መረጃ የማቅረብ ስልቶች

እንደ አሠልጣኝ እርስዎ በቂ ጊዜ ወስደው ይህን እትም መመርመርዎ ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ የመመሪያዎቹ መጽሐፍ «ዐውደ ንባብ–Primer ፕራይመር» ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በመላው ፕሮግራም ውስጥ በተደጋጋሚ የተጠቀሰ በመሆኑ ቅጂዎቹ ለኮርስ ተሳታፊዎች ሁሉ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል፡፡ የዚህ መመሪያ ተጓዳኝ የሆነው የመመሪያዎቹ መጽሐፍ በእንግሊዝኛ ከሚከተለው ድረ ገጽ ሊገኝ ይችላል፡-

http://www.ilo.org/global/publications/ilo-bookstore/order-online/books/WCMS_091340/lang--en/index.htm

ከዚህ ኅትመት ጋር የሚኖርዎት ትውውቅ በአገርዎና በአካባቢ ደረጃ አግባብነት ባላቸው አርአያዎች በወቅቱ ካለዎት የእኩል ሥራ ስምሪት ዕድል እውቀትና ልምድ ጋር ተዳብሎ ለሥልጠናዎ መሠረት ይጥላል፡፡ ቴክኒካዊ መሠረቱ እንደ አስተማሪ አመኔታን ለማግኘትዎ ወሳኝ ነው፡፡ እንደ አስተማሪ የግንኙነትዎ ውጤታማነት ከዚህ ጋር በእኩል ደረጃ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ግንኙነት የገላጭና የተቀባይ ጭብጦች ጥምረት ሆኖ ሳለ ከውጤታማ ግንኙነት 70 ከመቶው ተቀባይ (ማዳመጥ) ሲሆን 30 ከመቶው ብቻ ገላጭ (እርስዎ የሚልኩት) ነው፡፡ በገላጩ የግንኙነት ክፍል ውስጥ ሰዎች ከእርስዎ ከሚሰሙት ከግማሽ በላይ በሰውነት እንቅስቃሴ የሚልኩት ነው፡፡ ከውጤታማ ግንኙነት ትንሹ ክፍል ብቻ እርስዎ የሚናገሩአቸው ቃላት ሲሆኑ ሁለተኛው ትልቁ ነገር የድምጽዎ ቃና ወይም አረባብ ነው፡፡ ገላጭ ግንኙነት ከጥሩ ንግግር ወደ 30 ከመቶ የሚሆነውን ይይዛል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘው ግልጽና የታመነ የሰውነት እንቅስቃሴ ዝርዝር ነው፡፡

  • በጣም ያልተዝናና፣ በጣምም ያልተጨነቀ የሚመች አቋምን ይጠብቁ፡፡ ይህ ፍላጎትን ያመለክታል፡፡ በጣም ኮስታራ አቋም የሚስፈራራ ወይም እርስዎ ችኮላ ላይ መሆንዎን አመልካች ሊሆን ይችላል፡፡
  • ጥሩ የዓይን ግንኙነት ይኑርዎት፡፡ ይህ ፍላጎት እንዳለዎት፣ ግምት የሚሰጡ መሆንዎን ሲያመለክት የመተማመንና የመግባባትን መፈጠር ያሳድጋል፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች በጣም የበዛ ቀጥተኛ የዓይን ግንኙነት እንደ ፍጥጫ ወይም ግለኝነታቸውን እንደ መዳፈር አድርገው ስለሚቆጥሩት ለባህላዊ ወይም ከአካል ጉዳት በተያያዘ ለማይባሉ ነገሮች ጥንቁቅ ይሁኑ፡፡ የአለመመቸት አመላካቾችን በዓይንዎ ግንኙነት ይመልከቱና በዚያው መሠረት ራስዎን ያስተካክሉ፡፡
  • ከድንጋጤ፣ ከመከፋት፣ ከቁጣ ወይም ከአለመስማማት ነፃና ተፈጥሮአዊ የሆነ የፊት ገጽታ ነፃ ግንኙነትን ያበረታታል፡፡ እንደ አሠልጣኝ በሚጫወቱት ሚና ምቾት የሚሰማዎት ከሆነ ይህን ለማሳካት በአንጻራዊ መልኩ ቀላል ይሆናል፡፡ ይሁንና ለዚህ ሚና አዲስና በመጠኑ የተጨነቁ ከሆኑ መጨነቅዎን ስለሚያንጸባርቁ የፊት ገጽታዎችዎን ልብ ይበሉ፡፡ ጥሩ ነገር በማድረግ ላይ በሚያተኩሩበት ጊዜ በጣም ኮስታራ ሊመስሉ ስለሚችሉ ገጽታዎችዎም ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን ያሳያሉ ተብለው በስህተት ሊተረጐሙ ይችላሉ፡፡

እንደ ብዕርና ወረቀት ያለ ማንኛውንም ነገር በግልጽ ሁኔታ በእጅ ማፍተልተል የመሰለ ሃሳብን የሚሰርቅ የሰውነት እንቅስቃሴ ውጤታማ ግንኙትን ሊቀንስ ይችላል፡፡ የሰውነት እንቅስቃሴዎ የኮርስ ተሳታፊዎቹን ሃሳብ የሚሰርቅ ወይም የሚያበሳጫቸው እንደ ሆነ ልብ ማለትን ያስታውሱ፡፡ አንድ ሰው እርስዎ የሚያስቡትን እንዲያውቅ ከሚናገሩአቸው ቃላት ይልቅ በድምጽዎ የሚንጸባረቀው ሀቀኛነት ይበልጥ ኃይለኛ ነው፡፡ የድምጽዎ ቃና በጣም ጥብቅ፣ በጣም ተጫዋች፣ ወይም በጣም አምባ ገነን ከሆነ አድማጩ ይህን አስፈሪ፣ ዝቅ የሚያደርግ፣ ወይም እርስዎ በእነርሱ ላይ የበላይነት እንደሚሰማዎት አድርጎ ሊተረጕመው ይችላል፡፡  የድምጽ ቃና የሚናገሩአቸውን ቃላት ዓላማ የሚመጥን መሆን ሲኖርበት ለግለሰቡ ፍላጎቶች የተስተካከለ መሆን ይኖርበታል፡፡ ቃላት የገላጭ ግንኙነት የመጨረሻ ጫፍ ናቸው፣ ይህን ክፍልም በሚመለከት የሚደረጉአቸው ጥንቃቄዎች በቀላሉ ሊጠቃለሉ ይችላሉ፡፡ ከተማሪው ጋር በሚያደርጉአቸው ውይይቶች ልዩ አነጋገርና ለመረዳት የሚያስቸግር ቋንቋን ያስወግዱ፡፡ ስለዚህ ብዙውን ጊዜ የማይታወቅ ግን እርስዎ ሊጠቀሙበት የሚገባ የሆነውን ልዩ ቋንቋ የኮርሱ ተሳታፊ እንደሚረዳው ያረጋግጡ፣ እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ ማብራሪያ ቢጠይቁ ጥሩ እንደ ሆነ አዘውትረው ያሳስቡአቸው፡፡ በተጨማሪም የተወሳሰቡ ሃሳቦች ሲያስረዱና በምሳሌዎች፣ ሊሆኑ በሚችሉ ነገሮች፣ እንዲሁም በአማራጮች አማካይነት በሚናገሩበት ጊዜ እየተወያዩ ያሉባቸውን ሃሳቦች ግልጽ ለማድረግ የድምጽና ምስል (ኦዲዮ-ቪዥዋል) መሣሪያዎችን መጠቀም የሚረዳ ሊሆን ይችላል፡፡