ማጣቀሻዎችና ምንባቦች

  • Gunderson, M., & Hyatt, D. (1996). Do injured workers pay for reasonable accommodation? Industrial and Labor Relations Review, 50(1), 92-104.

    ደራሲዎቹ ከ1979 እስከ 1988 ባሉት ዓመታት በኦንታርዮ ካናዳ ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች ከደረሰባቸው ጉዳት በኋላ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ለማመቻቸት ለ«ተመጣጣኝ ማመቻቸት» መስፈርቶች ተብሎ ዝቅተኛ ክፍያዎች ባገኙበት ሁኔታ ዙሪያ ማስረጃ ያቀርባሉ፡፡ የመረጃ ምንጭ የሆነው የኦንታርዮ ሠራተኞች የካሳ ቦርድ ቋሚ እክሎች ያሉባቸውን ሰዎች በሚመለከት ያደረገው ቅኝት በሁለት የማመቻቸት ፈርጆች ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል፣ እነርሱም እንደ ተስተካከለ መሣሪያና አጭር የሥራ ሰንጠረዥ የመሰሉ የሥራ ቦታ ለውጦች፣ እንዲሁም ከማጎንበስ ወይም ክብደት ያለው ነገር ከማንሣት ነፃ መሆንን የመሰሉ የአካል እንቅስቃሴን የሚጠይቁ ድርጊቶች መቀነስ ናቸው፡፡  የተጎዳ ሠራተኛቸውን መልሰው የቀጠሩ አሠሪዎች ያደረጉትን የማመቻቸት ወጪ ሁሉ በውጤቱ ራሳቸው የወሰዱ ሲመስሉ በሌሎች ድርጅቶች ጉዳት የደረሰባቸውን ሠራተኞች የቀጠሩ አሠሪዎች ለሥራ ቦታ ለውጦች ከሚያስፈልገው ወጪ በርካታውን ድርሻ በዝቅተኛ ክፍያ መልክ ወደ ተጎዱት ሠራተኞች አዛውረዋል፡፡

    በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል (ደንበኝነት -subscription- ያስፈልጋል)፡-
    http://www.jstor.org/pss/2524391

  • Metts, R. (2000). Disability issues, trends, and recommendations for the World Bank. Social Protection, 1-100.

    ሁለት ወቅታዊ የአካል ጉዳት ትርጕሞችን ከገለጸና ለአካል ጉዳት ፖሊሲና ዕቅድ አመቺነታቸውን ካነፃፀረ በኋላ ጽሁፉ የአካል ጉዳት ፖሊሲና አሠራርን አዝጋሚ ለውጥና አሁን ያለበትን ሁኔታ ገላጭ ትንታኔ ያቀርባል፡፡

    በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-
    http://www-wds.worldbank.org/PDF/multi0page.pdf

  • Morris, J. (2001). Impairment and disability: Constructing an ethics of care that promotes human rights. Hypatia, 16(4), 1-16.

    ደራሲዋ ጄኒ ሞሪስ በማኅበራዊ የአካል ጉዳት ሞዴል ውስጥ የግል የእክል ተመክሮዋንና ሰብአዊ መብቶችን ለማሳደግ ለልዩነቶች እውቅና የመስጠትን አስፈላጊነት ታወያያለች፡፡

  • O'Neil, T., & Piron, L. (2003). Rights-based approaches to tackling discrimination and horizontal inequality: Background paper. Overseas Development Institute, 1-21.

