የሥልጠና ዝርዝር

4.2 መደበኛ ገለጻ - በውጤታማ ማበረታቻ ያልተደገፈ አስገዳጅ ኮታ

  • የገለጻ ማሳያ 66ን ተጠቅመው በዚህ ዓይነቱ የኮታ አሠራር ስር አሠሪዎች የአካል ጉዳተኞችን የተወሰነ ድርሻ (ኮታ) እንዲቀጥሩ በሕግ አማካይነት ይገደዳሉ፣ ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ማበረታቻ አንድም ስለማይኖር ወይም ማበረታቻው የተጠናከረ ስላልሆነ በማንኛውም ውጤታማ ማበረታቻ የተደገፈ እንዳይደለ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ይህ አለመኖር ሕጉ ውጤታማ ማበረታቻን ስለማይደነግግ ወይም የኮታ ግዴታው ባልተሟሉባቸው ጉዳዮች የመንግሥት ባለሥልጣኖች ክስ ለማቅረብ ባለመወሰናቸው ሊሆን ይችላል፡፡
  • ከታላቋ ብሪታኒያና ከታይላንድ ከተገኙት ምሳሌዎች ጋር ይህን ነጥብ ለማብራራት የገለጻ ማሳያዎች 67-68 tይጠቀሙ፡፡ ኮታ መጣል ብቻ በቂ እንዳልሆነ፣ ግን ኮታው ተግባራዊ ውጤት ማምጣት ካለበት ለውጤታማ የአፈጻጸም አሠራሮች ደንቦች መፈጠር እንዳለባቸው በመግለጽ ይደምድሙ፡፡

    በታላቋ ብሪታኒያ በ1993 ከእንግሊዛውያን አሠሪዎች ከሃያ በመቶ በታች የሚሆኑት በ1944ቱ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት ሕግ የተመሠረተውን ኮታ ሦስት ከመቶ አሟልተዋል፡፡ ለእንግሊዞቹ ኮታ አለመሳካት ምክንያት የሆነው ጥብቅ ነፃ የመሆን ፈቃዶችን ለመስጠትና አጥፊ አሠሪዎችን በፍርድ ቤት አማካይነት በመቅጣት ኮታውን ለማጠናከር የተከታታይ መንግሥታት ፈቃደኛ አለመሆንና አለመቻል
    ነበር፡፡ ጥቂት ክሶች ተከስተዋል፡፡ የ1995ቱ የአካል ጉዳት መድልዎ ሕግ በሥራ ላይ በዋለ ጊዜ ኮታው በ1996 ተሸሮአል፡፡

    በታይላንድ ለግል አሠሪዎች የኮታ ግዴታ የተመሠረተው በ1991ዱ የአካል ጉዳተኞች ተሀድሶ ሕግ ነው፡፡ ኮታውን ማሟላት ያቃታቸው ሰዎች በሕጉ ስር ቀረጥ እንዲከፍሉ ይገደዱ ነበር፡፡ የ1991ዱን ሕግ የተካው የ2007ቱ የአካል ጉዳተኞች ማጠናከሪያ ሕግ በመንግሥትና በግል አሠሪዎች ላይ የሥራ ስምሪት ኮታ የሚደነግግ ሲሆን ይህንንም በመከተል የወጣው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ትእዛዝ አንድ አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ በ100 ሠራተኞች መካከል እንዲገኝ ያዝዛል፡፡ የማይስማሙ አሠሪዎች የዋጋ ቅነሳ ሊያደርጉ፣ ሽያጮች ወይም አገልግሎቶች ሊያቀርቡ፣ ወይም ለአካል ጉዳተኞች ሙያዊ ሥልጠና ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ በእነዚህ አማራጮች የማይስማሙት የማካካሻ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ፡፡ ለሕጉ በመገዛት ወይም ባለመገዛት ዙሪያ መረጃዎች በማኅበራዊ ማበረታቻ መልክ ይፋ መደረግ ይችላሉ፡፡