የሥልጠና ዝርዝር

2.7. መደበኛ ገለጻ - የእኩልነት መርሆ

  • የገለጻ ማሳያዎች 29–32ን በመጠቀም ስለ እኩልነት መርሆና በሕግ ውስጥ እርሱን ለመግለጽ ስለሚያገለግሉት መንገዶች ለተሳታፊዎች ያስረዱ፡፡ እኩልነት መርሆ ከሰብአዊ ክብር አስተሳሰብ ጋር በቅርበት የተያያዘ ነው፡፡ ይህም አካላዊ፣ አእምሮአዊና ሌሎች ልዩነቶችን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ሰብአዊ ፍጡራን ሁሉ እኩል ዋጋና ግምት አላቸው በሚለው ጽንሰ ሃሳብ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የእኩል ግምትና ክብር ባለ መብትና ሊሰጠው የሚገባ ነው፣ ወይም በ1948ቱ ጠቅላላ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 1 እንደ ተገለጸው «ሰበአዊ ፍጡራን ሁሉ ነፃ እንዲሁም በክብርና በመብቶች እኩል ሆነው የተወለዱ ናቸው. . .» የዓሥድ የፊላዴልፊያ መግለጫ (1944) ዘር፣ ሃይማኖት፣ ወይም ፆታ ግምት ውስጥ ሳይገቡ ሰብአዊ ፍጡራን ሁሉ በነፃነት፣ በክብር፣ በኤኮኖሚያዊ ደህንነትና በእኩል ዕድል ቁሳዊ ደህንነታቸውንና መንፈሳዊ እድገታቸውን የማራመድ መብት አላቸው፡፡ ይህም ሴቶችና ወንዶች የሥራ ገበያውን ጨምሮ እኩል አጋጣሚ ሊኖራቸውና በኅብረተሰብ ውስጥ ለመሳተፍ እኩል ዕድሎች እንዲኖራቸው ይገባል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ልዩነቶች ችላ መባል አለባቸውን? አይደለም፣ በተቃራኒው አስቸጋሪ ሁኔታ በሚፈጥሩባቸው መንግዶች ከሌሎች የሚለዩ ሰዎች ከእነዚህ ልዩነቶች በመነሣት የሚገጥሙአቸውን ጉስቁልናዎች ለማካካስ በተለየ ሁኔታ መያዝ እንደሚኖርባቸው በስፋት ይታመናል፡፡.

    የእኩልነት መርሆ፣ እንዲሁም የእርሱ ተቀጽላ የሆነው መድልዎን መከልከል፣ በሕግ ውስጥ በተለያዩ መንገዶች መገለጽ ይችላሉ፡፡

    መደበኛ እኩልነት

    በመደበኛ የእኩልነት አቀራረብ በተመሳሳይ ሁኔታ የተቀመጡ ሰዎች በአንድ ዓይነት መንገድ መያዝ ይኖርባቸዋል (የገለጻ ማሳያ 31)፡፡ እንዲህ ያለው አቀራረብ ግለሰብን፣ ጭብጣዊ ልዩነቶችና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አዘውትሮ አግባብነት እንደሌላቸው አደርጎ ይተዋቸዋል፡፡ የአንድ ዓይነት አያያዝ መነፈግ ተከልክሎአል፣ ነገር ግን ማመቻቸቶችን ወይም ማስተካከያዎችን ለማድረግ የተቀመጠ መስፈርት የለም፡፡ ስለዚህ ይህ አቀራረብ የአንዳንድ አካል ጉዳተኞችን የድጋፍ ፍላጎቶች ማሟላት ያቅተዋል፡፡