    ለእኩልነትና ለማኅበራዊ መካተት የሰብአዊ መብቶች አስፈላጊነት፣ የመድልዎ ስፋትና ባህርይ እንዲሁም በገቢ፣ በንብረቶች፣ በጤና፣ በትምህርት አኳያ ያሉትን እኩል ያለመሆን ክስተቶች በማስረዳት ረገድ ያለው ድርሻ፣ መድልዎ የሚከሰተበት ሂደትና መንግሥታት ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ መድልዎን በሕግና በአሠራር የሚዋጉበት ደረጃ በዚህ ጽሁፍ የተካተቱ ፍሬ ነገሮች ናቸው፡፡ በተጨማሪም የሚፈጥሩአቸውን መድልዎና እኩል ያለመሆን ክስተቶች ለመዋጋት በመንግሥታት፣ በሲቪል ኅብረተሰብና በዓለም አቀፍ ለጋሾች የሚደረጉትን ‹በመብት ላይ የተመሠረቱ አቀራረቦች› እምቅ አስተዋጽኦ ይዳስሳል፡፡

    በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-
    http://www.odi.org.uk/Rights_and_Discrimination_Background_Paper.pdf

  • Rosenthal, E., & Sundram, C. (2003). International human rights in mental health legislation. World Health Organization. New York Law School Journal of International and Comparative Law. Volume 21 (3), p.469.

    ይህ ጽሁፍ መንግሥታት አካል ጉዳተኞችን የሚነኩ ሕጎች በሚያረቅቁበት ጊዜ ግምት ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸውን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግ ፍሬ ነገሮች አንዳንዶቹን ይገልጻል፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግ የአእምሮ፣ የጤናና የማኅበራዊ አገልግሎት መዋቅሮችን አሠራር ለሚቆጣጠሩ ሕጎች፣ እንዲሁም ዜጎችን ሁሉ ከመድልዎ ለሚጠብቁ ሰፋ ያሉ ሕጎች ሁለት ዋነኛ እንደምታዎች አሉት፡፡

  • The National Council on Disability Topical Overviews for Delegates to the 6th Ad Hoc Committee on the Protection and Promotion of the Human Rights of People with Disabilities.

    የተመድ ድንጋጌውን ከማርቀቅ ጋር ተያይዘው ይደረጉ ለነበሩት የሰብአዊ መብቶች ውይይቶች አንገብጋቢ በሆኑ ርእሶች ዙሪያ ይህ የተከታታይ ጽሁፎች ስብስብ እንዲዘጋጅ ብሔራዊ የአካል ጉዳት ምክር ቤት አዝዞአል፡፡  ጽሁፎቹ በውይይት ስር ያሉትን ጽንሰ ሃሳቦችና አወቃቀሮች እንዲገነዘቡና እንደጠቀሙባቸው ልኡካኑን ለመርዳት የታሰቡ ነበሩ፡፡ ርእሶቹ የሥራ ስምሪትና የሥራን፣ የትምህርትን፣ የጤና አጠባበቅን፣ ትራንስፖርትን፣ የመረጃ ቴክኖሎጂን፣ ራስን ችሎ መኖርን፣ እንዲሁም በፖለቲካዊና በሕዝባዊ ሕይወት መሳተፍን ያካትታሉ፡፡ እያንዳንዱ ጽሁፍ ለርእሱ አግባብነት ያላቸውን ቁልፍ ጉዳዮች ሲመረመር ለምሳሌ በሥራ ስምሪትና በመሥራት መብት ዙሪያ በሚያወሳው ጽሁፍ እንደ «ተመጣጣኝ ማመቻቸት» እና «ያልተገባ ችግር» ያሉት ጽንሰ ሃሳቦች ተብራርተዋል፡፡

    በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-
    http://www.ncd.gov/newsroom/publications/2005/publications.htm

  • Weiwei, L. (2004). Equality and non-discrimination under international human rights law. Research Notes.

    ይህ ጽሁፍ የመድልዎ አልባነትና የጽንሰ ሃሳቡን ታሪካዊ እድገት ጠቅላላ እይታ የሚሰጥ ሲሆን የመድልዎ አልባነት መርሆን ስፋት በዝርዝር ይመረምራል፡፡ ይህ ጽሁፍ መርሁ በቻይና ሥራ ላይ የዋለበትን ሁኔታ ለውይይት በማቅረብ የአገር ውስጥ ትግበራውን አስመልክቶ አጽንኦት ይሰጣል፡፡

    በሚከተለው ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡-
    http://www.mittendrinundaussenvor.de/fileadmin/bilder/0304.pdf