የቃላት መፍቻ

ዘመቻ

ለአንድ የተለየ ዓላማ የተዘጋጀ ሥነ ሥርዓታዊ የድርጊቶች ሂደት፡፡

ማትጊያ

ለድርጊት ወይም ለላቀ ጥረት የሚያነሣሳ ወይም ለበለጠ ምርታማነት ለማነሣሳት እንደ ወሮታ የሚሰጥ ነገር፡፡

ድጎማ

በመንግሥት ወይም በሌላ ተቅዋም ለግል ኢንዱስትሪያዊ ድርጅት፣ ለበጎ አድራጎት ድርጅት፣ ለግለሰብ ወይም ለመሰለው የሚሰጥ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ፡፡