የሥጋ ደዌ ተጠቂ የነበሩ አዛውንት ሴት ለኢትዮጵያ የቀድሞ ሥጋ ደዌ ተጠቂዎች ብሔራዊ ማኅበር የገቢ ማሰባሰቢያ ዓላማ የፈትል ጥጥ ሲያባዝቱ፡፡

ከ6 እስከ 9 ሰዓት (መማርን ለማጠናከር የተመረጡ አማራጭ መልመጃዎች በሚወስዱት የጊዜ መጠን ላይ በመመርኮዝ)

ይህ ክፍለ ትምህርት የአካል ጉዳትን፣ የመድልዎ አልባነትና የእኩልነት መርሆን፣ በሕግ ውስጥ የአካል ጉዳትን ጭብጥ፣ እንዲሁም ወደ አዎንታዊ እርምጃ የሚያመራ ማኅበራዊ ፖሊሲን በመዳሰስ ረገድ ሠልጣኙን በመርዳት አካል ጉዳትን እንደ ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ያረጋግጣል፡፡

የመማር ዓላማዎች

በኮርሱ ፍጻሜ ተሳታፊዎች ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች ዙሪያ በቂ ችሎታ ይኖራቸዋል፡-

  • የአካል ጉዳተኞችን እኩል የሥራ ስምሪት ዕድል መስፋፋት በመደገፍ ረገድ ዓሥድ የሚጫወተውን ሚና ያውቃሉ፡፡
  • አካል ጉዳትን እንደ ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ በመውሰድ ረገድ የግል እምነቶቻቸውንና አመለካከቶቻቸውን ያንጸባርቃሉ፡፡
  • የመድልዎ አልባነት መርሆን ያስረዳሉ፡፡
  • አካል ጉዳት በሕግ ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን ስፍራ ያሳያሉ፡፡
  • የሕግ ተጠቃሚ ማን ሊሆን በሚችልበት ጭብጥ ውስጥ አካል ጉዳትን ያብራራሉ፡፡
  • በሕግ ውስጥ የአካል ጉዳትን ትርጓሜ ዒላማ የሚያደርጉ ልዩ ግቦችን ለይተው ያውቃሉ፡፡
  • ወደ እኩልነት የሚያመሩ መሠረታዊ ሰብአዊ መርሆዎችን ያሳያሉ፡፡
  • የእኩል የሥራ ስምሪት ዕድል መንታ አቀራረብን ያስረዳሉ፡፡
  • መድልዎን በማጠናከር ረገድ ሥርዓተ ፆታ ሊጫወት የሚችለውን ሚና ያውቃሉ፡፡