የሥልጠና ዝርዝር

7.4 መደበኛ ገለጻ - አስተዳደራዊ አስፈጻሚ ተቅዋሞች

  • አስተዳደራዊ የማስፈጸሚያ አሠራሮች እንዲኖሩ በማድረግ የመድልዎ አልባነት መብታቸው እንደ ተጣሰ ለሚያስቡ ሠራተኞች ከፍርድ ቤት ሥነ ሥርዓቶች ጋር የሚያያዙ አንዳንድ አደጋዎችና ጉዳቶችን መቀነስ እንደሚችሉ ያስረዱ፡፡ እንደ እንባ ጠባቂ (ኦምቡድስማን) ተቅዋም እና/ወይም የሰብአዊ መብቶች፣ የእኩል ዕድሎች ወይም የአካል ጉዳት ኮሚሽን ያሉ አስቀድመው የገለጻ ማሳያ 116 የተዘረዘሩትን በጣም የተለመዱ የማስፈጸሚያ ድርጅቶች ዓይነቶች መልሰው ይመልከቱ፡፡

    የገለጻ ማሳያ 124ን በመጠቀም አነዚህ አካላት በጋራ የሚገለገሉባቸውን አሠራሮች ይመልከቱ፤ በተለያዩ ወገኖች ላይ ወጪዎችን አያስከትሉም፣ ሕጋዊ ውክልና አይጠየቅም፣ እንዲሁም የእነዚህ አካላት ውሳኔ የማያስገድዱ ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሣ በእነዚህ አካላት ፊት ያሉት ሥነ ሥርዓቶች እምብዛም መደበኛ ያልሆነ ባህርይ ሲኖራቸው በአሠሪው በኩልና በሌሎች ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ትብብር አለ፡፡

    የእንባ ጠባቂ ተቅዋሞችና የኮሚሽኖቹ ውሳኔዎች የማያስገድዱ የሆኑበት ጭብጥ ሕጋዊ ፋይዳ ይጎድላቸዋል ማለት አለመሆኑን ተሳታፊዎች እንደሚገነዘቡ ያረጋግጡ፡፡ በተቃራኒው እነዚህ አካላት በሚመለከታቸው መስኮች ልዩ የሙያ ችሎታ ማስፈለጉን ግምት ውስጥ በማስገባት የተቋቋሙ ናቸው፡፡ ይህ ማስተካከያ የሚመለከታቸው ወገኖች ይከተሉአቸዋል በሚል ተስፋ የእነዚህ ባለሙያ አካላት ውሳኔዎች ተደማጭነት ያላቸው በፍርድ ቤት ችሎቶችም ክብደት ይሰጣቸዋል የሚል እንደምታ አለው፡፡

  • የእንባ ጠባቂ (ኦምቡድስማን) ተቅዋም
    በብዙ አገሮች የመንግሥትን መልካም አሠራር ለዜጎች ለማሳደግ አንድ ወይም ብዙ የእንባ ጠባቂ ተቅዋሞች እንደ ተቋቋሙ ያስረዱ፡፡ እንዲህ ያሉት ተቅዋሞች በተለምዶ በመንግሥት እና/ወይም በሌሎች ሕዝባዊ ድርጅቶች ላይ ከግለሰቦች በጽሁፍ ወይም በቃል የሚቀርብ አቤቱታን የመመርመር ተግባር አላቸው፡፡ ትኩረታቸው መልካም አሠራርን ማሳደግ አስከ ሆነ ድረስ በግል አሠሪዎች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ለመመርመር ሥልጠኑ የላቸውም፡፡
    የዐውደ ንባቡን ክፍል 7.4.1 በመጥቀስና የገለጻ ማሳያ 125ን በመጠቀም አንድ የእንባ ጠባቂ ተቅዋም አቤቱታ የሚመረምርበትን ሂደት ይግለጹ፡፡ አንድን አቤቱታ በሚመረምሩበት ጊዜ የእንባ ጠባቂ ተቅዋሞች ምንም እንኳ ሥልጣናቸው በእነዚህ የሕግ ምንጮች የተወሰነ ባይሆንም ድርጊትን እንደሚለኩበት መነሻ የሰብአዊ መብቶች ሕግን፣ ዓለም አቀፍ የሠራተኛ ሕግንና የመድልዎ አልባነት ሕግን መጠቀም ይችላሉ፡፡ መደበኛ ያልሆነና አስታራቂ አቀራረብ በመጠቀም ችሎቶችን ያካሄዳሉ፡፡ የምርመራዎቻቸው ውጤቶች ብዙውን ጊዜ ታትመው ለሁለቱም ወገኖች የሚላኩ ሲሆን ተገቢ ከሆነም ለድርጊቱ መሻሻል መሪ ሃሳቦችን ይይዛሉ፡፡ ከእንባ ጠባቂ ተቅዋም የሚወጣ ትእዛዝ እንዲሁም ውጤታማነቱ በግልጽ በተደነገገው ሥልጣኑ ላይ ይመረኮዛሉ፡፡

    በዐውደ ንባቡን ገጽ 72 የቀረቡትን ምሳሌዎች በመጥቀስ የእንባ ጠባቂ ተቅዋሞች ግልጽ ሥልጣን በአገሮች ውስጥና በመከከላቸው እንደሚለያዩ ያስረዱ፡፡ እንደ ስዊድን ባሉ አንዳንድ አገሮች ለተለያዩ የመድልዎ ጭብጦች የተለዩ የእንባ ጠባቂ ተቅዋሞች አሉ፡፡ እንደ ኔዘርላንድስ ባሉ ሌሎች አገሮች ደግሞ የመንግሥትን ድርጊቶችና ግድፈቶች በተመለከተ ሰፊ ሥልጣን ያለው አንድ የእንባ ጠባቂ ተቅዋም አለ፡፡

