የሥልጠና ዝርዝር

2.9. መደበኛ ገለጻ - አካል ጉዳትና ሥርዓተ ፆታ

  • ችሎታዎችን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች በይበልጥ የተጎጂነት ሁኔታ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል እየጐላ በመሄድ ላይ ያለ ግንዛቤ እንዳለ ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ ይህ ለአካል ጉዳተኛ ግለሰቦች ደግሞ አውነት ይሆናል፡፡
  • በአካል ጉዳት አጋጣሚ ውስጥ ያለውንና የተከበበውን የሥርዓተ ፆታ ማዳላት ለመግለጽ የገለጻ ማሳያ 36ን ይጠቀሙ፡፡
  • ሕግ በማዘጋጀት ረገድ ብሔራዊ ሕግና ፖሊሲ አውጪዎች አካል ጉዳተኛ ሴቶችና ወንዶች ከእኩልነት እንደሚጠቀሙ እንዲያረጋግጡ ለአካል ጉዳት የሥርዓተ ፆታ መለኪያ፣ ለአካል ጉዳት ሕጎችና ፖሊሲዎች፣ በተቻለ መጠን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው አጽንኦት በመስጠት ይዝጉ፡፡