    የዕድል እኩልነት

    ሌላው እኩልነት በጽንሰ ሃሳብ መልክ ሊገለጽ የሚቻልበት መንገድ በዕድል እኩልነት አማካይነት ነው (የገለጻ ማሳያ 32)፡፡ ይህ ጽንሰ ሃሳብ እኩል አጋጣሚዎችን ይሰጣል፣ ግን የግድ እኩል ውጤቶችን አይደለም፡፡ በዚህ እኩልነትን የመመልከቻ መንገድ የግለሰብ አስፈላጊነትና የወገን ልዩነቶች የታወቁ ሲሆኑ ማኅበራዊ ተሳትፎን ሊያግዱ የሚችሉ አካል ጉዳተኞችን የሚያጋጥሙአቸው ውጫዊ መሰናክሎች ግምት ውስጥ ገብተዋል፡፡ የተዛቡ አመለካከቶችና መዋቅራዊ መሰናክሎች ለሙሉ ተሳትፎ እንደ እንቅፋቶች ታይተዋል፡፡ በዚህ አቀራረብ የተዛቡ አመለካከቶች ለድርጊት መሠረት ከሆኑና መጠቀምና መካተትን ለማሳደግ በማኅበራዊው ወይም በተገነባው አካባቢ የሚደረጉ ለውጦች አስፈላጊ ከሆኑ አካል ጉዳት ችላ ይባላል፡

    የውጤቶች እኩልነት

    የውጤቶች እኩልነት ለሁሉም ሰው አንድ ዓይነት ውጠቶች ማስገኘትን ይመለከታል (የገለጻ ማሳያ 33)፡፡ እኩልነት በዚህ መንገድ በሚታይበት ጊዜ የግለሰብና የወገን ልዩነቶች ይታወቃሉ፡፡ ለምሳሌ እኩል ክፍያ ያገኙ እንደ ሆነ የሚቀርብ ጥያቄን በመመርመር ረገድ ለአንድ አካል ጉዳተኛ ሠራተኛ የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ወጪዎች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ይህ የእኩልነት ጽንሰ ሃሳብ ድክመት አለበት፡፡ በመንግሥት፣ በግሉ ዘርፍና በግለሰብ ደረጃ እውነተኛ የውጤቶች እኩልነት ዋስትና ይገኝ ዘንድ የአካል ጉዳተኞችን ፍላጎቶች ለማሟላት ኃላፊነቱ የትኛው ላይ እንደሚያርፍ በግልጽ አያመለክትም፡፡ በዚህ አቀራረብ እኩል ያልሆኑ ውጤቶችን ለማስተካከል የግለሰቡ መልካም ሥራዎች ታውቀው እንደ ሆነ ግልጽ አይደለም፡፡

  • የገለጻ ማሳያ 29ን መልሰው ይመልከቱና በተሰጡት ሁለት መግለጫዎች እይታ የእኩልነት መርሆ ለእነርሱ ምን ማለት እንደ ሆነ እንዲያጋሩ ተሳታፊዎችን ይጠይቁአቸው፡፡ በመሠረቱ ይህ ሴቶችና ወንዶች የሥራ ገበያውን ጨምሮ በኅብረተሰብ ውስጥ ለመሳተፍ እኩል አጋጣሚ ሊኖራቸው እንደሚገባ ያመለክታል፡፡
  • ይህን ጥያቄ ለተሳታፊዎች ያቅርቡ፤- ስለዚህ ልዩነቶች ችላ መባል አለባቸውን? አይደለም፣ በተቃራኒው አስቸጋሪ ሁኔታ በሚፈጥሩባቸው መንገዶች ከሌሎች የሚለዩ ሰዎች ከእነዚህ ልዩነቶች በመነሣት የሚገጥሙአቸውን ጉስቁልናዎች ለማካካስ በተለየ ሁኔታ መያዝ እንደሚኖርባቸው በስፋት ይታመናል፡፡
  • የዕድል እኩልነት ጽንሰ ሃሳብ በአሁኑ ጊዜ እጅግ አዘውትሮ በብሔራዊ ሕግ ውስጥ ጥቅም ላይ እንደሚውል በአጽንኦት ያስረዱ፡፡