ማጣቀሻዎችና ምንባቦች

  • Barnes, C. (1992). Disability and employment. Department of Sociology & Social Policy, the University of Leeds, 1-28.

    ይህ ጽሁፍ በሥራ ስምሪት ረገድ በሚፈጸም ተቅዋማዊ መድልዎ ዙሪያ የሚያተኩር ሲሆን ጸረ መድልዎ ሕግ በአብዛኛው ለምን መፍትሔ እንደሚሆን ያስረዳል፡፡ ሪፖርቱ በአራት ክፍሎች የተከፋፈለ ነው፡፡ የመጀመሪያው በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈጸመውን ተቅዋማዊ መድልዎ ያብራራል፡፡ ሁለተኛው በሥራ ስምሪት የሚፈጸመውን ተቅዋማዊ መድልዎ ብዛት ያለው የተረጋገጠ ማስረጃ ያቀርባል፡፡ ሦስተኛው ለዚያ መድልዎ መንሥኤ የሆኑትን ዋነኛ ጭብ;ጦች ሲመረምር አራተኛው ከአካል ጉዳተኞች ጋር የሚገናኙ የመንግሥት ፖሊሲዎችን ይገመግማል፡፡

  • McDonnell, R., & Weale, A. (1984). Regulating for equal employment opportunities: The case of the disabled quota. Journal of Law and Society, 11(1), 105-114.

    ይህ ጽሁፍ የኮታን ታሪክ እንዲሁም በአካል ጉዳት ኮታዎች አጠቃቀም ረገድ የወቅቱን አዝማሚያዎች ይዳስሳል፡፡ የኮታዎች ውጤታማነትና አስተዳደራዊ ለውጦች ደግሞ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

    በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል (ደንበኝነት -subscription- ያስፈልጋል)፡-
    http://www.jstor.org/pss/1409933

  • Organisation for Economic Co-operation and Development (OECD); (2004) Transforming Disability into Ability: Polices to promote work and income security for disabled workers; Paris.

    ይህ እትም በኤኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት የተዘጋጀ ሲሆን የአካል ጉዳተኞችን የመሥራት ችሎታ የሚያበረታቱበትን ወይም የሚያጣጥሉበትን ሁኔታ አስመልክቶ በሃያ አገሮች ማኅበራዊ ፖሊሲዎች የተደረገ ንጽጽር ነው፡፡ በሚጠቀሙባቸው የድርጅቱ አባል አገሮች የኮታ አሠራሮች ምን ያህል ውጤታማ የመሆናቸው ጉዳይ ይህ ጥናት ከሚመረምራቸው ብዙ ፖሊሲዎች መካከል ይገኛል፡፡

  • Thornton, P. (1998) Employment Quotas, Levies and National Rehabilitation Funds for Persons with Disabilities: Pointers for policy and practice'

    ይህ ዘገባ የኮታ ቀረጥ አሠራሮችን ታሪክ፣ ጥቅሞችና ጉዳቶች፣ ቀረጥን መልሶ በማከፋፈልና በብሔራዊ የተሀድሶ እርዳታዎች ዙሪያ ያወያያል፡፡ የኮታ ቀረጥ አሠራሮችን ያቋቋሙና የተሀድሶ እርዳታዎች ልምድ ባላቸው አገሮች ለተካሄዱት ቅኝቶች መልሶችን ያቀርባል፣ እንዲሁም የኦስትሪያ፣ የቻይናና የሃንጋሪን ዘገባዎች ያጠቃልላል፡፡ በመጨረሻም በብሔራዊ እርዳታዎችና በፖሊሲ መማቋም አመራር ዙሪያ ዘገባ ያቀርባል፡፡

    በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል
    http://www.ilo.org/skills/what/pubs/lang--en/docName--WCMS_106625/index.htm