የሥልጠና ዝርዝር

4.3 መደበኛ ገለጻ - ሃሳብ በማቅረብ ላይ የተመሠረተ አስገዳጅ ያልሆነ ኮታ

  • አስገዳጅ ባልሆነ ኮታ ስር አሠሪዎች የተቀመጠን የአካል ጉዳተኞች መቶኛ እንዲቀጥሩ እንደማይገደዱ ግን እንዲያደርጉት እንደሚበረታቱ ያስረዱ፡፡ በኮታው መስማማት ይልቁን በፈቃደኛነት ላይ የሚመሠረት ሲሆን ካለመስማማት የሚመነጭ ማበረታቻ የለም፡፡ ይህን ዓይነቱን ኮታ ለማብራራት የገለጻ ማሳያ 69ን ይጠቀሙ፡፡
  • በ1980ዎቹ አጋማሽ አስገዳጅ ያልሆነ የኮታ አሠራር በኔዘርላድስ እንደ ነበር የገለጻ ማሳያ 70ን ተጠቅመው ያስረዱ፡፡ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ግቡን እንዲመታ የታቀደው ኮታ በሦስትና በአምስት ከመቶ መካከል ነበር፡፡ መንግሥቱ ይህን በሚገመግምበት ጊዜ አሠራሩ ያመጣው መሻሻል አነስተኛ በመሆኑ እንዲሻር ወስኖአል፡፡ በአሠሪዎች ላይ ምንም ሕጋዊ ግዴታ የማያመጣና ግቡን ማሟላት በማይቻልበት ጊዜ ምንም ማዕቀቦች የማያስከትል ፈቃደኛ ኮታ በሥራ ስምሪት በአካል ጉዳተኞች ብዛት ላይ ተጽእኖ ማምጣቱ እምብዛም እንደ ሆነ በመግለጽ ያጠቃልሉ፡፡

    ብራዚል በዓይነተኛ የኮታ ዘዴ አሠራር መዋቅር ዙሪያ አስገራሚ ልዩነት አላት - ፈቃደኛ አይደለም ወይም ቀረጦችን አይጠቀምም፡፡ ኮታው 100 ወይም ከዚያ በላይ ሠራተኞች ላሉአቸው ኩባኒያዎች የሚያገለግል ሲሆን በ100 የሠራተኛ ብዛት ሁለት ከመቶ የሚሆነው የሥራ ኃይል አካል ጉዳተኞችን እንዲይዝ ይጠይቃል፡፡ መስፈርቱ 1000 ሠራተኞች ላሉአቸው ድርጅች እስከ አምስት ከመቶ ይጨምራል፡፡ ቁጥጥርና አስፈጻሚነት የእንባ ጠባቂ (ኦምቡድስማን) ጽሀፈት ቤት ኃላፊነት ሲሆን አሠሪዎች መቀጫ በመክፈል በቀላሉ መስማማትን ላያስወግዱ ይችላሉ፡፡ ይልቁን የምልመላ፣ የቅጥር፣ የሥልጠናና ሌላውንም ዕቅዳቸውን ጨምሮ መስፈርቱን ለማሟላት ምን በማድረግ ላይ እንዳሉ በሚመለከት ዝርዝር ዕቅዶችና ማስረጃዎች ለእንባ ጠባቂ ጽህፈት ቤቱ ማቅረብና ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡ ራስን ችሎ የመኖር ማእከል የተባለው ድርጅትና ሌሎች የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት የኮታ መስፈርቱን በመተግበር ረገድ ንቁ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው ደግሞ የብራዚሉ ሞዴል በዓይነቱ የተለየ ነው፡፡ ባሁኑ ጊዜ 22 ራስን ችሎ የመኖር ማእከሎችና ከ500 በላይ የአካል ጉዳት ማኅበራት በብራዚል የሚገኙ ሲሆን ብዙዎቹ ራስ አገዝ ሲሆኑ አንዳቸውም ከፌዴራል ወይም ከአካባቢ መንግሥት የገንዘብ እርዳታ አያገኙም፡፡ የኮታ መስፈርቱን ለማሟላት ስትራቴጂዎችን በሚተገብሩበት ጊዜ ችሎታው ያላቸውን ሠራተኞች በመመልመልና በማሠልጠን እንዲረዱአቸው እንዲሁም በአንዳንድ ሁኔታዎች አካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን ለመምራት ብዙ አሠሪዎች ከእነዚህ ድርጀቶች ጋር ውል ያደርጋሉ፡፡  ራስን ችሎ የመኖር ማእከሎቹና የአካል ጉዳተኞች ማኅበራቱ ሥራ የሚፈልጉ አካል ጉዳተኞችን መረጃ የሚይዙ ሲሆን ሥራ ለሚሰጡአቸው ኩባኒያዎች በአስተባባሪነት ይሠራሉ፡፡ ራስን ችሎ የመኖር ማእከሎቹ ሥራውን የማለማመድ ጉዳዮችን በማቅረብ፣ የሥልጠና ትምህርት ቤቶች ቴክኒካዊ ሥልጠና በመስጠት፣ እንዲሁም በኩባኒያው ልዩ የሥራ ሥልጠና በመስጠት ስለሚሳተፉ አቀራረቡ ማኅበራዊ አጋሮችን ያካትታል፡፡ በተለምዶ ከሁለት ዓመት በታች ውሎች ያሉአቸውንና በማከሎቹና በአካል ጉዳት ማኅበራቱ የሚከፈላቸውን የተፈላጊ ሠራተኞች እንዲያቀርቡ ኩባኒያዎቹ ከድርጅቶቹ ጋር ይዋዋላሉ፡፡