ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦች

ይህ ክፍለ ትምህርት የአካል ጉዳተኞችን የሥራ ስምሪት ለማሳደግ የታቀዱ ሕጎችን ለማርቀቅ ወይም ለማሻሻል እንዲሁም እነዚህን ሕጎች ለመተግበር ፖሊሲዎችን ለማውጣት በሚሹበት ጊዜ የሕግና ፖሊሲ አውጪዎች በስፋት መመካከር እንደሚኖርባቸው በመሠረታዊ ነገሮች ዙሪያ ያተኩራል፡፡  በስፋት የተደረገ ምክክር የሕግና ፖሊሲ አውጪዎችን በማኅበረሰቡ ውስጥ ካለው አውቀት ለመጠቀም የሚያስችላቸው ሲሆን የጸደቀውን ማንኛውንም ሕግና ፖሊሲ ውጤታማነት ለማረጋገጥ ይረዳቸዋል፡፡