የግብርና ሠራተኛ

ከ6 እስከ 9 ሰዓት (መማርን ለማጠናከር የተመረጡ አማራጭ መልመጃዎች በሚወስዱት የጊዜ መጠንላይ በመመርኮዝ)

ይህ ክፍለ ትምህርት የኮታ ቀረጥ ዘዴ ምን እንደ ሆነና ውጤታማ ማበረታቻ ሳይኖር ለአስገዳጅ ኮታ ተገቢ የሆኑ ጉዳዮችን በመሸፈን የኮታ ዘዴዎችን አጠቃላይ እይታ ይሰጣል፡፡ የኮታ አሠራሮች በተግባር እንዲሠሩ የሚያደርጉ ተግባራዊ ስልቶች ጐልተው ተቀምጠዋል፡፡

የመማር ዓላማዎች

በኮርሱ ፍጻሜ ተሳታፊዎች ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች ዙሪያ በቂ ችሎታ ይኖራቸዋል፡-

  • የኮታ ዘዴዎችን እንደ አዎንታዊ ተግባር እርምጃ ያብራራሉ፡፡
  • የኮታ አሠራሮችን ሦስት መሠረታዊ ዘዴዎችና ለእያንዳንዱ ዘዴ ተገቢ የሆኑትን ጉዳዮች ለይተው ያውቃሉ፡፡
  • አንድ የኮታ አሠራር በተግባር እንዲሠራ ለማድረግ ውጤታማ ስትራቴጂዎችን ይነድፋሉ፡፡
  • የትኛዎቹ አካል ጉዳተኞች የኮታ ዘዴዎች ተጠቃሚና ባለ መበት መሆን እንደሚኖርባቸው ለይተው ያውቃሉ፡፡
  • ኮታ የተወሰኑ አካል ጉዳተኞችን መደገፍ ይኖርበት እንደ ሆነ የሚደግፉና የሚቃወሙ ወገኖችን ያወያያሉ፡፡
  • በመደበኛ ኮታ ወይም በተለያዩ የኮታ መጠኖች መካከል ይወስናሉ፡፡
  • አግባብ ያለው የኮታ መቶኛን እንዲሁም ለዚሁ የታሰቡ አሠሪዎች ልዩነትና መጠን ይለያሉ፡፡