃላይ የሥልጠና ፕሮግራም ቅኝት ደግሞ በአባሪ «ሀ» በማጣቀሻነት ቀርቦአል፡፡