ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦች

የአካል ጉዳት ሕጎች በሚረቀቁበትና ፖሊሲዎች በሚቀረጹበት ጊዜ በትግበራው የሚነሡ ችግሮች ተለይተው መታወቅና በቀላሉ መፈታት እንዲችሉ ለትግበራ ልዩ ትኩረት መሰጠት አለበት፡፡ ለአካል ጉዳተኞች እኩል የሥራ ስምሪት ዕድል ለማሳደግ የሚያቅድ ሕግና ፖሊሲ ውጤታማነት እነዚህን በሥራ ለመተግበር በሚጀመሩ እርምጃዎች ላይ ይመረኮዛል፡፡ እርምጃዎቹ በሕጉ ስር ስለ አካል ጉዳተኞች፣ አሠሪዎችና ሌሎች ባለ ድርሻዎች መብቶችና ግዴታዎች፣ ስለ ተጀመሩ የፖሊሲ ደንቦች፣ እንዲሁም ስለ አሠሪዎች፣ ለአካል ጉዳተኛ ሥራ ፈላጊዎችና ሠራተኞች ስለሚሰጥ የቴክኒክ ምክር፣ የድጋፍ አገልግሎቶችና እርምጃዎች የመረጃ ዘመቻዎችን ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ እርምጃዎች የገንዘብ ማትጊያዎችን እንዲሁም ከሥራ ጋር ተያያዥ የሆኑ ልዩ መሣሪያዎችን፣ ለሥራ ቦታ ማመቻቸት የሚሰጡ የገንዘብ እርዳታዎችን፣ ለዕለታዊ አኗኗር የሚያገለግሉ ልዩ መሣሪያዎችን የመሳሰሉ የተለዩ የሥራ ስምሪት ድጋፍ እርምጃዎችን ያካትታሉ፡