    በኖርዌይ እኩል መብቶችና ዕድሎችን በማሳደግ ረገድና ለእኩልነት ሕግ ተገዢ መሆንን ለመቆጣጠር የእኩልነት እንባ ጠባቂ (አምቡድስማን) ጽህፈት ቤት አስተዳደራዊ ኃላፊነት አለው፡፡ ጽህፈት ቤቱ አቤቱታዎችን የሚቀበልና መሪ ሃሳቦችን (በተለይ ትእዛዞችን) የሚያወጣ ሲሆን (ምንም እንኳ በመቅጠርና በማባረር ጉዳዮች ባይሆንም) አንድን ክስ ትእዛዞችን ለማውጣት ውሱን ሥልጣን ወዳለው የእኩል መብቶች ቦርድ ይወስዳል፡፡ የዚህ አሠራር አንዱ ግልጽ ጠቀሜታ በተጠቃሚው ሠራተኛ ላይ ወጪዎች የማያስከትል መሆኑ ነው፡፡

    በፊንላንድ በእኩልነት እንባ ጠባቂ ጽህፈት ቤቱ ተነሣሽነት የእኩልነት ምክር ቤቱ የ1986ቱን የእኩልነት ሕግ ቁጥር 609 በመጣስ የሚደረግ አድላዊ ድርጊትን ለማቆም የማገጃ ትእዛዝ ሊያወጣ በሚችልበት ልዩነት ከላይ ከተመለከተው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሥርዓት አለው፡፡
  • የሰብአዊ መብቶች፣ የእኩል ዕድል ወይም የአካል ጉዳት ኮሚሽን
    በተለያዩ አገሮች ሰብአዊ መብቶችን፣ የእኩል አያያዝና የአካል ጉዳተኞችን መብቶች ለማሳደግና ለማስጠበቅ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽኖች፣ የእኩል ዕድል ኮሚሽኖችና የአካል ጉዳት ኮሚሽኖች ተቋቁመዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ አካላት በመንግሥትና በግለሰብ አካላት ላይ የሚቀርቡ የግለሰብ አቤቱዎችን ለመቀበል ሥልጣኑ አላቸው፡፡ ምንም እንኳ በአከራካሪ ሁኔታ እጅግ የበለጠውን ቢሆንም የግለሰብ አቤቱታዎቹ ብይን ለእነዚህ አካላት ከተመደቡት ብዙ ተግባሮች አንዱ ነው፡፡

    የዐውደ ንባቡን ክፍል 7.4.2 በመጥቀስ፣ እንዲሁም የገለጻ ማሳያ 126ን በመጠቀም፣ እነዚህ ኮሚሽኖች የሚመለከታቸውን የሕጎች አካላት ለማሳደግና ለመጠበቅ በጣም ሰፊ ሥልጣን እንዳላቸው ያስረዱ፡፡ ከዚህ የተነሣ እነዚህ አካላት አዘውትረው በራሳቸው ተነሣሽነት ምርመራዎችን የመጀመር፣ ለሰብአዊ መብቶች ተገዢ በመሆን፣ በእኩል ዕድል፣ በአካል ጉዳተኞች መብቶች ዙሪያ ነፃ ጥናቶችን የማካሄድ፣ ነፃ ሪፖርቶችን የማሳተምና ሥልጣናቸው በሚፈቅድላቸው ጉዳዮች ዙሪያ መሪ ሃሳብ የማውጣትና እንደ ሕዝባዊ የመረጃ ዘመቻዎች ለሕጋዊ ቅስቀሳና ድጋፍ፣ ወዘተ. ባሉ ዘዴዎች የሰብአዊ መብቶች/የመድልዎ አልባነት ሕግ/የአካል ጉዳት ሕግ ጥሰት ሰለባዎች ለሆኑት ድጋፍ የመስጠት ተግባሮች እንዳሉአቸው አጽንኦት ይስጡ፡፡ አንዳንድ ሕጎች አሠሪዎች ሕጉን ለመተግበር በሚያደርጉአቸው ጥረቶች ሪፖርቶችን እንዲህ ላሉት ኮሚሽኖች እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፡፡

    በዐውደ ንባቡ ገጽ 73 የቀረበውንና ከአውስትራልያ የተገኘውን ምሳሌ በማሳየት ይህን ንኡስ ክፍል ይደምድሙ፡፡

    በአውስትራልያ የገለጻ ማሳያ 126 የተጠቀሱት ተግባሮች በአንድ አካል ይተገበራሉ፤ ይኸውም በሰብአዊ መብቶችና የእኩል ዕድል ኮሚሽን አማካይነት ሲሆን በአንድ ፕሬዚደንትና በአራት ኮሚሽነሮች ሆኖ የሚከተሉትን ማለትም ፆታን፣ አካል ጉዳትን፣ የሰብአዊ መብቶችና የአገሬ ተወላጆን ይወክላል፡፡ ለብቃት ሲባል የተለያዩ የሠለጠኑ አካላትን እውቀትና ችሎታ በማሰባሰብ ወደ አንድ የሰብአዊ መብቶችና የእኩል አያያዝ ኮሚሽን በማምጣት ረገድ ዓለም አቀፍ አዝማሚያ ያለ ይመስላል፡፡