የሥልጠና ዝርዝር

እርስዎ እንደ አስተማሪ እና/ወይም የኮርስ አስተባባሪ ለሥልጠናው ዝግጅት ዒላማ የሚሆኑ ሰዎችን ለይቶ ለማወቅ፤ የተለዩ ፍላጎቶቻቸውን ለይተው ማወቅዎን፤ ተሳታፊዎችን ለኮርሱ ማስተዋወቅዎንና መመዝገብዎን፤ ሥርዓተ ትምህርቱን ለዝግጅቱ ማስተካከልዎን፤ መሸፈን ባለበት ይዘት ላይ ተመሥርቶ እጅግ ተገቢ የሆኑ አስተማሪዎችን ለይተው ማወቅዎ፤ የሥልጠና አካባቢውን ማስተባበርዎና ማዘጋጀትዎ፤ የተሳታፊዎችን መገኘት ማረጋገጥዎና ለእነርሱም የዝግጅቱን መመሪያዎች መስጠትዎ ሥልጠናውን በትክክል ወደ ማካሄድ ነጥብ እንደሚያመራ ይገመታል፡፡ ከዚህ በታች ያለው የሥልጠና ዝርዝር ትክክለኛው ዝግጅት ከመካሄዱ አንድ ሰዓት አስቀድሞ ይጀምራል፡፡