የሥልጠና ዝርዝር

አጀማመር፡- ዝግጅት

  • ሴሚናሩ ከመጀመሩ ጊዜ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በፊት የሥልጠናውን አካባቢ ያዘጋጁ፡፡

  • የሥልጠናው ጽሁፎች ቅጂዎች መታደላቸውን ያረጋግጡ፡፡

  • ጥቅም ላይ ለመዋል ዝግጁ መሆኑን ለማረጋገጥ የድምጽና ምስል መሣሪያውን ያስተካክሉና ይሞክሩት፡፡ ተሳታፊዎች እየገቡ ሳለ ስክሪኑን አብርተው ይተዉት፡፡
    የገለጻ ማሳያ 1
  • ሦስት የፖስተር/የተገላጭ ወረቀቶች በግድግዳ ላይ ይስቀሉና በመጀመሪያው ከላይ «መሠረታዊ ደንቦች»፣ ቀጥሎ «የመማር ዓላማዎች»፣ በሦስተኛው ደግሞ «የማቆሚያ ቦታ» ብለው ይጻፉ፡፡
  • ለኮርስ ተሳታፊዎች አቀባበል ያድርጉ፣ ሴሚናሩንም በጊዜው ይጀምሩ፡፡