ቁልፍ ጽንሰ ሃሳቦች

የኮታ ዘዴዎች በሥራው ገበያ የአካል ጉዳተኞችን ውህደት ለማሳደግ የታቀዱ ምናልባትም በበለጠ የታወቁና አጅግ የተለመዱ የአዎንታዊ ተግባር እርምጃዎች ናቸው፡፡ ኮታዎች አንዳንዴ በሕግ አንዳንዴ ደግሞ በመንግሥት ውሳኔ ወይም ደንብ ይተዋወቃሉ፡፡

በኮታ ዘዴዎች ስር አነስተኛ ብዛት ያላቸውን ሰዎች የሚቀጥሩ አሠሪዎች ከሥራ ኃይላቸው የተወሰነው መቶኛ (ኮታ) በአካል ጉዳተኞች መያዙን እንዲያረጋግጡ ግዴታ ይጣልባቸዋል፡፡ ይህን መሰሎቹ ዘዴዎች መጀመሪያ ብቅ ያሉት ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ማግስት ሲሆን ከወታደራዊ ግዳጅ የተነሣ የአካል ጉዳት የደርሰባቸው የጦርነት ተመላሾች ብቸኞቹ ተጠቃሚዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ዘዴዎች አነስተኛ አሠሪዎችን በተለምዶ ነፃ አድርገዋል፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ባለው ጊዜ የኮታ ዘዴዎች ሲቪል አካል ጉዳተኞችን እንዲሸፍኑ የተስፋፉ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ባሉ አገሮች ተቀባይነት አግኘተዋል፡፡ ይሁንና ለአነስተኛ አሠሪዎች የተሰጠው ነፃ የመሆን ዕድል አዘውትሮ ተጠብአቆል፡፡ በጣም በቅርቡ አንዳንድ የኮታ ዘዴዎች ሥነ ኅሊናዊ ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች (በጃፓን እንዳለው የኮታ ዘዴ) እና የአእምሮ ጤና ችግሮች ያለባቸውን ሰዎች (በጀርመን እንዳለው) እንዲያካትቱ ሆነው በግልጽ ተስፋፍተዋል፡፡